Posts

Hawassa University Expresses its grief on the death of our late Prime Minister His Excellency Mr. Meles Zenawi. The University wishes strength for his family and the Ethiopian People.

Image
продвижение сайтов Hawassa University Expresses its grief on the death of our late Prime Minister His Excellency Mr. Meles Zenawi. The University wishes strength for his family and the Ethiopian People.

በኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የደቡብ ኢትዮጵያ ህብረት ጽህፈት ቤት ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሀዋሪያት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት፣ የሀዋሣ ጐተራ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡

  በኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የደቡብ ኢትዮጵያ ህብረት ጽህፈት ቤት ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሀዋሪያት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት፣ የሀዋሣ ጐተራ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የሀገራችን የልማት ሀዋሪያ፣ የምን ጊዜም ጀግና ፣ የፍሪካ ኩራት ናቸው፡፡ በሞት ቢለዩንም ህያው ሥራዎቻቸው በኢትዮጵያውያን ልብ ሲታወሱ ይኖራሉ ብለዋል፡፡   ለሀይማኖት መስፋፋት፣ ነፃነትና እኩልነት የተጉ መሪ እንደነበሩ ያመለከቱት መግለጫ ሰጪዎች በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች እጅ ለእጅ ተያይዘን የተጀመሩ የልማት ተግባራትን ከዳር ለማድረስ ቆርጠን እንሠራለን ብለዋል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/21NehTextN604.html  

የሲዳማ ዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መመሪያ፣ የእዥ ወረደ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል፡፡

ክቡር ጠቀላይ ሚኒስትር የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን እንዲሁም የህፃናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ ምቹ የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ በርሳቸው አመራር ኃላ ቀርነትን ታሪክ ለማድረግና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል መሠረት ተጥሏል፡፡ ይሁን እንጂ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሞት የከፋ ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል፡፡   በተመሳሳይ የሀዋሳ እርሻ ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማህበር ሀዋሣ ቅርንጫፍ ሀገራችንን በበሳል አመራር ላለፉት 21 አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በመምራትና ትክክለኛ የእድገት መንገድ በመቀየስ መሪ ሚና የተጫወቱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር በመለየታቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው አመልክተዋል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/21NehTextN204.html

የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳን በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ (ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ)

Image
የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳ በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡  በሕገ-መንግስቱ በአንቀጸ 39 ላይ የተደነገገውን መብት እስክንጎናጸፍ ድረስ የማንነት ጥያቄአችን ከምንም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ በምንም ዓይነት ሁኔታ አይቆምም!!! ውድ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ በሙሉ እንኳን በዓይነቱ ልዩ ለሆነውና በሲዳማ ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል ለሚገባው ለ2005 ዓ.ም ሲዳማ የዘመን መለወጫ fichee cambalaalla በዓል ለማየት፣ለመስማት አበቃችሁ/ በሰላም አደረሳችሁ/ን/!!  የሲዳማ ዘመን መለወጫ የfichee cambalaalla በዓል ነሐሴ 9/2004/ በሲዳማ ቀን አቆጣጠር መስከረም 1/ 2005 ዓ.ም በአስገራሚ ሁኔታ ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫዉ ወደ ሀዋሳ የመጡት የብሔሩ ተወላጆች ብቻ ሌሎች ታዳሚዎችን ሳይጨምር በጥቂቱ ቁጥራቸው ወደ 2.5ሚሊየን የሚጠጉ በባህላዊ አጋጌጥ ተውበው ጦርና ጋሻቸውን አንግበው በዋና ከተማቸው በድምቀት ለማክበር በቄጣላ በመግባታቸው የከተማውን ሕዝብ ጉድ ያስባለና ያስደነቀ ታሪካዊ በዓል መሆኑ ይታወሳል፡፡  በዕለቱም ሰፊው የሲዳማ ሕዝብና የበዓሉ ታዳሚዎች/ተጋባዥ እንግዶች በዓሉን እንደጓጉለት ለማክበር አልታደሉም፡፡ በዓሉን ለማክበር የወጣውን የሕዝብ ብዛት ከሩቁ የተመለከቱና ከየአቅጣጫው በቄጣላ የዘመኑ የሙዚቃ ቅንብር በማይተካ መ

ከተለያዩ የሲዳማ ዞን ወረዳዎች የተወጣጡ ሰዎች ለኣቶ መለሰ ዜናዊ በሲዳማ ባህል መሰረት እንጨት ተክሎ ማልቀሳቸው ተሰማ

በትናንትናው እለት ቁጥራቸው ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ መለስ ዜናዊ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል መሰረት ኣልቅሰዋል። በሲዳማ ባህል መሰረት ለጀግና እንደምለቀሰው ሁሉ ለኣቶ መለሰ ዜናዊም እንጨት ተተክሎ ቀይ ተቀብቶ የተለቀሰላቸው ሲሆን፤  'ጎባ ባኢታ ኣና ሆጌ' እያለ በቄጣላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። በሃዘን መግለጫ ስነስርዓቱ ላይ ከሽማግሌዎች የተወከሉ እና የክልል መንግስቱ ባለስልጣናት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸው በኣቶ መለሰ ዜናዊ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከዳር እንዲደርሱ ሁሉም በጋራ እንዲሰራ ጥር ኣቅርበዋል። በስነስርዓቱ ላይ የክልል እና የሲዳማ ዞን ባላስልጣናትን ጨምሮ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እና መንግስት ባዘጋጃቸው መኪኖች ባህላዊ ልብስ እንዲለብሱ ተደርገው ከየወረዳዎቹ የተጋበዙ ሰዎች መገኘታቸውን ወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘግቧል ።