Posts

የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳን በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ (ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኘ ጽሁፍ)

Image
የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳ በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡  በሕገ-መንግስቱ በአንቀጸ 39 ላይ የተደነገገውን መብት እስክንጎናጸፍ ድረስ የማንነት ጥያቄአችን ከምንም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ በምንም ዓይነት ሁኔታ አይቆምም!!! ውድ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ በሙሉ እንኳን በዓይነቱ ልዩ ለሆነውና በሲዳማ ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል ለሚገባው ለ2005 ዓ.ም ሲዳማ የዘመን መለወጫ fichee cambalaalla በዓል ለማየት፣ለመስማት አበቃችሁ/ በሰላም አደረሳችሁ/ን/!!  የሲዳማ ዘመን መለወጫ የfichee cambalaalla በዓል ነሐሴ 9/2004/ በሲዳማ ቀን አቆጣጠር መስከረም 1/ 2005 ዓ.ም በአስገራሚ ሁኔታ ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫዉ ወደ ሀዋሳ የመጡት የብሔሩ ተወላጆች ብቻ ሌሎች ታዳሚዎችን ሳይጨምር በጥቂቱ ቁጥራቸው ወደ 2.5ሚሊየን የሚጠጉ በባህላዊ አጋጌጥ ተውበው ጦርና ጋሻቸውን አንግበው በዋና ከተማቸው በድምቀት ለማክበር በቄጣላ በመግባታቸው የከተማውን ሕዝብ ጉድ ያስባለና ያስደነቀ ታሪካዊ በዓል መሆኑ ይታወሳል፡፡  በዕለቱም ሰፊው የሲዳማ ሕዝብና የበዓሉ ታዳሚዎች/ተጋባዥ እንግዶች በዓሉን እንደጓጉለት ለማክበር አልታደሉም፡፡ በዓሉን ለማክበር የወጣውን የሕዝብ ብዛት ከሩቁ የተመለከቱና ከየአቅጣጫው በቄጣላ የዘመኑ የሙዚቃ ቅንብር በማይተካ መ

ከተለያዩ የሲዳማ ዞን ወረዳዎች የተወጣጡ ሰዎች ለኣቶ መለሰ ዜናዊ በሲዳማ ባህል መሰረት እንጨት ተክሎ ማልቀሳቸው ተሰማ

በትናንትናው እለት ቁጥራቸው ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ መለስ ዜናዊ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል መሰረት ኣልቅሰዋል። በሲዳማ ባህል መሰረት ለጀግና እንደምለቀሰው ሁሉ ለኣቶ መለሰ ዜናዊም እንጨት ተተክሎ ቀይ ተቀብቶ የተለቀሰላቸው ሲሆን፤  'ጎባ ባኢታ ኣና ሆጌ' እያለ በቄጣላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። በሃዘን መግለጫ ስነስርዓቱ ላይ ከሽማግሌዎች የተወከሉ እና የክልል መንግስቱ ባለስልጣናት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸው በኣቶ መለሰ ዜናዊ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከዳር እንዲደርሱ ሁሉም በጋራ እንዲሰራ ጥር ኣቅርበዋል። በስነስርዓቱ ላይ የክልል እና የሲዳማ ዞን ባላስልጣናትን ጨምሮ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እና መንግስት ባዘጋጃቸው መኪኖች ባህላዊ ልብስ እንዲለብሱ ተደርገው ከየወረዳዎቹ የተጋበዙ ሰዎች መገኘታቸውን ወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘግቧል ።  

Ethiopia: Power scramble after premier’s death puts fragile state on the edge

Image
By Juma Kwayera Who is the Prime Minister? Aug 26, 2012, Nairobi (Standard) — Governing Ethiopia People’s Revolutionary and Democratic Front (EPRDF) faces an uncertain future following the death of Prime Minister Meles Zenawi. Ethnicity, as ever, is going to determine who takes over the reins of power. A week after Zenawi’s death was made public, the scramble for power has intensified with the members of the politburo of EPRDF said to be slugging it out, pointing to an imminent political turbulence or even a falling out. At the centre of the ensuing power struggle is acting Prime Minister Hailemariam Desalegn, his predecessor at the Foreign ministry and ambassador to China Seyoum Mesfin and Zenawi’s widow Azeb Mesfin, who had been tearing into each other long before the fallen Prime Minister became indisposed. There are also prominent political figures in the governing party Zenawi had suppressed as he maintained a stronghold on power. Smooth transition Altho

የሳምንቱ ምርጥ ጎል በገብረ ስላሴ

Image
New

ዩ ኤስ ኤ ኣትላንታ የሚኖሩ የሲዳማ ዲያስፖራ ኮሚኒት ኣባላት በሲዳማ ዞን የክልል ጥያቄን ኣስመልክቶ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት ኣሉ፤ የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክልል ጥያቄውን የመምራት ኃላፊነት እንዲዎስዱ ጠየቁ

Image
New ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በኣሜሪካን ኣገር በኣትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኣንዳንድ የሲዳማ ዳይስፖራ ኮሚኒት ኣባላት ለወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ከሁለት ወራት ጀምሮ  በመላዋ ሲዳማ የተቀጣጠለው የክልል ጥያቄ ማዕበል ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት። መንግስት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ለመንጠቅ ያደረገው ጥረት መክሸፉን ተከትሎ ጊዜ እየጠበቀ የሚነሳው የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በጋር ማስተዳደር የሚል የክልል መንግሥት ኣመለካከት ያንገሸገሻቸው የሃዋሳ ከተማ ባለቤቶች ያነሱት የክልል ይገባኛል ጥያቄ ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ መቀጠል ኣለበት ያሉት ዳያስፖራዎቹ፤ ኣዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት ኣመራር ሀገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ለህዝባዊው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ኣለባቸው ብለዋል። የሲዳማ ህዝብ ክልል ይገባኛል ጥያቄ  ሲያነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ኣለመሆኑን ያስታወሱት እነኝው ኣስተያየት ሰጪዎች፤ የዛሬ ኣስር ኣመት በተመሳሳይ መልኩ የተነሳው የህዝባዊ ጥያቄ በዞኑ ምክር ቤት ኣባላት ጭምር ተቀባይነት ኣግኝቶ መቶ በመቶ ድጋፊ ለሚመለከተው ኣካል መቅረቡ ተናግረዋል። ይሁን እና በጊዜው የሚመለከተው የመንግስት ኣካል የክልል ይገኛል ጥያቄውን በልማት እንዲቀየር ባቀረበው ኣማራጭ የክልል ጥያቄ ተደብስብሶ የታለፈ ቢሆንም በሰፊው የሲዳማ ህዝብ ልብ ውስጥ ግን ተቀብሮ  መቅረቱ ኣሁን ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄውን እንዲያነሳ ማገደዱን ኣስረድዋል። በኣሁኑ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ የተነሳው ክልል ይገባኛል ጥያቄ እንደከዚህ በፊት በተለያዩ ማባቢያዎች ተደብስብሶ  እንዳይቀረ ህዝቡ በመንግስት ማባቢያዎች ሳይታለል ለጥያቄ መሳከት ተግተው እንዲሰራ ኣደራ ብለዋል።  ኣክለውም የህዝቡን ጥያቄ  ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቅረብ በሽማግሌ