Posts

Ethiopia: Power scramble after premier’s death puts fragile state on the edge

Image
By Juma Kwayera Who is the Prime Minister? Aug 26, 2012, Nairobi (Standard) — Governing Ethiopia People’s Revolutionary and Democratic Front (EPRDF) faces an uncertain future following the death of Prime Minister Meles Zenawi. Ethnicity, as ever, is going to determine who takes over the reins of power. A week after Zenawi’s death was made public, the scramble for power has intensified with the members of the politburo of EPRDF said to be slugging it out, pointing to an imminent political turbulence or even a falling out. At the centre of the ensuing power struggle is acting Prime Minister Hailemariam Desalegn, his predecessor at the Foreign ministry and ambassador to China Seyoum Mesfin and Zenawi’s widow Azeb Mesfin, who had been tearing into each other long before the fallen Prime Minister became indisposed. There are also prominent political figures in the governing party Zenawi had suppressed as he maintained a stronghold on power. Smooth transition Altho

የሳምንቱ ምርጥ ጎል በገብረ ስላሴ

Image
New

ዩ ኤስ ኤ ኣትላንታ የሚኖሩ የሲዳማ ዲያስፖራ ኮሚኒት ኣባላት በሲዳማ ዞን የክልል ጥያቄን ኣስመልክቶ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት ኣሉ፤ የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክልል ጥያቄውን የመምራት ኃላፊነት እንዲዎስዱ ጠየቁ

Image
New ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በኣሜሪካን ኣገር በኣትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኣንዳንድ የሲዳማ ዳይስፖራ ኮሚኒት ኣባላት ለወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ከሁለት ወራት ጀምሮ  በመላዋ ሲዳማ የተቀጣጠለው የክልል ጥያቄ ማዕበል ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት። መንግስት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ለመንጠቅ ያደረገው ጥረት መክሸፉን ተከትሎ ጊዜ እየጠበቀ የሚነሳው የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በጋር ማስተዳደር የሚል የክልል መንግሥት ኣመለካከት ያንገሸገሻቸው የሃዋሳ ከተማ ባለቤቶች ያነሱት የክልል ይገባኛል ጥያቄ ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ መቀጠል ኣለበት ያሉት ዳያስፖራዎቹ፤ ኣዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት ኣመራር ሀገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ለህዝባዊው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ኣለባቸው ብለዋል። የሲዳማ ህዝብ ክልል ይገባኛል ጥያቄ  ሲያነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ኣለመሆኑን ያስታወሱት እነኝው ኣስተያየት ሰጪዎች፤ የዛሬ ኣስር ኣመት በተመሳሳይ መልኩ የተነሳው የህዝባዊ ጥያቄ በዞኑ ምክር ቤት ኣባላት ጭምር ተቀባይነት ኣግኝቶ መቶ በመቶ ድጋፊ ለሚመለከተው ኣካል መቅረቡ ተናግረዋል። ይሁን እና በጊዜው የሚመለከተው የመንግስት ኣካል የክልል ይገኛል ጥያቄውን በልማት እንዲቀየር ባቀረበው ኣማራጭ የክልል ጥያቄ ተደብስብሶ የታለፈ ቢሆንም በሰፊው የሲዳማ ህዝብ ልብ ውስጥ ግን ተቀብሮ  መቅረቱ ኣሁን ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄውን እንዲያነሳ ማገደዱን ኣስረድዋል። በኣሁኑ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ የተነሳው ክልል ይገባኛል ጥያቄ እንደከዚህ በፊት በተለያዩ ማባቢያዎች ተደብስብሶ  እንዳይቀረ ህዝቡ በመንግስት ማባቢያዎች ሳይታለል ለጥያቄ መሳከት ተግተው እንዲሰራ ኣደራ ብለዋል።  ኣክለውም የህዝቡን ጥያቄ  ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቅረብ በሽማግሌ

የሲዳማ ዞን ግብርና መምሪያ አመራሮችና ሠራተኞችን ጨምሮ በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸወን ሀዘን እየገለጹ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት መሪር ሀዘናቸዉን የገለጡት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ልማት ማህበርና ፣በጋሞ ጎፋ ዞን የጨንቻ ወረዳ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ወጣቶች፣ የክልሉ መምህራን ማህበር ጽህፈት ቤት አመራርና ሰራተኞች ፣የቡታጅራ ፍሬ ደረጃ አንድና ሁለት፣ደቡብ አድማስ ደረጃ ሶስት መለስተኛና አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር ናቸዉ ። በተጨማሪ የሲዳማ ዞን ግብርና መምሪያ አመራሮችና ሠራተኞች ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን ገልጠዋል ። ተቋማቱና ማህበራቱ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት መሪር ሀዘን ያሳደረብን ቢሆንም እርሳቸው ጥለውልን ያለፏቸውን መልካም ስራዎች፣ ፖሊስዎችና ስትራቴጂዎችን በማስቀጠል ራእያቸዉን እናሳካልን ሲሉ በአንድ መንፈስ አረጋገጠዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከአባይ ወንዝ አገራችን ተጠቃሚ እንድትሆን እስከ ዛሬ የነበሩ የትኛዎቹም የኢትዮጵያ መንግስታት ያለደፈሩትን የታላቁን የሀዳሴ ግድብ ግንባታ በማስጀመር ጀግንነታቸዉን በገሀድ ያሳዩና መላዉን ኢትዮጵያዊ ያኮሩ መሪ መሆናቸዉን በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል ። በብልሁ መሪያቸን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን እንዲሁም የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት ከመቼውም በበለጠ ጠንክረን እንስራለን ሲሉ በቁጭት አረጋግጠዋል ።

7 አባላትን ያቀፈ አንድ ቡድን ሀገሪቱን የመምራት ስራ ተረከበ

Image
ኢሳት የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ትናንት እንደዘገበዉ የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁኑ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት በአቶ ስዩም መስፍን የበላይነት የሚመራ 7 አባላትን ያቀፈ አንድ ቡድን ሀገሪቱን የመምራት ስራ የተረከበ ሲሆን ፤ 4 አባላቱ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸዉ፡፡  ምንም እንኳን ሐይለማሪያም ደሳለኝ በግዜያዊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመተካት የአመራሩን ቦታ እንደተረከቡ በኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ቢገለፅም ሀገሪቱን የመምራት ስልጣን ግን በዚህ ቡድን እጅ ነዉ ሲል ያተተዉ ይህ የኢሳት ዘገባ ቡድኑ የትግራዮች የበላይነት በሰፊዉ የነገሰበት ነዉ ሲል አብራርቷል፡፡ በዚህ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ በአቶ ስዮም መስፍን በሚመራዉ ቡድን ዉስጥ ምክትል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ብርሀነ ገብረ ክርስቶስ በምክትል ሊቀመንበርነት የተሰየሙ ሲሆን ፤ የመከላከያ ኢታማጆር ሹም የሆነዉ ጀኔራል ሳሞራ የኑስና የሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸዉ አሰፋ በአባልነት ይገኙበታል፡፡ ተያይዞም እንደተጠቆመዉ በቡድኑ ዉስጥ ከብአዴን ፣ ኦህዴድና ዴህዴን አንድ አንድ አባላት ተካተዋል፡፡ ቡድኑ ላዕላይና ታህታይ በሚል መዋቅር የተከፈለ ነዉ ያለዉ የኢሳት ዘገባ ምንም እንኳን በላዕላይ የአመራር መዋቅር ዉስጥ አጋር ድርጅቶች ባይሳተፉም በታችኛዉ መዋቅር ዉስጥ ይገኛሉ ሲል ጠቁሟል፡፡ ዘገባዉ አያይዞ እንደገለፀዉ ስርዓቱ ይህንን የአመራር ቡድን ለመፍጠር የተገደደዉ ምራባዉያኑንም ያስማማዉ በህወሓት ዉስጥ ጭምር በታየዉ የጎላ መከፋፈል ምክንያት ሁሉን የሚያስማማ መሪ መምረጥ አስቸጋሪ ሁኖ በመገኘቱ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከታሰቡ ሰዎች መካከል አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ዋና ዋና የህወሓት ባለስልጣናት የፓርላማ አባል