Posts

የኣቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በሲዳማ ሲጧጧፍ የነበረው እስር ጋብ ማለቱ ተገለጸ

የሲዳማ ክልል ጥያቄን ኣንግቦ በተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል ሃዋሳ ከተማን ጭምሮ በተለያዩ የሲዳማ ወረዳዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ይካሄድ የነበረው ግለሰቦችን የማሰር እንቅስቃሴ ጋብ ብሏል። በኣለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች መታሰራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከታሰሩት ማካከል ካላ ብርሃኑ ሀንካራን ጨምሮ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ሃዋሳ ከተማ ከምገኘው ፍርድ ቤት የቀረቡ ወደ ኣስር የሚሆኑ ግለሰቦች ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ ማረሚያ ቤት ተመልሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ መለስ ዜናዊን ይተካሉ ተብሎ የሚጠበቁት የኣገሪቱ ምክትም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኣቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሲዳማ የክልል ጥያቄን በተመለከተ በምኖራቸው ኣቋም ላይ የተለያዩ ኣስተያዬቶች እየተሰጡ ነው። ያነጋገርናቸው  ካላ ደመቀ ዳንጋሞ እና ቤላሞ ባሻ   የሃዋሣ ከተማ ነዋሪዎች እንደምሉት ከሆነ፤ ኣቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሲዳማ ህዝብ ጋር የኖሩና ሲዳማን ህዝብ ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸው ለክልል ጥያቄው ኣዎንታዊ ምላሽ ልሰጡ ይችላሉ። ይህንን ኣስተያየት የተቃረኑት ካላ ኣስፋ ላላንጎ እና ካላ ናኦራ ቡኤ በበኩላቸው፤ ኣቶ ኃይለማርያም ካለፉት ኣስር ዓመታት ጀምሮ ጸረ ሲዳማ ኣቋም ያላቸው እና ከኣስር ኣመታት በፊት በርካታ ሲዳማዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እንዲገደሉ ካደረጉት የደቡብ ክልል ባላስልጣናት መካከል ኣንዱ በመሆናቸው የክልል ጥያቄውን በተመለከት የሚኖራቸው ኣቋም ኣዎንታዊ ልሆን ኣይችልም ብለዋል። ክቡራን የብሎጋችን ኣንባቢያን የሲዳማ ክልል ጥያቄ እና የወደፊት እጣ ፋንታ በተመለከተ ያላችሁን ኣስተያየት በሚከተለው ኣድራሻ ላኩልን፦ no

Life after Ethiopia's Meles Zenawi - Inside Story - Al Jazeera English

Life after Ethiopia's Meles Zenawi - Inside Story - Al Jazeera English New

ኢትዮጵያ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በኋላ

Image
በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት በኢትዮጵያ የሥልጣን ሳይሆን የአመራር ብቃት ክፍተት ሊያጋጥም እንደሚችል አንድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አስታወቁ ። በአለም አቀፉ የፀጥታ ጉዳዮች ጥናት ተቋም አጥኚ ዶክተር መሐሪ ታደለ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በመለስ አለመኖር አገሪቱ የሥልጣን ክፍተት አያጋጥማትም እስካሁን የመረጋጋት ችግር እልታየባትምም ፣ወደፊት ግን የአመራር ብቃት ክፍተት ሊኖር ይችላል ። በፖለቲካው መስክ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ደግሞ ገዥው ፓርቲ የምክክር ና የስምምነት መድረኮችን ማዘጋጀቱ ጠቃሚ ይሆናል ብለዋል ። ላለፊት 21 አመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከመሩት ከአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ የገዥው ፓርቲ የኢህአዲግ አመራር እንዴት ይቀጥላል ? ኢትዮጵያስ ከመለስ በኋላ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የምታገኘው ድጋፍና የሚኖራት ተቀባይነት ምን ይሆናል ? መለስስ በምን ይታወሳሉ የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች ማነጋገራቸውን ቀጥለዋል ። በአለምአቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ጥናት ተቋም ተመራማሪ ዶክተር መሐሪ ታደለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአመራር ዘመናቸው በኤኮኖሚና ማህበራዊ መስኮች ለኢትዮጵያ አዳዲስ ውጤቶች ማሰገኘታቸው ይጠቅሳሉ ። በፖለቲካው መስክ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይከተሉት የነበረው መርህ ብዙ ችግሮችና ቅሬታዎች ያስከተሉ እንደነበር ዶክተር መሐሪ ገልፀዋል ። ይም ሆኖ ሃገሪቱ መሠረታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንድትገባ ያደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ ብለዋል ። ከእንግዲህ በኋላስ የሚለው ሌላው ጥያቄአችን ነበር ። ዶክተር መሃሪ እንደሚሉት በተለይ አቶ መለስ ጥሩ አመራር ሰጥተው ውጤት አሳይተዋል ባሉት የኢኮኖሚ መስክ የታዩ ለውጦችን መቀጠል ከባድ ፈተና መሆኑን ይገልፃሉ ። በፖለቲካ መስክ ደግሞ አሁ

ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩትን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት የሰማነው በታላቅ ድንጋጤና መሪር ሐዘን ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ለማስወገድ በተደረገው ትግል በመታገልና በማታገል ለሀገራችን ለውጥ ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡ እንዲሁም ሀገራችን የህገ መንግስት ባለቤት እንድትሆንና በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሰረት ጠንካራ መንግስት እንዲኖራት ለማድረግ የታገሉ ግንባር ቀደም መሪያችን ነበሩ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ለተመዘገበው እድገት መሰረት የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ነደፈው ተግባራዊ እንዲደረግ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱና በነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አማካኝነት ለተመዘገበው እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው መሪም ነበሩ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ የፌዴራል ስርዓት እውን እንዲሆን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ፣ ዛሬ የክልላችንና የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ለተጎናፀፏቸው ራስን በራስ የማስተዳደርና በልማት አስተዋጿቸው ልክ የመጠቀም አቅጣጫ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው መሪያችን በመሆናቸው የክልላችን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የዝንተ ዓለም ባለውለታ ናቸው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ችግር ፈቺ ሐሳቦችን በማመንጨትና በማፍለቅ ሀገራችንና አህጉራችን በአለም አቀፍ ደረጃ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነሰርዓት ተፈጸመ

Image
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ ። በቀብር ስነ ሰርዓቱ ላይ  ተጠባባቂ  ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ሚኒስትሮች ፣  የተለያዩ አገራት አብያተ ከርስቲያናት መሪዎች ፣ አምባሳደሮችና  በሺዎች የሚቆጠሩ  የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል ። በስነ ስርዓቱ ላይ  አቶ ሀይለማሪያም ብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አገሪቱን ከድህነት ለማላቀቅ በተደረገው ጥረት ከፍተኛ ተሳታፊ የነበሩ አባት ናቸው ብለዋል ። በቤተ ክርስቲያኗም ሆነ በአገሪቱ በተከናወኑ የልማት ስራዎች ከነበራቸው ተሳትፎ ባለፈ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት  ዘንድ ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም የአገራቸውን  በጎ ገፅታ ያሳወቁ ብልህ አባት ነበሩ ሲሉም ገልጸዋቸዋል። የአቡነ ጳውሎስን የበጎ አድራጎት ተግባር ተሳትፎን  ያስታወሱት አቶ ሀይለማሪያም ፥ በኤች አይ ቪ /ኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በመደገፉ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት በመከላከሉ ረገድ ያከናወኗቸው ስራዎች የሚያስመሰግናቸው ነው ብለዋል ። የዓለም አብያተ ክስርስቲያናት ምክር ቤት ፀሃፊ በበኩላቸው የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ጳውሎስ ለዓለም ሰላም የሰሩና የአመራር ብቃታቸውንም ብዙዎች አርዓያ የሚያደርጉት መሆኑን ተናግረዋል ። በ76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አቡነ ጳውሎስ ከ1985 ዓመተ መህረት ጀምሮ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አምስተኛ ፓትሪያሪክ  ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል ። በ1999 ዓመተ ምህረት በብራዚል በተካሄደው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጉባኤ ላይም የምክር ቤቱ