Posts

ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በታማኝነት አገራቸውን አገልግለው ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ያሳዩትን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት የሰማነው በታላቅ ድንጋጤና መሪር ሐዘን ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ለማስወገድ በተደረገው ትግል በመታገልና በማታገል ለሀገራችን ለውጥ ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡ እንዲሁም ሀገራችን የህገ መንግስት ባለቤት እንድትሆንና በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መሰረት ጠንካራ መንግስት እንዲኖራት ለማድረግ የታገሉ ግንባር ቀደም መሪያችን ነበሩ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ለተመዘገበው እድገት መሰረት የሆኑ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ነደፈው ተግባራዊ እንዲደረግ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱና በነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አማካኝነት ለተመዘገበው እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው መሪም ነበሩ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ የፌዴራል ስርዓት እውን እንዲሆን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ፣ ዛሬ የክልላችንና የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ለተጎናፀፏቸው ራስን በራስ የማስተዳደርና በልማት አስተዋጿቸው ልክ የመጠቀም አቅጣጫ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው መሪያችን በመሆናቸው የክልላችን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የዝንተ ዓለም ባለውለታ ናቸው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ችግር ፈቺ ሐሳቦችን በማመንጨትና በማፍለቅ ሀገራችንና አህጉራችን በአለም አቀፍ ደረጃ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነሰርዓት ተፈጸመ

Image
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ ። በቀብር ስነ ሰርዓቱ ላይ  ተጠባባቂ  ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ሚኒስትሮች ፣  የተለያዩ አገራት አብያተ ከርስቲያናት መሪዎች ፣ አምባሳደሮችና  በሺዎች የሚቆጠሩ  የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል ። በስነ ስርዓቱ ላይ  አቶ ሀይለማሪያም ብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አገሪቱን ከድህነት ለማላቀቅ በተደረገው ጥረት ከፍተኛ ተሳታፊ የነበሩ አባት ናቸው ብለዋል ። በቤተ ክርስቲያኗም ሆነ በአገሪቱ በተከናወኑ የልማት ስራዎች ከነበራቸው ተሳትፎ ባለፈ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት  ዘንድ ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም የአገራቸውን  በጎ ገፅታ ያሳወቁ ብልህ አባት ነበሩ ሲሉም ገልጸዋቸዋል። የአቡነ ጳውሎስን የበጎ አድራጎት ተግባር ተሳትፎን  ያስታወሱት አቶ ሀይለማሪያም ፥ በኤች አይ ቪ /ኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በመደገፉ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት በመከላከሉ ረገድ ያከናወኗቸው ስራዎች የሚያስመሰግናቸው ነው ብለዋል ። የዓለም አብያተ ክስርስቲያናት ምክር ቤት ፀሃፊ በበኩላቸው የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ጳውሎስ ለዓለም ሰላም የሰሩና የአመራር ብቃታቸውንም ብዙዎች አርዓያ የሚያደርጉት መሆኑን ተናግረዋል ። በ76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አቡነ ጳውሎስ ከ1985 ዓመተ መህረት ጀምሮ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አምስተኛ ፓትሪያሪክ  ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል ። በ1999 ዓመተ ምህረት በብራዚል በተካሄደው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጉባኤ ላይም የምክር ቤቱ

በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቀረቡለት 1ሺህ 4 መቶ 11 የክስ መዛግብት ለ1ሺህ 3መቶ 90 ውሣኔ መስጠቱን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ፍርድ ቤት ገለፀ፡፡

የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ወንድሙ ቂጤሶ እንደገለተጹት  በተጠናቀቀው በጀት አመት ጽህፈት ቤቱ ከቀረቡለት 1ሺህ 4 መቶ 11 የክስ መዛግብት ውስጥ 1 ሺ 3 መቶ 90 ዎቹ ውሣኔ መሰጠቱንና ቀሪዎቹ 21 መዛግብት ደግሞ ለቀጣዩ አመት ማስተላለፉን ተናግራል፡፡ ፍትህ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የአመቱነ አፈፃፀም 98 ነጥብ 5 ከመቶ ማድረሱን ጠቅሰው፤ ለቀጣዩ አመት መቶ በመቶ ለማድረስ ጠንክረው እየሰሩ አንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ አርሶ አደሩ ከልማት ሥራው ሣይለይ ፍተህ በአከባቢው ያገኘ ዘንድ በተቋቋሙ 4 ማዕከላት ፍትህ በመስጠት አበረታች ውጤት የተመዘገበ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አመት ወደ 6 ለማሣደግ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ አርሶ አደሩ በህገ ወጥ ደላላዎች ይገጥመው የነበረውን የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍ ጧት ከችሎት በፊት በባለሙያዎች ትምህርት እየተሰጠ እንዳለ ገልፀዋል፡፡የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/14NehTextN904.html

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብቡን አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በአመቱ ለመሰብሰብ ያቀደው 6 ሚሊዮን ብር ሲሆን  ከ9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሰበሰበብ መቻሉን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስራቅ በቴ ገልፀዋል ፡፡ የአመቱ እቅድ ክንውን አፈፃፀም 98 ነጥብ 2 ከመቶ መሆኑንና ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ3 ሚሊዮን 61ዐ ሺህ 196 ብር ብልጫ ማሳየቱን ኃላፊው አስረድተዋል ፡፡ ገቢው ሊሰበሰብ የቻለው ከቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም ከልዩ ልዩ ገቢዎች መሆኑን አብራርተዋል ፡፡ ለገቢው መጨመር የግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብር የመክፈል ግንበዛቤ እያደገ መምጣት፣ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነት መፈጠርና የወረዳው መስተዳደርና ባለድርሻ አካላት ከገቢ ሰብሳቢው ጽህፈት ቤት ጋር የተቀናጀ ሥራ በማከናወናቸው መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል ፡፡ በቀጣይ አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በማፈላለግ የተጀመረውን የ5 ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አቶ ምስራቅ መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል ፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/14NehTextN604.html

የደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን መሪር ሀዘን ገለፁ

  አዋሳ ነሐሴ 17/2004 በደቡብ ክልል የሚገኙ የተለያዩ መስሪያ ቤቶችና ተቋማት አመራር አባላትና ሰራተኞች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ነዉ ። የደቡብ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ፣የክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ፣የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋምና የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ሠራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች በታላቁ መሪያችን ሞት ጥልቅና መሪር ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል ። ቢሮዎቹና ተቋማቱ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ ላይ እንዳስታወቁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከወጣትነት እድሜያቸዉ ጀምሮ እስከ እለተ ሞታቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከድህነት ተላቆ በእድገትና ብልጽግና ጎዳና እንዲጓዝ ታላቅ ራእይ ሰንቀዉ የተነሱ ቆራጥና አስተዋይ መሪ ነበሩ ብለዋል ። የየቢሮዎችና የተቋማቱ ሰራተኞች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የአመራር ጥበባቸውን በመጠቀም ኢትዮጵያን በልማት ለማሳደግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አሁን ለደረሰንበት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ያበቁ ታታሪና ብልህ መሪ እንደነበሩ አስታዉቀዋል ። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ "ለመጪው ትውልድ ዕድገት፣ ብልፅግናና ልማትን እንጂ ድህነትን አናወርስም "በማለት በቆራጥነትና በታላቅ ኃላፊነት መንፈስ ሲሰሩ የቆዩ የለውጥ ሐዋሪያ ናቸው ሲሉ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኢትዮጵያ በአለም ከምትታወቅበት የተመፅዋችነትና የረሃብ ታሪክ እንድትላቀቅ በዓለም ትልቅ የልማት ተስፋ ሆነው ከሚታዩ የዓለም አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደረጉ ጀግናና በሳል መሪ ነበሩ ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የእርሳቸዉን በጎ ተግባር በመከተል ብቃት ያለው የልማት ሠራዊት መሆን የሚችል በሁሉም መስክ የሰለጠነ የሰው