የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ዕረፍት አስመልክቶ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሰጡት አስተያየት
በመገናኛ ብዙኅን የሰማሁት ነገር እጅግ ልብ የሚነካና የሚያሳዝን ነው፡፡ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትልቅ ራዕይና አቅም የነበራቸው መሪ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ይኼ ነው የማይባል ጊዜያቸውን መስዋዕት አድርገው፣ አምባገነኑን የደርግ ሥርዓትን መክቶ ማሸነፍ የቻለ ፓርቲ መመሥረት የቻሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ ከዚያም በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ነው የማይባል የፖለቲካና የኢኮኖሚ መነቃነቅን የፈጠረ አቅም የነበራቸው ግለሰብ ነበሩ፡፡ ወደፊትም በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም ርቀትን ለመሄድ የሚያስችል አቅም የነበራቸው ግለሰብ ናቸው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ለኢትዮጵያ ካቀዱትና ይዘውት ከተነሱት ዓላማ አኳያ መታጣታቸው እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ በተረፈ እንደ አባት ደግሞ ለቤተሰቦቻቸው እጅግ ትልቅ እጦት ነው፡፡ ለአፍሪካ ማኅበረሰብም አፍሪካን በማስተሳሰርና አንድነትን በማምጣት፣ በልማት መስመር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ቀላል የማይባል ሚና የተጫወቱ ግለሰብ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ስናያቸው እንደ አገር መሪ ይዘውትና ሰንቀውት የተነሱት ነገር ረጅም ርቀት የሚወስደን መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ወደፊትም ቢሆን በጀመሩት ነገር ላይ ተጨማሪ ሥራ ለመሥራት አቅም የነበራቸው ግለሰብ ነበሩ፡፡ እስከዛሬ ድረስ የሰበሰቡት ዕውቀት፣ ያከማቹት ግንዛቤና ተሞክሮ ወደሚቀጥለው ኃይል ተላልፎ አለማየትም ትልቅ እጦት ነው፡፡ በቀጣይ የሚጠበቀው ነገር ከኢሕአዴግ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ ላይ በሰፈረው መሠረት ኢሕአዴግ የሥልጣን ሽግግሩን በአግባቡ መወጣት አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ፣ በማያሻማና በሚታይ ሁኔታ መሆን አለበት እላለሁ፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ አገርን በማልማትና በማሳደግ ሒደት ውስጥ ቀዳዳ እንዳይኖረው