Posts

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ግለ ታሪክ

Image
የ ሲዳማ  ቡና ስፖርት  ክለብ ግለ ታሪክ አመሠራረት የሲዳማ   ቡና   ስፖርት   ክለብ   የተመሠረተው   በ 1997  ዓ . ም   ነው፡፡ ሲዳማ ቡና በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶችን በስፖርት በማሳተፍ የአካባቢውን ህዝብ የሚወክል ጠንካራ ቡድን ማቋቋም በሚል ህሳቤ በጥቂት ስፖርት ወዳድ ወጣቶች የተቋቋመ ቡድን ነው፡፡           ዳራ   በሲዳማ   ልዩ   ዞን   የአንድ   ወረዳ   ስያሜ   ስም  ነው፡፡  ክለቡ   ሲመሰረትም የነበረው ስያሜ ‹‹ዳራ   ክለብ››  የሚል ነው፡፡  ይሁንና ክለቡ በ1999ዓ.ም የገንዘብ ችግር ስለገጠመው የስም ለውጥ ለማድረግ ተገዷል፡፡ በዚህም መሰረት ክለቡ በ1999ዓ.ም በኢትዮጲያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ለመካፈል የገጠመውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ ሲል ለዞኑ ምክር ቤት ባቀረበው የዕርዳታ ጥያቄ መሠረት የክለቡ ስያሜ ‹‹ሲዳማ ዳራ›› ሊባል ችሏል፡፡ ይሁን እንጂ ክለቡ በዚህ ስያሜ ቢሆንም ብዙ መዝለቅ አልቻለም፡፡  ክለቡ በክልል ክለቦች ውድድር ወደ ብሄራዊ ሊግ የመሳተፍ ዕድልን አገኘ፡፡ ይህ ውድድር ደግሞ ከክልል ክልል በመዘዋወር የሚደረግ በመሆኑ ከፍተኛ ውጪ ይጠይቃል፡፡ ይህን ወጪ ደግሞ ዞኑ ብቻዬን የምቋቋመው አይደለም በማለቱ ለሦስተኛ ጊዜ የስም ለውጥ በማድረግ ዛሬ ያለውን ስያሜ እንዲይዝ ተደርጓል፡፡  የሲዳማ ልዩ ዞን በቡና ልማት ዘርፍ ከሚታወቁ የሀገራችን አካባቢዎች አንድዋ ናት፡፡ ስለሆነም አብዛኛው የአካባቢው ህብረተሰብ በቡና ልማትና ንግድ ዘርፍ የተሰማራ ነው፡፡ ከቡና ንግድ ጋር በተያያዘ በርካታ ባለሀብቶችም በዚህ ዞን ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም የስፖርት ክለቡን የገንዘብ ችግር በቀጣይነት ለመቅረፍና ክለቡን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የክለቡ ስያሜ የዞኑንና የነጋዴውን ማህ