Posts

በሲዳማ ዞን በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመፈጸም ላይ ያለው የሰብኣዊ መብት ረገጣና እስራት ቀጥሏል፤ ዛሬ ምሽት ላይ ሌሎች ሁለት ሰዎች ታሰሩ

Image
በሲዳማ ዞን ውስጥ የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ ሰዎች ህዝብ በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል እየታሰሩ ሲሆን፤ ሰሞኑን ታስረው ፍርድ ቤት በመቅረብ ላይ ካሉት በተጨማር ዛሬ ምሽት ላይ ካላ ጥሩነህ ቱቀላ የተባሉ በሲዳማ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሚስሩ የሁለት ልጆች ኣባት ከበንሳ የተሰሩ ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ  ካላ ደሳለኝ ወልደ ሚካኤል የተባሉ በዞኑ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የሚሰሩ የሶስት ልጆች ኣባት ከቦና ታስረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ሃዋሳ ከተማ እና በሌሎች የዞኑ ከተሞች እና ወረዳዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመታደን ላይ ናቸው። ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በላኩት መልእክት፤ የመንግስት ኃይሎች በደፈናው ሰዎችን የተለያዩ  ስሞችን እየለጠፉ በማሰር እና ሰብኣዊ መብት በመረገጥ ላይ ስለሆኑ የሚመለከተቸው የሰብኣዊ መብት ተቆርቋር ዓለም ኣቀፍ ኣካላት ጠልቃ እንዲገቡ ጥሪ ኣቅርበዋል። 

በሲዳማ ዞን ውስጥ የሰብኣዊ መብት ረገጣው ተባብሶ ቀጥሏል፤ እስከ ኣሁን ድረሰ ከመቶ የማያንሱ ሰዎች ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል ክስ ተመስርቶባቸው በመላው ሲዳማ ተስረዋል

በሲዳማ ዞን ውስጥ በመንግስታ የጸጥታ ኃይሎች እየተፈጸመ ያለው ሰብኣዊ መብት ረገጣ የተባባሰ ሲሆን በርካታ ሰዎች ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል በመታሰር ላይ ናቸው። በዞኑ ውስጥ የክልል ጥያቄን ጋር በተያያዘ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ንቅናቄ  ለመቀልበሰ በኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የምመራው የደቡብ ክልል መንግስት በሚያደርገው ጥረት የተለያዩ  ኣፈናዎችን በመፈጸም ላይ ነው። ሃዋሳ ከተማ የተጀመረው ግለሰቦችን የማሰር እና የማስፈራራት ተግባር ወደ ተለያዩ ወረዳዎችም የተዛመተ  ሲሆን፤ ለኣብነት ያህል ባላፈው ቅዳሜ ከታሰሩት 46 ግለሰቦች በተጨማሪ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ በጎርቼ ወረዳ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች  ታስረዋል። ሰሞኑን ከታሰሩት የሲዳማ ተወላጆች መካከል ጥቅቶቹ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ጉዳያቸው ከኣስራ ኣንድ ቀናት በኃላ እንዲታይ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስርቤት ተመልሰዋል። ዛሬ ከፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የቀድሞ የዳሌ ወረዳ ምክትል ኣስተዳዳሪ ካላ ዘገዬ ሀመሶ  እና ካላ ብርሃኑ ሀንካራ  ይገኑበታል።   ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሰዎች ሙሉዝርዝር ከታች ይመልከቱ  They were all presented to Court and appointed for 25 th of August 2004 E.C (11 days from now). They are to stay there until then!!! Cry freedom!! Cry Sidama!! Innocent Elites and Intellectuals are being brutalized in front of the world in the mid of 2012!!!  No Name

Sidama people have been paying ultimate sacrifice for the cause of regional self administration for several years. The following January 2006 VOA report explains how the situation was unfolding then.

Image
Part One  Part Two

ከተባበሩት የሲዳማ ፖለትካ ድርጅቶች የተሰጠ መግለጫ

በአገር ዉስጥና ውጭ ለምትገኙ ለስዳማ ተወላጆች በሙሉ  የሲዳማ ሕዝብ የማንንም በር አንኳክቶ ደጃፉንም ረግጦ አያውቅም። ዎሮበሎችና ሌቦች ግን በተከታታይ ዘመናት ለመዳፈር ሞክረዋል። የሲዳማ ሕዝብ ከአጼ ምንልክ ሥርወ መንግስት አንስቶ አሁን እየተንገዳገደ እስካለው የወያኔ ከፋፋይና ዋሾ መንግሥት ድረስ ለዲሞክራሲና ለነፃነቱ የምያደርገዉን ትግል ባለማቌረጥ በየደረጃዉም ያገኟቸውን ድሎች በማጎልበት ነፃና ያልተሸራረፈ የሥልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበትን ሥርዓት ለመመሥረት ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ኃይሎች ጋሪ ግንባር በመፍጠር ትግሉን በማፋፋም ላይ ይገኛል።ዛሬም ትግሉ ቀጥሎ ወደ አድስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ደርሰናል። አሁን ያለንበት ሁነታ በትዕብትና በጥላቻ የተዎጠረዉ ህወሃት/እሕአደግ በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው በደል ከምንግዘዉም የኬፋበት ነው።ጥቅት ግለሰቦችን በገንዘብና በስልጣን በመደለልና መማታለል የራሳቸዉን ጥቅም ያስጠብቃሉ፡በተለያየ መልኩ ከሕዝባችን በዘረፉት ገንዘብ መልሰዉ ሕይወቱን ለማኮላሸት ይጥራሉ፡ ብሳካላቸዉ አንድነታችንን ለማናጋትና ከፋፍለዉ ልገዙን ቀንና ሌልት ይደክማሉ፡ ብዙዎችንም ለስደትና ለመከራ ዳርገዋል፡ለዘመናት ተከባብረን ከኖርንባቸዉ ጎሮበቶቻችን ሕዝቦች ጋር ትንኮሳን በመፍጠር ለዕልቅት ለመዳረግ ይጥራሉ፡መሠረታዊ መብትን ለመጠየቅ የወጣዉን ሕዝባችንን በቈየዉ በግፍ ጨፍጭፈዋል።በአሁኑ ግዘ በተለይ በህገመንግስቱ የተደነገገዉን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንድሰጠዉ ህዝባችን ለአመታት ከዳር እስከዳር እየተንቀሳቀሰ ስጠይቅ የቆየዉን መብት ጥቅማቸውን ስለሚነካባቸዉ ከማስፈጸም ይልቅ ሕዝባችንን በእስራትና በአፈና ለማንበርከክ እየዳዳቸዉ ናችው። አምባገነኑ መር መለስ ዜናዊ ከተሰወሩ ወራቶች ቢያልፉም ከንቀታቸው የተነሳ መ

Hawassa Gobaye

Image
ሃዋሳ ጎባያ ሲዳሙ ሲርባ