Posts

የሲዳማን ኣዲስ ኣመት የፊቼን በኣል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው፤ የሲዳማ ቋንቋ ስምፖዚዬም እና ጫምባባላ በነገው እለት በሲዳማ ባህል ኣዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራሉ፤ ከፊቼ በኣል ጋር በተያያዘ በሃዋሳ ከተማ የጸጥታ ቁጥጥሩ መጥበቁ እየተነገረ ነው

በሃዋሳ ከተማ ነገ እና ከነገ ወዲያ የሚከበሩት የጫምባባላ እና የፊቼ በኣል፤ የሲዳማ ህዝብ መለያ እሴቶች በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ስጥተው ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶት ተደርገው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል። በበኣሉ ላይ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች የታጋበዙ ሰዎች ተሳታፊ እንደምሆኑ ሲገለጽ፤ በነገው እለት የጫምባባላ በኣል በሲዳማ  ባህል ኣዳራሽ ከሲዳማ ቋንቋ ስምፖዚዬም ጋር በጥምር ይከበራል። የዞኑ ማስታዎቂያ እና ባህል መምሪያ የቋንቋ ስምፖዚዬሙን ኣስመልክቶ ያዘጋጃቸውን ቲሸርት እና ኮፊያ ለበኣሉ ተሳታፊዎች በማደል ላይ ሲሆን፤በዚምፖዚዬሙ ላይ የሲዳማን ቋንቋ እና ባህል በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፎች እና ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሲዳማ ባህል ኣዳራሽ ዝግጅት ላይ እንድገኙ የተለያዩ የመንግስት ባላስልጣናትን ጨምሮ  ታዋቅ ሰዎች እና የሃዋሳ ከተማ  ነዋሪዎች ተጋብዘዋል። የፊቼ በኣል ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ከሲዳማ ህዝብ ወጪ በዞኑ ነዋሪ በሆኑ በሌሎች ብሄሮችም ጭምር እየተከበረ ያለ ሲሆን፤ ከሌሎች ኣካባቢዎችም  በርካታ ሰዎች በኣሉን ከሲዳማ  ህዝብ ጋር ለማክበረ ወደ ሃዋሳ ከተማ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሃዋሳ ከተማ  ኣስተዳዳር እና የሲዳማ ዞን ለበኣሉ ድምቀት የፖሊስ ማርሽ ኦርኬስትራ ያስመጡ ሲሆን፤ የፖሊስ ኦርኬስትራው  የተለያዩ ጣእመ  ዜማዎችችን  በበኣሉ ያቀርባል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ካለፈው ወር ጀምሮ ከሲዳማ ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሲዳማ ዞን ውስጥ ተነስቶ የነበረው  ህዝባዊ  ንቅናቄ  በፊቼ  ኣከባበር ላይ ችግር ልፈጥር ይችላል በምል የጸጥታ ቁጥጥሩ መጥበቁ እየተነገረ ሲሆን፤ ከሃዋሳ መግቢያ ላይ በተለይ ሞኖ ፖል ላይ ግለሰቦች የጦር መሳሪያ ይዘው ወደ ከተማ እንዳይገቡ እየተፈሹ ነው።

ኣንዳንድ በሲዳምኛ ቋንቋ ላይ የተሰሩ ጥናቶች

STUDENTS' ATTITUDE TOWARDS MOTHER TONGUEINSTRUCTION AS A CORRELATE OF ACADEMIC ACHIEVEMENT: THE CASE OF SIDAMA ABSTRACT The purpose of this study is to investigate students' attitude towards Sidamalanguage as a medium of instruction and its determination on the languageachievement.To carry out this aim, 391 students' were chosen from 7 Sidama Zone upperprimary schools. In addition to background information students were given withattitude and motivation questionnaires to measure their inclination towards the nativelanguage instruction. In the mean time students' one year cumulative GPA of Sidamalanguage were obtained from the record offices.Stepwise multiple regression analysis was conducted to find out the combinedand independent effect of the independent variables. Path analysis was employed toexamine the relationships among the predictor variables and between the predictorvariables and the criterion variable. Comparison of means and chi-square technique

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በሲዳምኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራም ሊከፍት ነው፡፡

Image
ሃዋሳ ነሃሴ 6/2004/በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብሄር ብሄረሰቦችን ቋንቋ ለትምህርትና ለምርምር ስራ ለማዋል እየሰራ መሆኑን የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት አስታወቁ፡፡ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሲዳምኛን ቋንቋን ለመጀመሪያ ጊዜ በድግሪ የትምህርት ፕሮግራም ለመጀመር መዘጋጀቱም ተመልክቷል፡፡ የሲዳምኛን ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ለማስተማር የተቀረጸው የስርዓተ ትምህርት ለመገምገምና የማዳበሪያ ሀሰብ ለማከል ትናንት በሀዋሳ ከተማ የምክከር መድረክ ተካሂዷል ። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦችን ማንነትን፣ ባህል፣ ታሪክና ወግ የሚጠናበትና የሚታወቅበት መንገድ ለማመቻቸት ራሱን የቻለ የቋንቋ ጥናት ትምህርት አስፈላጊ ነዉ ። ዩኒቨርስቲው በደቡብ ክልል ከ54 በላይ ብሄር ብሄረሰቦች ማዕከል በሆነችው ሀዋሳ ከተማ እንደመገኘቱ አሁን በሲዳምኛ ቋንቋ በድግሪ ደረጃ የትምህርት ፕሮግራሙን ለመክፈት የተደረገዉ ዝግጅት ተጠናቆ ከያዝነው ክረምት ጀምሮ ወደ ተግባርይሸጋግራል ብለዋል ። በሲዳምኛ ቋንቋ በድግሪ ደረጃ የሚጀምረዉ የትምህርት ፕሮግራም በማስፋፈት ወደፊት የሌሎችንም ብሄር ብሄረሰቦችን ቋንቋ በተመሳሳይ የመማሪያና የምርምር ስራ ለማዋል እቅድ መኖሩንም ዶክተር ዮሴፍ አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎች የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራም መከፈት የብሄር ብሄረሰቦችን ባህላዊ እሴት ከማሳደግ ባለፈ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ተናግረዋል ፡፡ የዩኒቨርስቲው የሶሻል ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ንጉሴ መሸሻ በበኩላቸው የሲዳምኛን ቋንቋን በድግሪ ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጠዋል ። በዚህ የትምህርት ደረጃ መኖሩ የብሄርሰቦች አፍ መፍቻ ቋ

ተቋሙ በተያዘው የበጀት ዓመት ከ1ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ሊያበድር ነው

አዋሳ ነሐሴ 05/2004 በደቡብ ክልል በተያዘው የበጀት ዓመት ቁጠባን መሰረት ያደረገ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ ለተጠቃሚዎች ማመቻቸቱን የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አሰታወቀ፡፡ በክልሉ በሚገኙ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች የተጀመረው የቁጠባ ኤክስቴንሽ አገልግሎት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመልክቷል፡፡ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሀላፊ አቶ ሰሎሞን ገለቱ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ብድሩ የተመቻቸው ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ተደራጅተውና በግል ስራ ፈጥረው ለሚንቀሳቀሱ ከ200 ሺ በላይ ተጠቃሚዎች ነው፡፡ ለስራቸው ማጠናከሪያና ማንቀሳቀሻ የሚሰራጨው ይሄው የብድር ገንዘብ ለእያንዳንዳቸው ከ5 ሺ እስከ 100 ሺ ብር የሚሰጥ መሆኑን አመልከተው ሰርተውበት ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ተመላሽ እንዲያደርጉ የክትትልና የሙያ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በተመሳሰይ ሲሰጥ የቆየው የብድር ገንዘብ በአብዛኛው ተመላሽ መደረጉን ያመለከቱት ኃላፊው ህብረተሰቡ የወሰደውን የብድር ገንዘብ በአግባቡ በመጠቀም በወቅቱ የመመለሱ ባህሉ እየዳበረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ከ896 ሺ በላይ አዲስና ነባር ደንበኞች ላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በቁጠባ ለማሰባሰብ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ባለፈው የበጀት ዓመት በክልሉ በሚገኙ ቀበሌዎች ባለሙያዎች በመመደብ የተጀመረው የገንዘብ ቁጠባ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሰሎሞን አመልክተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ በክልሉ የተለያዩ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ ከ3 ሺ በላይ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች መጀመሩን አመልከተው እስካሁንም ከ120 ሺ በላይ የቁጠባ ሳጥኖች ለተጠ

“በክር ሥራ ጀምራ በናይሮቢ ሱቅ የከፈተች የሃዋሳ ወጣት

Image
ፎቶ ኣዲስ ኣድማስ ፍላጐት እውቀትና ሙያ፣ ጉልበትና በራስ መተማመን እንጂ፣ ቤሳ ቤስቲን አልነበራትም፡፡ አንድ የቤትና የቢሮ ቁሳቁስ ማምረቻ ድርጅት ሄዳ ጣውላ በዱቤ እንዲሸጡላት ጠየቀች፡፡ የድርጅቱ ባለቤት ወጣቷ ሴት በድፍረትና በልበ ሙሉነት ባቀረበችላቸው ጥያቄ ቢገረሙም፣ “ከየት አምጥተሽ ልትከፍይኝ ነው? አይሆንም” አላሉም፡፡ “እሺ ውሰጂ” አሏት፡፡ ድርጅቱ የሽመና መሳሪያ አምርቶ አያውቅም፡፡ ስለዚህ ራሷ የመሸመኛውን፣ የማድሪያውን፣ የምርት መጠቅለያውን ዲዛይን ሠርታና እንጨት ገጣጥማ እያሳየች አሠራች፡፡ ክር መሸጫ ሄዳ በዱቤ፣ የ80 ብር ክር ወስዳ፣ በሽመና መሳሪያው ክሩን ወደ ጨርቅነት ለወጠችው፡፡ ከዚያም ጨርቁን ቆራርጣ መንገድ ዳር አሰፋች፡፡ በገና 1995 በዓል ዕለት ሰባት የሰፈር ሕፃናት ሰብስባ ያሰፋቻቸውን ልብሶች አልብሳ ለቀቀቻቸው - ሳትታዘዝ፡፡ የአራቱ ልብሶች ዋጋ ወዲያው ሲከፈላት ሦስቱ በዱቤ ተሸጡ፡፡ መቶ ብር በማይሞላ የክር ዱቤ ሥራ ጀምራ ዛሬ ከግማሽ ሚሊዮን (500,000) ብር በላይ፣ እንዲሁም የተለያዩ ማምረቻ መሳሪያዎች ስለተገዙ በደንብ ሂሳብ ከተሠራ ከተጠቀሰው በላይ (ኧረ በግምት ሚሊዮን ሳይደርስ ይቀራል ብላችሁ ነው?) ካፒታል እንዳላት ተናግራለች - ወጣት ዙፋን ኢብራሂም፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ ምርቶቿን በምሥራቅ አፍሪካ እያስተዋወቀች መሆኑን ተናግራለች፡፡ በናይሮቢ - ኬንያ አስሊ 10th street እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ምርት ማሳያና መሸጫ ሱቅ መክፈቷን ገልፃለች፡፡ ዙፋን፣ በታንዛኒያም ተመሳሳይ ሱቅ ለመክፈት ሐሳብ እንዳላት ገልፃለች፡፡ ዙፋን፣ ወላጆቼ እኔን ከሙዚቃ ለመለየት ኢትዮ ስዊድሽ ሕፃናትና ወጣቶች ማረሚያና ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ቢያስገቡኝም፣ ዛሬ፣ ኢትዮ ስዊድሽ መተዳደሪያ ሆኖኛል ትላለች፡፡ ም