Posts

The Heroes and the Villains in the Sidama Liberation Struggle: Undoing the Misinformation

Ever since Bushe and Maldia, the ancestors of the Sidama nation, settled in Teelamo, the epicentre of the Sidama civilization and nation building, as they returned back from Dawa in search of better lands for cattle herding and sedentary farming, the society lived in peace and tranquillity albeit minor ethnic conflicts from neighbouring tribes for control of grazing lands. However, the situation changed drastically when the Abyssinian army invaded the southern nations immediately after the 1882 Berlin Conference of the western nations that decided to divide Africa among themselves. The Abyssinian army supplied with rifles and other modern weapons by these rival western colonizing powers, marched towards the south between the late 1880s and the beginning of the 20th century for control of the vast fertile land and other resources owned by the peoples of the free southern nations. These nations waged bitter armed struggle against the occupying forces of King Minelik during this period

በሲዳማ ዞን መልጋ ወረዳ በበልግ ወቅት የተዘሩ ሰብሎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ::

Image
በሲዳማ ዞን መልጋ ወረዳ በበልግ ወቅት የተዘሩ ሰብሎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ:: የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ታከለ አርጋው እንደገለጹት የወረዳውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በበልግ ሥራ 2 ሺህ 5 መቶ 21 ሄክታር መሬት በበቆሎ፤ በድንች እንዲሁም በተለያዩ የጓሮ አትክልቶች እንደተሸፈነ ገልጸው ለዚህ ሥራም 3 መቶ 75 ኩንታል ማዳበሪያ እንደተጠቀሙ አስረድተዋል:: ስራው ውጤታማ እንዲሆን የልማት ሠራተኞችና በየቀበሌው የተቋቋሙ የልማት ቡድኖች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ባደረጉት ርብርብ እንደሚጠቀስ መግለጻቸውን አካሉ ጥላሁን ከጅንካ ቅርንጫ ጣቢያ ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/23HamTextN304.html

በሃዋሳ ከተማ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የትራፊክ ማዕከል ግንባታ በሁለት ወር ውስጥ ተጠናቆ ስራ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 17፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃዋሳ ከተማ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ የትራፊክ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ስራ ሊጀምር ነው። በቅርቡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ክልሎች በራሳቸው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማትን በአቅራቢያቸው ከፍተው የአሽከርካሪዎች የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎት ማቅረብ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲኖር አቅጣጫ አስቀምጧል። የደቡብ ክልል ትራንስፖርት ቢሮም ይህን መሰረት በማድረግ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታውን እያካሄደ ይገኛል። ማዕከሉ አዲስ አበባ ከሚገኘውና በሀገሪቱ ብቸኛ ከሆነው የአሽከርካሪወች ማሰልጠኛ ተቋም ጋር በአደረጃጀቱና በይዘቱ ተመሳሳይ መሆኑ ነው የተገለፀው ። በ3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ማዕከል ለግንባታው 9.5 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገለት ሲሆን ፥ በሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል። ማዕከሉ በክልሉ ብቁ የሆኑ አሽከርካሪዎችን በማፍራቱ ሚናው  ከፍተኛ እንደሚሆን  ታምኗል ።

ሲዳሙ ኣፎ ጭምሮ በ25 ቋንቋዎች የትምህርት መዛግብተ ቃላት እየተዘጋጁ ነው

ሐዋሳ (ኢዜአ)፡- የትምህርትን ጥራት በየደረጃው ለማረጋገጥ መንግሥት የሚደርገውን ጥረት ለማገዝ በኢትዮጵያ 25 የብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋዎች የተጀመረው የትምህርት መዝገበ ቃላት ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የመዝገበ ቃላቱ ዓላማና አስፈላጊነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በደቡብ ክልል ደረጃ የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት የሁለት ቀናት አውደ ጥናት በሀዋሳ ከተማ ተካሄዷል፡፡ መዝገበ ቃላቱ እየተዘጋጀ ያለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ20 ዓመታት በላይ የማስተማር ልምድና ዕውቀት ባላቸው ምሁራን ከሁለት ዓመት በፊት በተቋቋመው ስፖትላይት የትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ትብብር መሆኑ ተገልጿል።  የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ አህመዲን በአውደ ጥናቱ ላይ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን በየደረጃው ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት የትምህርት መፃሕፍት ግብአት አቅርቦት አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል። በክልሉ 14 ቋንቋዎች ሳቢና ማራኪ አቀራራብ ለህጻናት አመቺ በሆነ መልኩ ከተዘጋጁት የትምህርት መጻህፍት መካከል በ10 የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች የቀረቡት በዝርዝር ታይተው ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡  በአሁኑ ወቅት የደቡብ ክልል ቋንቋዎችን ጨምሮ በሀገር ደረጃ በ25 የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እየተዘጋጁ ያሉት የትምህርት መዘገበ ቃላት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ አስተዋጾኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ብርሃኑ ቦጋለ እንዳስረዱት በኢትዮጵያ 25 ቋንቋዎች የትምህርት መዝገበ ቃላት መዘጋጀተው ለትምህርት ጥራት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ከተማሩ በኋላ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለመማር እንደሚገ

በመከላከልን መሠረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ ውጤታማ ለማድረግ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተሠራው ሥራ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ለውጥ መታዩተን የዳራ ወረዳ ጤና ፅህፈት አስታወቀ::

Image
በመከላከልን መሠረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ ውጤታማ ለማድረግ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተሠራው ሥራ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ለውጥ  መታዩተን የዳራ ወረዳ ጤና ፅህፈት አስታወቀ:: የጽህፈት ቤቱ በሽታ መከላክልና ጤና ማጎልበት ኦፊሰር አቶ ማቲዎስ ማልኬ እንደተናገሩት ለጤና ኤክስቴንሽን ባሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የጤና ፓኬጁን ተግባራዊ ለማድረግ በ1 ለ5 ትሥሥር የጤና ልማት ሠራዊት በመገንባት በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል:: አቶ ማቲዎስ አክለውም ተላላፊ በሽታን ለመከላከል የኅብተተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ ጠቅሰው በክረምት ወቅት ለሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል:: የወረዳው ዘርፈ ብዙ ኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና ማስተባበር ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሙሉነህ ኪአሞ በበከኩላቸው በወረዳው የኤች አይቪ  ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር መበራከት ከታዩ  ለውጦች እንደ አብነት የሚጠቀሰ ነው ብለዋል፡፡ ሲል አዳነ አለማየሁ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/23HamTextN104.html