Posts

በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በወንዶገነትም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተነስቷል።

Image
New ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከሶስት ቀናት በፊት በሲዳማ ዞን በመልጋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ ወደ ወንዶገነትም ተዛምቶ፣ የባሻ ወረዳ ሊቀመንበር መገደሉንና የወረዳው መስተዳደር መኪና መቃጠሉን ዘጋቢያችን ገልጧል። በግጭቱም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ፣ ነገር ግን በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መቁሰላቸው ታውቋል። ሁለቱ ወረዳዎች ኩታገጠም ሲሆኑ፣ በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማሳመን ወደ ታች ወርደው በሚነጋገሩበት ጊዜ ነው ግጭቱ የተነሳው። በእነዚህ አካባቢዎች ያለው አብዛኛው ሰው በከብት ርቢ የሚተዳደር የነፍስ ወከፍ መሳሪያ የታጠቀ መሆኑ ፣ በወረዳ ባለስልጣናት እና በፖሊሶች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዳባባሰው ዘጋቢያችን አክሎ ገልጧል። መልጋ እና ወንዶገነት ወረዳዎች አሁንም በፌደራል ልዩ ሀይል ቁጥጥር ሲሆኑ፣ ዜናውን እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ ውጥረት እናደለ ዘጋቢያችን ገልጧል። በመልጋ ወረዳ ወረዳ ሰሞኑን በተነሳው ግጭት 12 የፌደራል ፖሊስ አባላትና ከ20 በላይ ሲቪሎች መቁሰላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የዞኑ ነዋሪዎች ክልል የመሆን ጥያቄያችን መልስ እስካላገኘ ድረስ ግብር አንገብርም በማለት ጠንካራ አቋም ይዘዋል። የክልሉ ምክርቤት ከትናንት በስቲያ ስብሰባ ቢያካሂድም በዞኑ ስላለው ግጭት ምንም ውሳኔ ሳያሳልፍ ተበትኖአል።

በቅርቡ በማልጋ ወረዳ በፈዴራል ፖሊስ እና በወረዳው ነዋሪዎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት ህዝብ ከፊዴራል ፖሊስ ላይየማረካቸውን የጦር ማሳሪያ ለመንግስት መመለሱን ሲዳማ ኔሽን ኦንላይን የተባለ ድረ ገጽ ዘገበ

እንደ ድረ ገጹ ዘገባ ከሆነ ጉጉማ ላይ ተከስቶ በነበረው በዚህ ግጭት ህዝቡ19 ከፈዴራል ፖ ሊስ ኣቁስሎ ከ18 በላይ የጦር መሳሪያ ላይ ማርኳል። ህዝቡ የማረከውን የጦር መሳሪያ በትናንትናው እለት ለመንግስት ተወካዮች ያስረከበ ሲሆን፤ የጦር መሳሪያዎቹን ልማርክ የቻለው  ራስን የመከላከል እርምጃ በወሰደውወቅት መሆኑን ግልጸዋል። በተያያዘ ዜና ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በበርካታ የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እየተደረጉ ናቸው ።   ለዝርዝር መረጃ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ፤ የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄ ያለ ምንም ቅድምያ ሁኔታ አፋጣኝ መልስ እንዲያሰጠው ጠየቀ

ከሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ኀብረት፡ ስለሲዳማ የወቅቱ ሁኔታን በተመለከተ  የተሰጠ መግለጫ ተንኰለኞችና ወንጃለኞች በተፈጥሮአቸው የገሙ ስለሆኔ እነሱን ያካተተ መንግሥት፡  አገርንና መንግሥትንም ጭምር ያገማል፡ ላል ሚካኤል ጋድ ስለመንግሥት ተመራማሪ።  የወያኔ አገዛዝም በኢትዮጵያ በዚህ መልክ የሚታይ ነው። ወያኔ የሕዝቦች አብሮ መኖርንና  ሰላማዊ ሕይወትን የማይቀበል ስለሆነ እንደታመሰ ለ20 ዓመታት የቆየ ሲሆን፡ ሀገራዊ ራዕይ  የሌላቸው የወንጃለኖች ጥርቃሞ ነው። የሲዳማ ፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት ይህንን ከተረዳ  የቆየ ቢሆንም አሁን የደረሰንበት ደረጃ በጣም አደገኛ እየሆነ በመምጣቱ፡ ወያኔ በአስቸኳይ  ተመንግሎ መውደቅ ያለበት መሆኑን ህብረቱ አሰምሮበታል። ድርጅታችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲዳማ በመካሄድ ላይ ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ከመረመረ  በኋላ፡ ለመላው ኢትዮጵያውያን ለማሳወቅና እንደ ስልቻ በትዕቢት የተወጠረው ወያኔ ከዚህ  ተንኰለኛ ተግባሩ ይቆጠብ ይሆን በማለት ለማሳሰብ የወጣ መግለጫ ነው። ሴራኛው ወያኔ በሲዳማ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ዛሬ ሳይሆን የአዲስ አበባን ቤተመንግሥት  ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡በዚህም በሲዳማ ውስጥ ተወልዶ ያደገውን እጅጉ  ገ/ሚካኤል የተባለውን ትግሬ በመመልመልና በመሾም የሲዳማ ታጋዮችን እነፊሣ ፍቾን  በስውር አስገድሎዋል። ቀጥሎም የተቃሚዎችን ጐራ ለማዳከም አንዳንድ ለጥቅማጥቅም  የተገዙ ግላሰቦችን በመናኛ ገንዘብና መሬት (ቤት መሥሪያ ቦታ) በመስጠትና በመደለል ወደ  ወያኔ እንድቀላቀሉ በማድረግ ትግለችን ለማኰለሸት ሞክረዋል: ግን አልተሰካላቸውም። ከዚህም ሌላ፡ በረከት ስሞን ኤርትራዊውን አማራ፡ ኩማ ደመቅሣ ትግሬውን ኦሮሞ ብለው  እንደ ሾሙው ሁሉ በሲዳማ ውስጥ ተወልደው ያደጉትን፡ 1ኛ ሽፈረው

Declaration: The Peoples’ Alliance for Freedom and Democracy

Image
New (OLF, ONLF, SLF and some candidates of AFD) July 26, 2012 (oromoliberationfront.org) - The aforementioned peoples’ alliances of Ogaden Somalis, Oromo, Sidama and the new candidates of AFD: After deliberating on the current situation in Ethiopia and carefully observing the level of struggle against the current regime and the apparent confusion created by the sudden disappearance of Meles Zenawi, the “strong man” ruling Ethiopia for the past twenty one years; Being apprehensive of the current regimes attempts to delude the peoples in Ethiopia regarding Zenawi’s fate and their attempt to maintain the status quo in order to continue their ruthless suppression of all peoples in Ethiopia; After considering, the current disarray and lack of political will of some opposition groups to embrace the political and social changes that Ethiopia has undergone in the last forty years and their archaic adherence to political precepts that are no longer tenable in the 21 century such as

የሲዳማ ፖለቲካ

ወደ ሲዳማ የባሕል አዳራሽ ሲዘልቁ በቀጭኗ መግቢያ ላይ ፊትዎን ወደ ግራና ቀኝ እንዲያማትሩ ይገደዳሉ። በስተቀኝ በኩል ብሔሩን የሚወክለው ትልቁ መሰብሰቢያ የ‹‹ሲዳማ የባሕል አዳራሽ›› በሰፊው ተንጣሎ ይመለከቱታል። ወደ ግራ አይንዎትን ሲያማትሩ በተለያየ ቅርፅ የተሰሩና ለብሔሩ ‹ማንነት›› ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን የሚታሰቡበት የተለያዩ ሐውልቶች ተሰድረው ያገኛሉ። የግቢው ድባብ የባሕል አዳራሹን ከማየት ይልቅ ጀግኖቹን ወደመመልከቱ እንዲያጋድሉ ያስገድዳል። እናም ወደ ሐውልቶቹ ተጠግተው ፊትዎን ቀና አድርገው ሲመለከቱ ጀግኖቹ ፊታቸው ኮስተርተር ብሎ የሲዳማን ባሕላዊ ልብስና የክብር መለያ ለብሰው፤ አንዳንዶቹ በፈረስ ላይ፣ አንዳንዶቹ ቀጥ ብለው ቆመው፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያቸውን ታቅፈው ይመለከታሉ። እነዚህን ጀግኖች ፊታቸው ላይ ያለውን ግርማ ሞገስ ብቻ መመልከቱ አያጠግብም። ምን ቢሰሩ ነው? የሚለው ጥያቄም አእምሮን ማጫሩ አይቀርም። ከታች በእምነበረድ ላይ በተቀረፀ ጽሁፍ ጀግኖቹ ከማን ጋር ለምን አላማ እንደተዋጉ ተፅፎ ይገኛል። ከሐውልቱ ስር ተቀርፆ የተቀመጠው ፅሁፍ የመንግስትን አቋም የሚያንፀባርቅ ነው የሚል እምነት አለኝ። መንግስት ጀግኖቹ የሰሩትን ገድል እውቅና የሰጠ ብቻም ሳይሆን ተተኪዎቹ የሲዳማ ተወላጅ ህፃናት ይህንን ታሪክ እየሰሙ አርአያ እንዲሆኗቸውም ጭምር ለማስተማሪያ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ትውልዱ ታሪክን መገረብ ብቻ ሳይሆን ‹‹ጠላቶቹ›› እነ ማን እንደሆኑ እግረ መንገዱን ያጠናም ዘንድ በሰፊው ተፅፎለታል- በሲዳማ የባህል አዳራሽ። ሐውልቱ ስር የተቀረፀውን ፅሁፍ በአንድ ወገን እንደ መንግስት አቋም ተቀብለን፣ በሌላ ወገን የብሔሩ ተወላጅ ምሁራን የፃፏቸውን አስረጂ ፅሁፎች ይዘን፤ ሲዳማዎች ስለራሳቸው እና ስለተቀረው የአገሪ