የሲዳማ ፖለቲካ
ወደ ሲዳማ የባሕል አዳራሽ ሲዘልቁ በቀጭኗ መግቢያ ላይ ፊትዎን ወደ ግራና ቀኝ እንዲያማትሩ ይገደዳሉ። በስተቀኝ በኩል ብሔሩን የሚወክለው ትልቁ መሰብሰቢያ የ‹‹ሲዳማ የባሕል አዳራሽ›› በሰፊው ተንጣሎ ይመለከቱታል። ወደ ግራ አይንዎትን ሲያማትሩ በተለያየ ቅርፅ የተሰሩና ለብሔሩ ‹ማንነት›› ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን የሚታሰቡበት የተለያዩ ሐውልቶች ተሰድረው ያገኛሉ። የግቢው ድባብ የባሕል አዳራሹን ከማየት ይልቅ ጀግኖቹን ወደመመልከቱ እንዲያጋድሉ ያስገድዳል። እናም ወደ ሐውልቶቹ ተጠግተው ፊትዎን ቀና አድርገው ሲመለከቱ ጀግኖቹ ፊታቸው ኮስተርተር ብሎ የሲዳማን ባሕላዊ ልብስና የክብር መለያ ለብሰው፤ አንዳንዶቹ በፈረስ ላይ፣ አንዳንዶቹ ቀጥ ብለው ቆመው፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያቸውን ታቅፈው ይመለከታሉ። እነዚህን ጀግኖች ፊታቸው ላይ ያለውን ግርማ ሞገስ ብቻ መመልከቱ አያጠግብም። ምን ቢሰሩ ነው? የሚለው ጥያቄም አእምሮን ማጫሩ አይቀርም። ከታች በእምነበረድ ላይ በተቀረፀ ጽሁፍ ጀግኖቹ ከማን ጋር ለምን አላማ እንደተዋጉ ተፅፎ ይገኛል። ከሐውልቱ ስር ተቀርፆ የተቀመጠው ፅሁፍ የመንግስትን አቋም የሚያንፀባርቅ ነው የሚል እምነት አለኝ። መንግስት ጀግኖቹ የሰሩትን ገድል እውቅና የሰጠ ብቻም ሳይሆን ተተኪዎቹ የሲዳማ ተወላጅ ህፃናት ይህንን ታሪክ እየሰሙ አርአያ እንዲሆኗቸውም ጭምር ለማስተማሪያ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ትውልዱ ታሪክን መገረብ ብቻ ሳይሆን ‹‹ጠላቶቹ›› እነ ማን እንደሆኑ እግረ መንገዱን ያጠናም ዘንድ በሰፊው ተፅፎለታል- በሲዳማ የባህል አዳራሽ። ሐውልቱ ስር የተቀረፀውን ፅሁፍ በአንድ ወገን እንደ መንግስት አቋም ተቀብለን፣ በሌላ ወገን የብሔሩ ተወላጅ ምሁራን የፃፏቸውን አስረጂ ፅሁፎች ይዘን፤ ሲዳማዎች ስለራሳቸው እና ስለተቀረው የአገሪ