Posts

የቡና ኤክስፖርት እንቅፋት ገጥሞታል

የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኢንተርፕራይዝ በሚያካሂደው የመልቲ ሞዳል አሠራር ምክንያት በተፈጠረው ችግር፣ ባለፉት ሁለት ሳምንት ቡና ወደ ውጭ መላክ እንዳላስቻለ ምንጮች ገለጹ፡፡ በ2004 ዓ.ም ዓመት በቡና ንግድ ላይ የተፈጠረው ችግር በአዲሱ በጀት ዓመትም ሊደገም ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡   የመልቲ ሞዳል አሠራርን ተግባራዊ ያደረገው ኢንተርፕራይዝ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይም መስተጓጎል እየተፈጠረ መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡   በ2003 ዓ.ም. ወደ ውጭ የተላከው የቡና መጠን 197 ሺሕ ቶን ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም. በአገሪቱ ከፍተኛ የቡና ምርት ቢኖርም ከታቀደው 270 ሺሕ ቶን ውስጥ የተላከው 170 ሺሕ ቶን ብቻ ነው፡፡   ይህ ሊሆን የቻለው ንግድ ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ጊዜያት የቡና ንግድን በሚመላከት ባወጣቸው መመርያዎች ምክንያት ነው ሲሉ፣ የቡና ነጋዴዎች ጣታቸውን በሚኒስቴሩ ላይ ይቀስራሉ፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ የቡና ነጋዴዎች በውጭ ደንበኞቻቸው ዕምነት እየታጠባቸው መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡   “ውል በገባነው መሠረት ቡና ማቅረብ ተስኖን ዓመቱን አጠናቀናል፤” ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የቡና ኤክስፖርተር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡   የተፈጠሩት ችግሮች የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥራቱና በጣዕሙ ቢታወቅም፣ በዋጋ ከሁሉም አገር ቡናዎች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንዲገኝ አድርጎታል፡፡   ችግሮቹን ከፈጠሩት መካከል ቡና በኮንቴይነር ይላክ መባሉና በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል የሚወጣው ጨረታ የፈጠረው የአላላክ ዘዴ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የቡና ላኪዎች ማኅበርና ታዋቂ የቡና ላኪዎች ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በ

ከሃዋሳ ወጥቶ የነበረው የፈዴራል ሃይል ተመልሶ ገባ፤ከየወረዳዎች የተወጣጡ የኣገር ሽማግሌዎች የክልል ጥያቄን በተመለከተ ከዞኑ ኣስተዳዳሪ ጋር ያደረጉት ውይይት ያለ ውጤት ተጠናቀቀ ቀጣይ ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት ለማደረግ ታቅዷል

Image
ካለፈው ወር ጅምሮ የሲዳማ የክልል ጥያቄ በተመለከተ የተቀጣጠለውን  ህዝባዊ ንቅናቄን ለመቆጣጠር የሃዋሳን ከተማ ጨምሮ በኣንዳንድ የሲዳማ ወረዳዎች ሰፍሮ የነበረው የፊዴራል ሃይል ባለፉት ሳምንታት መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ ሲዳማ  ተመልሷል። የፈዴራል ሃይሉ ወደ ሲዳማ መመለስን በተመለከተ የተለያዩ ኣስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን ህዝባዊ ንቅናቄው  በተለይ በወረዳዎች ተቀጣጥሎ  በመቀጠሉ ለሃይሉ መመለስ ምክንያት ሳይሆን ኣይቀርም ተብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዞኑ ወረዳዎች የተወጣጡ ሽማግሌዎችን ያካተተ ኣንድ የሲዳማ ልኡካን ቡድን በትናንትናው እለት ከዞኑ ኣመራር ጋር የክልል ጥያቄን በተመለከተ የተወያይ ሲሆን ስብሳባው ያለ በቂ ውጤት ተጠናቋል። የሲዳማ  ሽማግሌዎች ህገ መንግስቱ በምፈቅደው መሰረት የክልል ጥያቄ በሲዳማ ዞን ምክር ቤት ኣባለት እንዲቀርብ ጥያቄ  ያቀረቡ ሲሆን፤ በካላ ሚሊዮን ማትዎስ የተመራው የዞን ካቢኔ የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ሳይቀበል ቀርቷል። ካላ ሚሊዮን በስብሰባው ላይ የክልል ጥያቄ ከዚህ በፊት ተነስቶ የነበረ ነገር ግን በልማት ጥያቄ የተተካ በመሆኑ መልሶ ማንሳት ኣያስፈልግ የምል ኣቋም ኣንጸባርቀዋል። በመረጧቸው እና በገዛ ልጆቻቸው ምላሽ ያልተደሰቱት ሽማግሌዎቹ የስልጣን እርከኑን ተከትለው ከላይ ካሉት ባለስልጣናት ጋር  ለመነጋገር ለሚቀጥለው ሳምንት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል።

The official inauguration ceremony of WaDF and fund raising event held on Saturday, 21 July 2012 in Hawassa city

Image
Woldeamanuel Dubale Foundation(WaDF) Among the notable customs and values of Sidama nation, one can mention the rule of truth (Halaale), the government of the elders, dialogical and consensus based method of problem solving, and the fear of God (Magano). Apart from being liable to burden of excise tax and forced labor, Sidama people were obliged to abandon the long standing social, and political authority systems, which include woma, mote, and the luwa systems. The people through its leaders resisted  the inhuman actions and maltreatments of previous governments. During the Era of Menelik II and thereafter Sidama Compatriots fought against the regimes , in time and space, in an unorganized and organized manners.  As an organized resistance, Sidama Liberation Movement (SLM) waged an armed struggle, against the military regime for more than 10 years between 1978 -1990 and fully liberated 3 high land districts of Arbegona, Bensa and Aroressa in the South Eastern Sidama land fro

The Murder of Mathewos Korsisa and his Nephews

Image
It is often argued that the socialist regime of the military junta that took power after the 1974 revolution in Ethiopia was not exclusively an Abyssinian (Tigre and Amhara) dominated administration. On the basis of such argument is to be found the occasional participation of few, handpicked surrogates who were ready to serve their Abyssinian masters at the expense of their own peoples.  In this regard, there were a number of notorious non Abyssinian cadres of the socialist government who tortured, maimed and even killed their own people to obtain favours from their Abyssinian masters. Ali Musa of the then Bale province in the present Oromia region, and Pertros Gebre of the then southern Shewa province are indicative cases in this regard. These individuals were indeed some of the most brutal and the most feared non Abyssinian cadres of the socialist government of the time.  Although such surrogates were encouraged by the Abyssinian socialist dictators to kill and maim their own

ሲዳማን ጨምሮ በዲላ ከተማ ከሶስት ዞን ለተውጣጡ የዓይን ህሙማን የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው

ዲላ ሃምሌ 11/2004በጌዴኦ ሲዳማና ቦረና ዞኖች በአይን ሞራ ግርዶሽና ትራኮማ ለተጎዱ ወገኖች የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ሀንሴሻ ተራድኦ ልማት ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ገለጸ። የድርጅቱ ስራ አሰኪያጅ አቶ ታደሰ አላኮ በዲላ ከተማ ከሶስቱ ዞኖች ለተውጣጡ የዓይን ህሙማን የህክምና አገልግሎት በተሰጠበት ወቅት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የአይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ህሙማን በመለየት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። ባለፉት ስድስት ዓመታት በአይን ህክምናው በተለይ በዓይን ሞራ ግርዶሽና በትራኮማ የተያዙ ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች ህክምና ማግኘታቸውን ገልጸዋል። ድርጅቱ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናን በዝዋይና ቡታጅራ በሚገኙ የህክምና ማእከላት እንደሚሰጥ ገልጸው የትራኮማ ቀዶ ህክምናና ሌሎች ቀላል ህክምናዎችን በዲላ ሆስፒታል እየሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል። ማየት ተስኗቸው በቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ 20 ልጆችን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የብሬል ስልጠና በመስጠት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረጉን አቶ ታደሰ ገልጸዋል። በጌዴኦ ዞን የዲላ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አቶ አለማየሁ ገመዴ ሁለት ልጆቻቸው በአይን ሞራ ግርዶሽ ማየት ተስኗቸው እንደነበር አስታውሰው ባለፈው ዓመት በተደረገላቸው ቀዶ ሕክምና ሙሉ ለሙሉ ለማየት መቻላቸውን ተናግረዋል። በድርጅቱ አጋዠነት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙት ተማሪዎች መካከል ተማሪ ጥላሁን ተፈራና ሁሴን መሃመድ ከዚህ ቀደም ድጋፍ የትምህርት እድል ሳያገኙ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን ባገኙት ድጋፍ ሶስተኛ ክፍል መድረስ መቻላቸውን ተናግረዋል።