Posts

የሲዳማ ኣመራሮች በቅርቡ በሚከበሩት የሲዳማ ቋንቋ ስምፖዚዬ እና የዘመን መለዎጫ ፊቼ በኣላት ኣከባበር ዙሪያ ተፋጠዋል፤ሁለቱም በኣላት ከሃዋሳ ከተማ ውጪ እንዲከበሩ ሳይደረግ ኣይቀርም እየተባለ ነው

የውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትወርክ እንደተነገሩት፤ ባለፈው ሳምንት መገባዳጃ ላይ በክልሉ ፕሬዚዳንት ሰብሳቢነት በበኣላቱ ኣከባበር ዙሪያ ላይ በመከረው ዝግ ስብሰባ የተለያዩ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል። የዞኑ ኣስተዳዳሪን እና የከተማዋ ከንቲባ በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሁለቱም የሲዳማ ህዝብ በኣላት ከሃዋሳ ከተማ ውጪ በወረዳዎች እንዲከበሩ የሚል ሀሳብ ያነሱ ሲሆን፤ ለዚህም የጸጥታ ጉዳይን እንደምክንያትነት ኣንስተዋል። በኣላቱ በሃዋሳ ከተማ ውስጥ እንዳይከበሩ ማድረግ በቅርቡ ከከተማዋ ኣስተዳደር ጋር በተያያዘ ተነስቶ ለነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ መባባስ ምክንያት ይሆናል በሚል ኣንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች የፕሬዚዳንቱን ሀሳብ የተቃዎሙ ሲሆን፤እንደኣማራጭም የከተማዋን ጸጥታ ሁኔታ ኣጠናክረው በኣላቱ ሃዋሳ እንዲከበሩ መደረግ ኣለበት ብለዋል። ኣንዳንድ የሲዳማ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበሩትን እነዚህን በኣላት ከሃዋሳ ከተማ እንዳይከበሩ መከልከልም ሆነ መፍቀድ ለህዝባዊው ንቅናቄ የራሳቸው የሆነ ኣዎንታዊ ገጽታ ኣላቸው። በኣላቱ ከሃዋሳ ከተማ እንዲከበሩ ከተፈቀደ በኣላቱን ለማክበር የሚሰባሰበው ህዝብ ከሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ጋር በተያያዘ ያላቸውን ቅሬታ ለመግለጽ ኣጋጣሚ የሚፈጥር ሲሆን፤ መከልከሉ ደግሞ መንግስት ለህዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ኣለመሆኑ እንድታወቅ ያስችላል ብለዋል።

በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ በርካታ የኣመራር የስራ መደቦች ላላፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ክፍት ሆነው መቆየታቸው በከተማዋ ለሚካሄዱት ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎች ማነቆ መሆናቸውን ኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፤የኣመራር ስራ መደቦችቹ ለረዥም ጊዜያት ክፍት ሆነው መቆየታቸው መንግስት የከተማዋን ኣስተዳደር ከሲዳማ ለመንጠቅ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር ሳይያያዝ ኣቀርም የሚል ጥርጣሬ ፈጥሯል

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎችና ሰራተኞች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ የከተማው ኣስተዳደር ምክትል ከንትባና ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ የስራ መደብን ጨምሮ በማዘጋጃ እና በስምንቱም ክፍለ ከተማዎች ቢያንስ ኣራት ኣራት የኣመራር የስራ መደቦች ላላፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ሰው ኣልተመደበባቸውም። የእነዚህ  መደቦች የእለትተእለት ስራዎች በተወከሉ ሰዎች በመከሄድ ላይ ያሉ ሲሆን፤ ሰው ካልተመደበባቸው መደቦች መካከል የከተማዋ የመንግስት ኮሚኒኬሽን፤ የማዘጋጃ ቤቱ ምክትል ኣስተዳዳር መደብ፤ ግቢይትና ህብረት ስራ መምሪያ እና የፍትህ መምሪያ ይገኙበታል። በየስራ መደቦቹ ላይ ከዚህ በፊት ተመድበው ይሰሩ የነበሩ ግለሰቦች በተለያዩ ምክንያቶች ስራ የለቀቁ ወይም እንዲለቁ የተደረጉ መሆኑ ሲገለጽ፤ መደቦቹ ለረዥም ጊዚያት ክፍት መሆናቸው በከተማዋ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች ኣፈጻጸም ላይ ችግር መፈጠራቸው ተገልጿል። እንደኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ኣስተያየት ከሆነ መንግስት የከተማዋን ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ለማውጣት ከተማዋን ያስተዳድሩ በነበሩ የብሄሩ ተወላጆች ላይ የተለዩ ስነ ምግባራቸውን የሚያወርዱ ገጽታዎችን እየቀባ ያለ ምንም ተጨባጭ  ሲያስር ቆይቷል። ይህ ኣይነቱ የመንግስት ድርጊት የሲዳማ ኣመራሮች የማስተዳደር ኣቅም የላቸውም፤ በክራይ ስብሳብነት የተዘፈቁ ናቸው የምል ግንዛቤ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ለማስያዝና ኣመራሩን በሌላ ኣመራር ለመተካት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ  ሳይሆን ኣይቀርም ተብለዋል። ለዚህም ማሳያነት በቁልፍ የኣመራር መደቦች ላይ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል መሬት በመቸብቸብ እና በሌሎች ወንጀሎች ተወንጅለው ላለፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ታስረው

ማኑ ጎባስራ ሻራማ

Image
ከሬሆ ማንቶ ዛላቃሽ ኣዲንታን ካሬሆ ይኖሞ ሲዳሙ ቆቆው ሃዋሲ ሲዳሙ ቆቆዎ እካታ ማይራላ ዎሎቱ ሂናሱ ዳንቺሌ ቁቱዋ ሄሬና ኮባላ ዛላቁራ ባሲ ዲጮማኖ ቅሽሪሮ ዋሲ ዲኖሴ ጎሎንሁ ዳላሲ ያናቴ ቃኤክራ ቃፊ ሳትላፌ ሳትላፌ። ዳጉራው ዳጉራው ሲዴ ሎጶ ያን ጋራማዎ ሻራማዎ ... annitine maccishe

ሲዳማ ሱስተናንሴ(Sidama Sustenance) የተባለ በሲዳማ ለምግብነት በጥቅም ላይ በሚውለው በዌሴ ላይ የተጻፈ ኣዲስ መጽህፍ ገበያ ላይ ዋለ።

Image
በዶና ሲያን የተጻፈ ይህንን መጽህፍ በሲዳማና ሲዳማን በተመለከቱ ጉዳዮች ትንተና ይጀምር እና ስለ ዌሴ ተክል ሳይንሳዊ ኣመጣጥ ይተርካል፤ ከዛም ስለ ዌሴ ኣተካከል ከችግኝ ማለትም ከፉንታ ኣቆራረጥ እስከ ኣፋፋቅ ያትታል። በመጨረሻም ከዌሴ ምርቶች የተለያዩ የምግብ ኣይነቶች ኣዘገጃጀት ላይ ስፊ ማብራሪያ  ይሰጣል። መጽሀፉ እያንዳንዱን ማብራሪያ በፎቶ  ኣስደግፎ የሚስጥ ሲሆ ን ኣቀራረቡ ማንም ሰው በሚረዳ መልኩ ነው። በመጽሀፉ ውስጥ ካሉ ፎቶዎች መካከል የምከተሉት ይገኛሉ፦  ይህንን የሲዳማን ባህላዊ ምግብ ለኣለም የሚያስተዋውቀውን መጽሀፍ ገዝታችሁ ለማንበብ ኣቅም የለንም ወይም ልናገኘው ኣልቻልንም የምትሉ ካላችሁ በሚቀጥለው ሊንክ ሙሉ መጽሀፉን ኦንላይን ማንበብ ትችላላችሁ። መልካም ንባብ  Sidama Sustenance

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ190 በላይ የምርምር ስራዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛል

Image
አዋሳ ሃምሌ 10/2004 የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ከ190 በላይ የተለያዩ የምርምር ሰራዎችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አስታወቁ ። ከነዚህም ውስጥ 90 በመቶ ያህሉ በዩኒቨርስቲው አካባቢ በሚገኙ የቴክኖሎጂ ማመንጫና ማስፋፊያ ወረዳዎች ላይ መሆኑም ተገልጧል ። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው በነደፈዉ የአምስት ዓመት የምርምርና የልማት ስትራቴጂ ለአርሶ አደሩ ከፍተኛ ጠቀሜታ በሚያስገኙና ችግር ፈቺ ለሆኑ ምርምሮች ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቷል ። ዩኒቨርሲቲዉ በተለይ በምግብና በቢራ ገብስ ቴክኖሎጂ፣ በጤፍ አመራረት፣ በድንች ፣ በደጋና በወይና ደጋ የቅባት እህሎች፣ በምርጥ የቡና ዝርያ ብዜት፣ እንዲሁም በእንሰት አዘገጃጀት ቴክኖሎጂ ላይ በስፋት እየሰራ መሆኑን አስታዉቀዋል ። በእንስሳት እርባታና በተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ምርታማ የሆኑ የእንስሳት መኖ ዝርያዎችን በምርምር ጣቢያዎች በማባዛት የማስተዋወቅ፣ የተሻሻሉ የበግና የፍየል ዝርያዎችን የማዳቀል፣ ዘመናዊ የንብ ማነብ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ ስራ እያካሄደ መሆኑን ገልጠዋል ። ዉጤታማነታቸዉ በምርምር የተረጋገጡ የሳርና የዛፍ ዝርያዎችን የተፋሰስ ስራዎች በተካሄዱባቸዉ አካባቢዎች እንዲተከሉ ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል አበረታች ተግባር እያከናወነ መሆኑን ዶክተር ዮሴፍ አስታዉቀዋል ። በተጨማሪ ዩኒቨርሰቲው የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ስድስት የቴክኖሎጂ መንደሮችን በመለየት ከክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት፣ በማስተዋወቅና በማስፋፋት ላይ እንደ