Posts

ማኑ ጎባስራ ሻራማ

Image
ከሬሆ ማንቶ ዛላቃሽ ኣዲንታን ካሬሆ ይኖሞ ሲዳሙ ቆቆው ሃዋሲ ሲዳሙ ቆቆዎ እካታ ማይራላ ዎሎቱ ሂናሱ ዳንቺሌ ቁቱዋ ሄሬና ኮባላ ዛላቁራ ባሲ ዲጮማኖ ቅሽሪሮ ዋሲ ዲኖሴ ጎሎንሁ ዳላሲ ያናቴ ቃኤክራ ቃፊ ሳትላፌ ሳትላፌ። ዳጉራው ዳጉራው ሲዴ ሎጶ ያን ጋራማዎ ሻራማዎ ... annitine maccishe

ሲዳማ ሱስተናንሴ(Sidama Sustenance) የተባለ በሲዳማ ለምግብነት በጥቅም ላይ በሚውለው በዌሴ ላይ የተጻፈ ኣዲስ መጽህፍ ገበያ ላይ ዋለ።

Image
በዶና ሲያን የተጻፈ ይህንን መጽህፍ በሲዳማና ሲዳማን በተመለከቱ ጉዳዮች ትንተና ይጀምር እና ስለ ዌሴ ተክል ሳይንሳዊ ኣመጣጥ ይተርካል፤ ከዛም ስለ ዌሴ ኣተካከል ከችግኝ ማለትም ከፉንታ ኣቆራረጥ እስከ ኣፋፋቅ ያትታል። በመጨረሻም ከዌሴ ምርቶች የተለያዩ የምግብ ኣይነቶች ኣዘገጃጀት ላይ ስፊ ማብራሪያ  ይሰጣል። መጽሀፉ እያንዳንዱን ማብራሪያ በፎቶ  ኣስደግፎ የሚስጥ ሲሆ ን ኣቀራረቡ ማንም ሰው በሚረዳ መልኩ ነው። በመጽሀፉ ውስጥ ካሉ ፎቶዎች መካከል የምከተሉት ይገኛሉ፦  ይህንን የሲዳማን ባህላዊ ምግብ ለኣለም የሚያስተዋውቀውን መጽሀፍ ገዝታችሁ ለማንበብ ኣቅም የለንም ወይም ልናገኘው ኣልቻልንም የምትሉ ካላችሁ በሚቀጥለው ሊንክ ሙሉ መጽሀፉን ኦንላይን ማንበብ ትችላላችሁ። መልካም ንባብ  Sidama Sustenance

የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ190 በላይ የምርምር ስራዎችን በማካሄድ ላይ ይገኛል

Image
አዋሳ ሃምሌ 10/2004 የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ከ190 በላይ የተለያዩ የምርምር ሰራዎችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አስታወቁ ። ከነዚህም ውስጥ 90 በመቶ ያህሉ በዩኒቨርስቲው አካባቢ በሚገኙ የቴክኖሎጂ ማመንጫና ማስፋፊያ ወረዳዎች ላይ መሆኑም ተገልጧል ። የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው በነደፈዉ የአምስት ዓመት የምርምርና የልማት ስትራቴጂ ለአርሶ አደሩ ከፍተኛ ጠቀሜታ በሚያስገኙና ችግር ፈቺ ለሆኑ ምርምሮች ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቷል ። ዩኒቨርሲቲዉ በተለይ በምግብና በቢራ ገብስ ቴክኖሎጂ፣ በጤፍ አመራረት፣ በድንች ፣ በደጋና በወይና ደጋ የቅባት እህሎች፣ በምርጥ የቡና ዝርያ ብዜት፣ እንዲሁም በእንሰት አዘገጃጀት ቴክኖሎጂ ላይ በስፋት እየሰራ መሆኑን አስታዉቀዋል ። በእንስሳት እርባታና በተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር ምርታማ የሆኑ የእንስሳት መኖ ዝርያዎችን በምርምር ጣቢያዎች በማባዛት የማስተዋወቅ፣ የተሻሻሉ የበግና የፍየል ዝርያዎችን የማዳቀል፣ ዘመናዊ የንብ ማነብ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ ስራ እያካሄደ መሆኑን ገልጠዋል ። ዉጤታማነታቸዉ በምርምር የተረጋገጡ የሳርና የዛፍ ዝርያዎችን የተፋሰስ ስራዎች በተካሄዱባቸዉ አካባቢዎች እንዲተከሉ ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል አበረታች ተግባር እያከናወነ መሆኑን ዶክተር ዮሴፍ አስታዉቀዋል ። በተጨማሪ ዩኒቨርሰቲው የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ስድስት የቴክኖሎጂ መንደሮችን በመለየት ከክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት፣ በማስተዋወቅና በማስፋፋት ላይ እንደ

በሀዋሳ ከተማ ከ40ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ተጀመረ፡፡

Image
ሃዋሳ ሃምሌ 9/2004 በሀዋሳ ከተማ ከ40ሺህ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ፡፡ የወጣቶችን የስራ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንዲጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፕሮግራሙ መጀመር ምክንያት በማድረግ በሀዋሳ መስቀል አደባባይ ዛሬ በተዘጋጀው የትውውቅ ስብሰባና የቸግኝ ተከላ ስነ ስርዓት ላይ የከተማው ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት መልካሙ ጋጋዶ እንደገለጸው የከተማው ወጣቶች ባለፉት ሶስት ዓመታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደራጀ መንገድ ተሳታፊና ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶቹ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ለአካባቢው ልማትና ደህንነት በነፃ ያበረከቱበት በሂደትም ሌሎችን በመርዳት ከማህበረሰቡ የተለያየ እውቀት የቀስሙበት የተግባር መሳሪያ ነው ብሏል፡፡ በዘንድሮም ክረምት ከከተማው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ከወጣት አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር እራሳቸውንና ህብረተሰቡን ጠቅመው የከተማውን ልማት በሚያፋጥኑ የበጎ አድራጎት ተግባራት ለመሰማራት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ወጣት መልካሙ አብራርቷል ። የከተማው አስተዳደር ህፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ፣ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ስምረት ግርማ በበኩላቸው የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በከተማው ከተጀመረ ወዲህ የወጣቶች ተነሳሽነትና ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡ በ2002 የክረምት ወራት በስድስት ዓይነት የበጎ ፈቃድ አገልገሎት መስኮች 9ሺህ 463 ወጣቶች ተሳታፊ የነበሩበት ሲሆን በቀጣይ አመት የስራ መስኮቹ ወደ ስምንት የተሳታፊ ወጣቶች ቁጥር ደግሞ ከ36 ሺህ በላይ በማሳደግ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል፡፡ በ

ጡማኖና ፋቂሳ ስለተባሉ የሲዳማ ነገድ ኣባቶች እና መካነ መቃብሮቻቸው ምን ያህል ያውቃሉ?

Image
  ቴላሞ የጡማኖ  መታሰቢያ የጡማኖ መካነ መቃብር እና የሃገር ሽማግሌው አቶ ሲዳሞ ቢረጋ ከለኩ ከተማ በስምንት ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኘው ቴላሞ ነው፤ ቴላሞ የሲዳማ አድባር ነው ሲሉ የሃገር ሽማግሌዎቹ ይገልጻሉ፡፡ አረንጓዴ ምድር ምን ማለት እንደሆነ በቴላሞ ቅጥር ግቢ ያሉት ሃገር በቀል ግዙፍ የዛፍ ዝርያዎች ለትውልድ የቆሙ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ መልከአ-ምድራዊ ውበቱ ይማርካል፤ ከደኑ መሃል በአጥር የተከበበ አንድ ቅጥር አለ፤ በዚህ ቅጥር ውስጥ የሲዳማ ነገድ አባት የሆነው የጡማኖ መቃብር ይገኛል፡፡ በስፍራው በየእጽዋቱ ስር የአረብኛ ጽሁፍ ያለባቸው ድንጋዮች ይገኛሉ፤ እንደ አካባቢው ሽማግሌዎች ገለጻ እነዚህ የአረብኛ ጽሁፍ ያለባቸው ድንጋዮች መቃብሮች ናቸው፡፡ ሲዳሞ ቢራጋ የሃገር ሽማግሌ ናቸው፤ በየግዜው ለተለያየ ጉዳይ ወደ ቴላሞ ይመጣሉ፤ ይህንን ስናጠናቅር በስፍራው ያገኘናቸውም ለተመሳሳይ ዓላማ በቴላሞ ውብ ቅጥር ግቢ ለውይይት አረፍ እንዳሉ ነው፡፡ የሲዳማ የሃገር ሽማግሌዎች የሚለብሱትን ባህላዊ አለባበስ የለበሱት አቶ ሲዳሞ ቢራጋ ስፍራውን በሚመለከት አንዳንድ ጥያቄዎችን ስናቀርብላቸው በማራኪ አተራረክ ለዛ መልሰውልናል…መነሻችን ደግሞ ቴላሞ ምንድን ነው የሚል ነበር አቶ ሲዳሞ በተረጋጋ ሁኔታ ረጃጅም የቅጥሩ ዛፎች ላይ አይናቸውን ተክለው አብራሩልን….   ይሄ ቦታ ቴላሞ ይባላል፤ ጡማኖ የሲዳማ አባት ነው፤ እዚህ ነው የተቀበረው፤ ቦታው ብዙ ዓመቱ ነው….ማን ይቆጥረዋል ብዙ ነው፤ እዚህ የወለደ ሰው አሁን አስራ ስድስት ትውልድ ሆኗል፡፡ የቅጥሩን ዙሪያ ገባ በዓይናቸው ቃኘት አድርገው መልሰው ወደ ሽማግሌዎቹ በመመልከት የቴላሞን አካባቢ ሁለንተናዊ እሴት በወፍ በረር መተረኩን ቀጥለዋል….. በዓመት በዓመት ኮርማ ይገባል…