ለመሆኑ ደኢህዴን የምር ኪራይ ሰብሳቢነትን መዋጋትና የማድረቅ ፍላጎት አለው ወይስ በሙስና ስም የሲዳማ ብሔር ተወላጆችን ለይቶ መምታት ነው ኣላማው ? ለመሆኑ የኪራይ ሰብሳቢዎችስ ማዕከል የት ነው? እስከ አሁን በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ የተወሰዱ ተጨባጭ እርምጃዎች ምንድናቸው?
ሳይገባን ቀርቶ አይደለም የህዝብን ደም የመጠጠ ባለስልጣን ሆኖ ሀዋሳ ከተማን ከሲዳማ እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት ሲዳማን የሚያፈንቅልላቸቸው ከሆነ ከሙስና የፀዳ የስርአቱ አርበኛ ተደርጎ መቆጠሩ አይደንቅም፡፡ በአጠቃላይ ለደኢህዴን ሙስናን መዋጋት ማለት በወረዳ ህዝብን የበዘበዘ የህዝብ ጩሄት ሲበዛ በዞን ላይ መሾም፤ የዞኑን በክልል፤ የክልሉን ወደ ፈዴራል አዛውሮ መሾም መሆኑ ከማንም ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም፡፡ በዚህ አይነት ከደቡብ ዞኖች ወደ ክልልና ወደ ፈዴራል ተሸጋሽገው ለስልጣን ሽልማት የበቁት ባለስልጣናትና ለሹመት ሽልማት ያበቃቸውን ስራ ለግንዘቤ እንዲረዳ ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ 1 የደኢህዴን መጨረሻ ስልጣን ደረጃ ላይ የተቀመጡ በአሁኑ ጊዜ በፌዴራል የተሾሙ ባለስልጣናት በልዩ ትዕዛዝ ከሊዝ ደንብና መመሪያ ውጪ ለራሳቸው 425 ካ/ሜ በተጨማሪ ማስፋፊያ ሳይጠይቁ 250 ካ/ሜ ጨምረው በህገ ወጥ መንገድ የያዙት መሬት ከሙስና የጸዳ ይባል ይሆን? 2 እኚው ባለስልጣን ለጓደኞቹና ለብሔሩ ተወላጆች በተመሳሳይ ትዕዛዝና መንገድ ለኢንቨስትመንት የተሸነሸነውን መሬት ወደ መኖሪያ ቦታነት አስቀይረው ለእያንዳንዳቸው 500 ካ/ሜ ያሰጡበትና የመሬት አገልግሎት አጠቃቀም እንዲዛባ ማድረጉ ምን ያስጠይቃል ጃል? ያሸልማል እንጂ፡፡ 3 ለደቡብ ፖሊስ ባንድ መሣሪያ ግዥ ምክንያት 5000,000 ብር የተመዘበረና በተጨባጭ ተደርሶበት ክስ ተጀምሮ ሳለ በልዩ ትዕዛዝ የታፈነ፤ ይባስ ብሎ ይህን ምዝበራ የፈፀመውን ኮሚሽነር መልሶ በመሾም ይህን አድራጎት የታገሉ የፖሊስ አባላት ብላቴ ተወስደው በእኚ ባለስልጣን በበቀል እንዲባረሩ መደረጉ ሽልማት ቢያሰጥ ለምን ይገርማል፡፡ 24 ይህ ኮሚሽነር በዳቶ ኦዳሄ ቀበሌ አርሶ አደሮችን በማፈናቀል 1000 ካ/ሜ