በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ የሚገኙ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተሸለሙ
በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ የሚገኙ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተሸለሙ::አርሶ አደሮቹ ለሽልማት የበቁት በተጠናቀቀው የበጅ ዓመት በቡና ተክል፤ ሰብል ምርት እንዲሁም በእንስሳት እርባታና በባህላዊና ዘመናዊ መስኖ አጠቃቀም ረገድ የላቀ ውጤት በማስመዝገባቸውና መነሻ ካፒታላቸውም ከ5 መቶ ሺህ እሰክ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ማፍራት በመቻላቸው ነው:: የወረዳው የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሌጣ ለገሰ ሽልማቱ ምርትና ምርታማነትን ከፍ ከማድረግ በተጨማሪ የማስፋት ስትራቴጂን አጠናክሮ በማስቀጠል የውድድር መንፈስን ማዳበር እነንዲያስችል አስረድተዋል:: የሸበዲኖ ወረዳ ደኢህዴን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ታፈሰ በበኩላቸው የተዘጋጀውን ሽልማት ካበረከቱ በኋላ እንዳሉት ያገኙትን ውጤት በማስጠበቅ በሚቀጥሉት ጊዜያትም የበለጠ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል:: የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሽልማት ስነ ስርዓት 99 ግንባር ቀደም አርሶ አደሮችና 38 የግብርና ባለሙያዎች እንደተሸለሙ ከወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል:: http://www.smm.gov.et/_Text/04HamTextN604.html