Posts

ወልደ ኣማኑኤል ሃውልት ኣካባቢ ቆሞ ታክሲ እንኳን መያዝ ተከልክሏል፤በኣላሙ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ የሰፈሩት ወታደሮች የኣከባቢውን ነዋሪ እያሳቀቁ ናቸው ተባለ።

Image
ባለፈው እሁድ ማታ ወልደ ኣማኑኤል ዱባሌ ሃውልት ኣካባቢ ሰዎች በፈዴራል ፖሊስ ከተበደቡ ወዲህ በሃውልቱ ኣካባቢ  ሌላ ግጭት ይነሳል በሚል ታክሲ እንኳን ቆሞ መጠበቅ መከልከሉ ተነግሯል። እሁድ ማታ ላይ በተከሰተው ግጭት ወደ 150 የሚሆኑ ሰዎች በወቅቱ በፈዴራል ፖሊስ ታሰረው በዛውኑ ሌሊት የተፈቱ ቢሆንም እስከተፈቱበት ሰኣት ማለትም እስከ ከሌሊቱ ሰባት ስኣት ደረስ ክፍተኛ ድብደባ እንደተከሄደባቸው ተናግረዋል።  ከዚህ ጋር በተያያዘ በኣላሙ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ጊዚያዊነት የሰፈረው ወታደር በኣከባቢው ከፍተኛ ጥበቃ በማድረግ ላይ ያለ ሲሆን፤ የኣከባቢውን ነዋሪ በማሳቀቅ በእለትተእለት ኑሮዎ ላይ ችግር እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ በመግለጽ ላይ ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ ኣስተዳዳሪ ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ በሲዳማ የክልል ጥያቄ ዙሪያ ባናጋረበት ወቅት የሲዳማን የክልል ጥያቄ ደግፈው የተናገሩ ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች የስልክ የማስፈራሪያ መልእክት እየደረሳቸው መሆኑን በመናገር ላይ ናቸው። 

The Sidama People Press ahead with their Demand for Regional Self Administration.

Press Release By United Sidama Parties for Freedom and Justice (USPFJ), June 30, 2012 After overthrowing the military regime on May 28, 1991, EPRDF adopted Proclamation No.7/1992 (http://www.forumfed.org/pubs/occasional_papers/OCP5.pdf) ‘[page6]’ that sought to devolve state power to territorially based ethno-linguistic groups with the aim of “ensuring” the right of nations, nationalities and peoples to self-determination and “ensure” the preservation of their language, culture and histories. The Proclamation established fourteen national/regional self-governments and identified the ethnic communities inhabiting each of the regions, with the exception of that of the capital city, Addis Ababa. The five of the fourteen national/regional self-governments included regions 7, 8, 9, 10 and 11 comprising about 56 nations and nationalities that inhabit Southern Ethiopia today. The legislation vested these national/regional self-governments with legislative, executive and judicial pow

ሰበር ዜና በአዋሳ በተነሳ ግጭት 1 ሰው ተገደለ 2 ሰው ቆሰለ

Image
ኢሳት ዜና:-ባለፉት 2 ሰማንታት በአዋሳ የነበረው ውጥረት እየተባባሰ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ትናንት ማታ በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል በተነሳ ግጭት 1 ሰው ሲገደል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል። ግጭቱ የተነሳው በአዋሳ ከተማ ወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ አካባቢ የተካሄደውን የሰርግ ስነስርአት ተከትሎ ነው። የሲዳማ ወጣቶች በሲዳምኛ እየጨፈሩ ሙሽሮችን ለመቀበል ሲሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተውባቸዋል። በፖሊሶች ድርጊት የተበሳጩት የከተማዋ ነዋሪዎችም በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ድንጋዮችን በመወርውር ተቃውመዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላትም ተቃውሞን ለመበትን በርካታ ጥይቶችን ሲተኩሱ አድረዋል። በዛሬው እለትም በአንዳንድ አካባቢዎች የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር። ከባድ መሳሪያዎችን የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን አጨናንቀው መዋላቻውን፣ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና በማንኛው ጊዜ የከፋ ግጭት ሊነሳ እንደሚችል በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣  የግብርና ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የክልሉ ፖሊስ ተወካዮች፣ የምክር ቤት አባላትና  እና ሌሎችም ከ 300 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ባለፈው ቅዳሜ በአዋሳ ከተማ በህቡእ ተሰባስበው የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ የሚል ድርጅት መመስረታቸውን መግለጣችን ይታወሳል። ______________________

የትናንትናውን የሃዋሳ ከተማ ግዲያን ተከትሎ የተለያዩ ኣስተያዬቶች በማህበራዊ መረቦች እየቀረቡ ነው

የትናንትናውን የሃዋሳ ከተማ ግዲያን ተከትሎ የተለያዩ ኣስተያዬቶች በማህበራዊ መረቦች  እየቀረቡ ነው። ከቀረቡት ኣስተያዬቶች መካከል ለኣብነት ያህል የሚከተለውን ይመልከቱ። Meles Zenawi's killing squad- instructed by the puppet Southern regional president Shiferaw Shuguxe (remote controlled by the current Minister for foreign affairs-Hailemariam Desalegn-who was the main culprit of the May 24, 2002 massacre of the 100s of Sidama civilians at Loqqe village--- ultimately masterminded by Meles Zenawi himself) once again started slaughtering Sidama people in their own soil in attempt of silensing their peaceful and no-violent quest for regional Self Adminstration. The Sidama people claimed nothing else other than this!! The Sidama people never stop this quest until it's 100% addressed Constitutionally without further delay. The Sidama people never give up their quest and never give in into intimidation and killings. The Sidama people's quest peacefully and non-violently continues! This must be clear to those who share their stances or o

ፈዴራል ፖሊስ በሃዋሳ ከተማ ወልደ ኣማኑኤል ጎዳና ላይ ሰላማዊ ሰዎችን ስደበድብ ኣመሽ

በዛሬ ቀን በሃዋሳ ከተማ በተለምዶ ወልደ ኣማኑኤል ሃውልት ኣካባቢ ካለው ኣንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በጊዜያዊ ካምፒነት ተከራይተው የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ ኣባላት በኣካባቢው በመንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩትን  የሲዳማን ተማሪዎች በመደብደባቸው የኣካባቢው ነዋሪዎች ድርጊቱን በመቃዎወም ተቃውሞኣቸውን ድንጋይ በመወርወር ስገልጹ ማምሸታቸው ተገለጸ። ከኣከባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ የሲዳማ የክልል ጥያቄን ተከትለው በኣካባቢው የሰፈሩት እና በተለይ ሲዳማውን በክፉ ኣይን ስከታተሉ የነበሩት የፈደራል ፖሊስ ኣባላት ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት መንገድ ላይ የነበሩትን ተማሪዎች ደብድበው ለሆስፒታል እና ለሞት ዳርጓዋል። ከተደበደቡ ተማሪዎቹ መካከል ከዎንሾ ወረዳ የመጣ ኣብረሃም የተባለው  ተማሪ ኣንዱ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ ከተደበደበ በሃላ በኣንድ ፈዴራል ፖሊስ ተገድሏል የሚል ወሬ በመነፈስ ላይ ነው። በተጨማሪም ተማሪዎቹ ለምን ይደበደባሉ በማለት የተቃዎሙ ሰዎችም ራሳቸው በፈዴራል ፖሊስ በኣሰቃቂ ሁኔታ የተደበደቡ ሲሆን ከነዚሁ ሰዎች መካከል ሁለቱ ሆስፒታል መግባታቸው እየተነገረ  ነው። በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ ብሎም ዝርዝር መረጃ እንደደረደን እናቀርባለን። ከክስተቱ ጋር በተያያዘ መረጃው ያላችሁ ሰዎች በዚህ ኢሜል መልእክቶቻችሁን ልትልኩልን ትችላላችሁ: nomonanoto@gmail.com