Posts

የትናንትናውን የሃዋሳ ከተማ ግዲያን ተከትሎ የተለያዩ ኣስተያዬቶች በማህበራዊ መረቦች እየቀረቡ ነው

የትናንትናውን የሃዋሳ ከተማ ግዲያን ተከትሎ የተለያዩ ኣስተያዬቶች በማህበራዊ መረቦች  እየቀረቡ ነው። ከቀረቡት ኣስተያዬቶች መካከል ለኣብነት ያህል የሚከተለውን ይመልከቱ። Meles Zenawi's killing squad- instructed by the puppet Southern regional president Shiferaw Shuguxe (remote controlled by the current Minister for foreign affairs-Hailemariam Desalegn-who was the main culprit of the May 24, 2002 massacre of the 100s of Sidama civilians at Loqqe village--- ultimately masterminded by Meles Zenawi himself) once again started slaughtering Sidama people in their own soil in attempt of silensing their peaceful and no-violent quest for regional Self Adminstration. The Sidama people claimed nothing else other than this!! The Sidama people never stop this quest until it's 100% addressed Constitutionally without further delay. The Sidama people never give up their quest and never give in into intimidation and killings. The Sidama people's quest peacefully and non-violently continues! This must be clear to those who share their stances or o

ፈዴራል ፖሊስ በሃዋሳ ከተማ ወልደ ኣማኑኤል ጎዳና ላይ ሰላማዊ ሰዎችን ስደበድብ ኣመሽ

በዛሬ ቀን በሃዋሳ ከተማ በተለምዶ ወልደ ኣማኑኤል ሃውልት ኣካባቢ ካለው ኣንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በጊዜያዊ ካምፒነት ተከራይተው የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ ኣባላት በኣካባቢው በመንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩትን  የሲዳማን ተማሪዎች በመደብደባቸው የኣካባቢው ነዋሪዎች ድርጊቱን በመቃዎወም ተቃውሞኣቸውን ድንጋይ በመወርወር ስገልጹ ማምሸታቸው ተገለጸ። ከኣከባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ የሲዳማ የክልል ጥያቄን ተከትለው በኣካባቢው የሰፈሩት እና በተለይ ሲዳማውን በክፉ ኣይን ስከታተሉ የነበሩት የፈደራል ፖሊስ ኣባላት ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት መንገድ ላይ የነበሩትን ተማሪዎች ደብድበው ለሆስፒታል እና ለሞት ዳርጓዋል። ከተደበደቡ ተማሪዎቹ መካከል ከዎንሾ ወረዳ የመጣ ኣብረሃም የተባለው  ተማሪ ኣንዱ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ ከተደበደበ በሃላ በኣንድ ፈዴራል ፖሊስ ተገድሏል የሚል ወሬ በመነፈስ ላይ ነው። በተጨማሪም ተማሪዎቹ ለምን ይደበደባሉ በማለት የተቃዎሙ ሰዎችም ራሳቸው በፈዴራል ፖሊስ በኣሰቃቂ ሁኔታ የተደበደቡ ሲሆን ከነዚሁ ሰዎች መካከል ሁለቱ ሆስፒታል መግባታቸው እየተነገረ  ነው። በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ ብሎም ዝርዝር መረጃ እንደደረደን እናቀርባለን። ከክስተቱ ጋር በተያያዘ መረጃው ያላችሁ ሰዎች በዚህ ኢሜል መልእክቶቻችሁን ልትልኩልን ትችላላችሁ: nomonanoto@gmail.com

ዳግም የሲዳማ እናቶች እንዳያነቡ!

Sidaamu Amuwi Lanyikimeesho Wila’anoki Gede ፖለቲካ እና ሥልጣንአርብ ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ.ም. የአዋሳ ከተማ ከወትሮው የተለየ ግርግር ይታይባታል። ያ  አመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተሃድሶ ፕሮግራም ቁም ስቅሉን እያየ የነበረበት ቀውጢ ጊዜ ነበር። ወቅቱ ነባር የህወሓት ታጋዮች ከቀድሞው የትግል አጋሮቻቸው ጋር በፖለቲካው መግባባት ባለመቻላቸው  ምክንያት ድርጅታቸው ለሁለት የመሰንጠቅን አደጋ  ያስተናገደበት ወቅት ነበር፡፡ አዋሳም የዚህ ወላፈን ተቋዳሽ ብቻም ሳትሆን ትዕይንቱን ዘግናኝ በሆነ ታሪካዊ ክስተት ያስተናገደች ከተማ ነበረች።የአዋሳ ከተማ ከ1994 በፊት በተደነገገው የፌዴራል ሥርዓት መሰረት የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስትና የሲዳማ ዞን መስተዳደር የጋራ ዋና ከተማ ወይም ማዕከል ሆና እስከ 1994ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ዘለቀች። ይሁን እንጂ ከመንግስት ተላልፏል በተባለ ትዕዛዝ መሰረት አዋሳ የክልሉ መንግስት ርዕሰ ከተማ ብቻ እንድትሆንና ‹‹የሲዳማ ዞን መስተዳደር ወደ አለታወንዶ ከተማ እንደተዛወረ ተወስኗል›› የሚል ትዕዛዝ ተላልፏል የሚለው ዜና የሲዳማ ብሄር ተወላጆችን እጅግ አስቆጣ፡፡ ህዝቡም ህገ-መንግስቱ ይፈቅድልኛል ባለው ሰላማዊመቃወሚያ ዘዴን ተጠቅሞ ብሶቱን ለማሰማት ወደአደባባይ ለመውጣት መሰናዶውን አጠናቀቀ። በወጣው ፕሮግራም መሰረት ሰልፉ ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓ.ም. እንደሚካሄድና መነሻውም ከሃዋሳ ከተማ በስተደቡብ ከ5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ‹‹ሎቄ›› ከተባለች ከተማ ሆኖ የሰልፍ መጨረሻም በአዋሳ እምብርት ከሚገኘው አብዮት አደባባይ እንዲሆን ታቀደ። በታቀደው ፕሮግራም መሰረት የብሄሩ ተወላጆች ከየመንድራቸው የተውጣጡ ቁጥራቸው ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጐች በባ

የአዋሳው እሳት የወያኔ መጥፊያ ይሆናል!!!

Image
ከአስር ዓመታት በፊት “ሲዳማ ክልል ሁና ትደራጅ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው በአንድ ቀን ውስጥ ከ60 በላይ የሆኑ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በአጋዚ ጦር በግፍ ተጨፈጨፉ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳቶች ተዳረጉ፤ በርካቶች ታሰሩ። ከሰባት ዓመታት በፊት ደግሞ  - በምርጫ 97 ማግሥት – “ድምፃችን ይከበር” በማለታቸው እስካሁን ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ የአዋሳ ወጣቶች ተገደሉ፤ በርካታ ወጣቶችና አዛውንት ታሰሩ፣ ተደበደቡ፣ ተጋዙ። ዛሬም አዋሳ በውጥረት ውስጥ ነች። የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ሠራዊት እንደለመደው የአዋሳን እና የአካባቢው ነዋሪዎች ሊገድል፣ ሊያቆስል፣ ሊያስር ዘምቷል። ከአዋሳ ወጣ ብላ በምትገኘው አለታ ጭኮ የመለስ ዜናዊ ፓሊሶች ነዋሪዎችን ገድለዋል፤ በርካቶችን አቁስለዋል። ነዋሪዎችም በፓሊሶች ለደረሰባቸው ጥቃት በወሰዱት የመከላከል እርምጃ አንድ ፓሊስ ሕይወቱን አጥቷል። የሚሰማቸው ጆሮ አላገኙም እንጂ ሕዝብን ከሕዝብ በማጣላት ሙያ የተካኑት  የመለስ ካድሬዎች “አዋሳ ከተማ ወደ ፌደራል ትጠቃለል  ያሉት ወላይታዎች ናቸው” እያሉ በማስወራት ላይ ናቸው። መለስ ዜናዊ የፈጠረው ዘርን ብቻ መሠረት ያደረገው “ፌደራሊዝም” በማር የተለወሰ መርዝ መሆኑ ባለፉት ሃያ ዓመታት በተግባር ያየነው ጉዳይ ነው። የመለስ ዜናዊ የውሸት ፌደራሊዝም ከሁሉም የአገራችን ክፍሎች በባሰ የተሳለቀበት “የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት” በሚባለው የአገራችን ክፍል ነው። አዋሳ ደግሞ የዚህ የአቅጣጫ ስያሜ የተሰጠው “መንግሥት” መቀመጫ ናት። አዋሳ እና እሷ የምትወክለው “የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት” የመለስ ዜናዊ ፌደራሊዝም አስከፊ ገጽታ ማሳያዎች ናቸው። በመለስ ዜናዊ ፌደራሊዝም ምክንያት ውቧ አዋሳ የግጭቶች

ኢሳት “ሰበር ዜና” የሲዳማ ወጣቶች “ሲወን” የሚል አዲስ የህቡዕ ድርጅት ዛሬ በአዋሳ መሰረቱ

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣  የግብርና ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የክልሉ ፖሊስ ተወካዮች፣ የምክር ቤት አባላትና  እና ሌሎችም ከ 300 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ዛሬ በአዋሳ ከተማ በህቡእ ተሰባስበው የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ የሚል ድርጅት መስረተዋል። በጉባኤው ላይ ከ22 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተወከሉ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን፣ የትግል ስትራቴጂያቸውን እና አላማቸውን ለተሰብሳቢው ይፋ አድርገዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ጉባኤ ላይ የወጣቱ አመራሮች የሲዳማ ህዝብ ማንነቱን ለማረጋገጥ የሚያደረገውን ትግል ወጣቶቹ ወደ ፊት ለመግፋት መወሰናቸውን የገለጡ ሲሆን ፣ የመጨረሻ ግባቸው ኢትዮጵያን አሁን ከገባችበት ፈተና ለማላቀቅ ትግል ማድረግ መሆኑን ገልጠዋል። የወጣቶቹ አመራሮች የተለያዩ ብሄረሰብ ተወካዮችን ለመጥራት የተገደዱትም አላማቸው አካባቢያዊ ሳይሆን ብሄራዊ አጀንዳ ያለው መሆኑን ለማሳየት ነው ብለዋል። በጉባኤው ላይ የወላይታ ተወካይ ” እኛ ወንድማማች ህዝብ ነን፤ ኢትዮጵያዊነታችን ይበልጣል፣ ሀይለማርያም ደሳለኝ በሰራው ስህተት ወላይታ በሙሉ በሲዳማ የሚጠላበት እና የምንለያይበት ምክንያት የለም ፣ ሀይለማርያም በምንም አይነት መልኩ ወላይታን አይወክልም፤ ስለዚህ በእርሱ አይን ባታዩን፣ አብረን ብንሰራ ይህችን አገር እናሳድጋለን፣ ከገባችብት ችግር እናወጣለን” ብሎአል። የንቅናቄው አመራሮች “የእኛ ትግል የብሄር ጥያቄ አይደለም ፤ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ እና የሌሎች ብሄርና ብሄረሰቦችን ተወካዮችን የጋበዝነውም አላማችን ብሄራዊ መሆኑን ለማሳየት ነው፣ አሁን የሲዳማን ጥያቄ አንስተናል ትግላችን ግን በዚህ አያቆምም፣ አብረን ለኢትዮጵያ ነጻነት እንታገላለን” የሚል መልስ ሰጥተዋል።