የጭኮ እና የይርጋለም ህንጻዎች መፈክሮች ተውበው ታዩ፣ መፈክሮችን ለማጥፋት ህንጻዎች እንዲፈርሱ ተደርጓል
ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጭኮና በይርጋለም ከተሞች ዛሬ ጠዋት የታየው ነገር በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ይላል ዘጋቢያችን። ሰላም የራቀውና በሀዘን ድባብ ላይ የሚገኘው የከተማው ህዝብ ከቤቱ በጧት ሲወጣ የጠበቀው እንደ ሰሞኑ ፍርሀትና ጭንቀት ሳይሆን ደስታና ተስፋ ነበር። በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሌሊቱን በሙሉ በደማቅ ቀለማት ሲሸለሙ አድረዋል። ህዝቡም በግድግዳዎቹ ላይ የተጻፉትን መፈክሮች ለማየት እየተደዋዋለ ወደ አደባባዩ ጎረፈ። የሚይዙት የጠፋቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና ፖሊሶች መፈክሮችን በውሀ ለማጥፋት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። ተስፋ በቆረጠ ስሜትም ጽሁፎችን ለማጥፋት የፊት ግድግዳዎች መፍረስ እንደገና መልሰውም በስሚንቶ መለሰን ነበረባቸው። ፖሊሶች የህንጻ መቦርቦሪያ ማሽኖች እየያዙ በየህንጻዎች ላይ በመውጣት ሲቦረቡሩ ፣ ሲለስኑ የከተማው ህዝብም በፖሊሶች ድርጊት ይዝናና ነበር። ከ 10 በላይ መፈክሮች በከተማዋ አስፓልት ላይም ተጽፈው ነበር። ፖሊሶችም መኪኖችን አስቁመው አስፓልቱን በጋዝ ሲወለውሉ ውለዋል። ዘጋቢያችን በጭኮ ወረዳ በግድግዳዎች ላይ ከተጻፉት መፈክሮች መካከል የተወሰኑት እንደሚገኙበት ገልጧል።፡” በጭኮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ” ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን ህዝብ አይወክልም፣ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ይመለስ፣ ጥያቄያችን ሳይመለስ ትግላችን አይቋረጥም” ይላል። ከተማ መሀከል ከተጻፉ መፈክሮች መካከል ” የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ይመለስ ” የሚል ተጽፎአል። በከተማዋ መናሀሪያ ላይ ደግሞ ” አዋሳና ሲዳማ አይነጣጠሉም “፣ የኢህአዴግ ካድሬዎች የሲዳማን ህዝብ ደም ማፍሰስ ያቁሙ፣ የሲዳማ ተወላጆች የወገኖቻቸውን ደም ማፍሰስ ያቁሙ፣ ሲ