Posts

ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ

Image
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል። ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ።በደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሠ-ከተማ በአዋሳና በአካባቢዉ ከተሞች አደባባይ የወጣዉን ሕዝብ ለመቆጣጠር መንግሥት በርካታ ፀጥታ አስከባሪዎች አስፍሯል።የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል።ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ ሁኔታዉን ተከታትሎታል። ሙሉ ዘጋባውን በሚቀጥለው ሊንክ ያዳምጡ ሠላማዊ ሠልፍና ግጭት በደቡብ ኢትዮጵያ

በመላው ኣለም ላይ የሚገኙ የሲዳማ ዳይስፖራ በሲዳማ ዞን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄ በንቃት በመከታተል እና በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ገለጹ።

የዳይስፖራው ተወካዮች ለሲዳማ ወራንቻ የኢንፎርሜሽን ማእከል በላኩት መልእክት እንዳስታወቁት፤ የሲዳማ ህዝብ ያነሳቸውን የመልካም ኣስተዳደር እና የክልል ጥያቄዎችን ይደግፋሉ ለተግባራዊነቱም ከዞኑ ህዝብ ጎን ይቆማሉ። በሰሜን ኣሜሪካ፡ በታላቋ ብርታኒያ፡ በኖርዌይ፡ በኔዘርላንድ፡ በመካከላኛው ኣውሮፓ ኣገራት፡ በህንድ፡ በሳውድ ኣረቢያ እና ደቡብ ኣፍሪካ ነዋሪ የሆኑት የዞኑ ዳይስፖራ ኣባላት ህዝባዊ ንቅናቄውን በቅርበት በመከታተል ላይ መሆናቸውን ኣስታውቀዋል። ህዝባዊ ንቅናቄው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በንቅናቄው ላይ የኣለም ህዝብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው በተለያዩ የዜና ኣውታሮች የሚቀርቡ ዘገባዎች ከህዝባዊው ንቅናቄ ኣላማዎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የማደረግ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ኣስረድታዋል። ኣያይዘውም ለህዝባዊ ንቅናቄ መሳካት ኣስፈላጊውን ደጋፍ ለማደረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል።

Image
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአዋሳ እና ከሲዳማ ዞን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በካናዳ ትምህርታዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው በመመለስ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአዋሳ ጉዳይ ለተነሳው ተቃውሞና ለጠፋው የሰው ህይወት ችግሩን የቀሰቀሱትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ለክልሉ ራዲዮ ተናግረዋል። አቶ ሽፈራው የአዋሳ ጉዳይ በሀሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል። ከህዝቡና ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር በመሆን ጉዳዩን እንደሚያብላሉትም ገልጠዋል። ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑነ በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ቢገልጡም ሀላፊነቱን ለመውሰድና ይቅርታ ለመጠየቅ አልሞከሩም፣ ይልቁንም ችግሩን የፈጠሩት የተቃዋሚ አባላት ፓርቲና አንዳንድ ባለሀብቶች መሆናቸውን በመግለጥ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ወገኖች ግን ግጭቱን የቀሰቀሱት የደኢህዴግ ኢህአዴግ አባላት ናቸው:: አዋሳ አሁንም በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀች ነው። ወደ ይርጋለም በሚወስደው መንገድ ላይ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰፍረው ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት

Freedom

Image

የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻቸውን ለምመለከተው መንግስታዊ ኣካል በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ እንዲያስችላቸው በየወረዳዎች ደረጃ የሚወክሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ላይ ሲሆኑ፤ የክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው ህዝብ እንዲረጋጋ በመጠየቅ ላይ ናቸው::

በየኣስር ኣመቱ በክልል ባለስልጣናት እየረቀቀ የሚቀርበውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ጥያቄ ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ታስቦ የተጀመረውን የክልል ጥያቄ ከዳር ለማድረስ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ እንደቀጠለ ሲሆን: የሲዳማ ህዝብ ያሉትን የመልካም ኣስተዳደር ችግሮን እና የክልል ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቀረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል:: የበንሳ ወረዳ የህዝብ ንቅናቄ ኣባላት የወረዳው ህዝብ በመወከል ህዝባዊ ጥያቄዎችን የሚያቀረቡ ሽማግሌ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችም የባንሳ ወረዳ ኣረኣያ በመከተል ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ላይ መሆናቸው ተገልጿል:: ሰሞኑን በዞኑ ኣስተዳዳሪ የተመራው ኣንድ ከሲዳማ ዞን እና ከክልል ቢሮዎች የተወጣጣ የሲዳማ ልኡካን ቡድን ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣቅንቶ የተመለስ ሲሆን በዛሬው ቀን ሙሉ ቀኑን የዞን ካቢኔዎች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጓዧቹ ከፈዴራል መንግስት ባለስጣናት የተሰጣቸውን ምላሽ ለመስማት ኣልተቻለም:: ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች የፈዴራል መንግስት ኣጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጥ እንዳልቀረ ከውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ያገኝናቸው መረጃዎች ያሳያሉ::   በዛሬው እለት መላዋ ሲዳማ በተለይ የሃዋሳ ከተማ ምንም እንኳን በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለ ቢሆንም በከተማዋ ጸጥ ረጭ ብለው የነበሩ ንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ ቀደሞው እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል::  በሌላ በኩል የክልሉ ፕሬዚዴንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልሉ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክት ያስተላላፉ ሲሆን፤ በደኢህዴን ተዘጋጅቶ ወሳኔ ሳይሰጥበት በድንገት ወደ ህዝብ ጆሮ የደረሰው እና ለተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ መሰረት የሆነው ጽሁፍ “በሬ ወለደ ወሬ”