Posts

Freedom

Image

የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻቸውን ለምመለከተው መንግስታዊ ኣካል በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ እንዲያስችላቸው በየወረዳዎች ደረጃ የሚወክሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ላይ ሲሆኑ፤ የክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው ህዝብ እንዲረጋጋ በመጠየቅ ላይ ናቸው::

በየኣስር ኣመቱ በክልል ባለስልጣናት እየረቀቀ የሚቀርበውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ጥያቄ ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ታስቦ የተጀመረውን የክልል ጥያቄ ከዳር ለማድረስ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ እንደቀጠለ ሲሆን: የሲዳማ ህዝብ ያሉትን የመልካም ኣስተዳደር ችግሮን እና የክልል ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቀረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል:: የበንሳ ወረዳ የህዝብ ንቅናቄ ኣባላት የወረዳው ህዝብ በመወከል ህዝባዊ ጥያቄዎችን የሚያቀረቡ ሽማግሌ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችም የባንሳ ወረዳ ኣረኣያ በመከተል ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ላይ መሆናቸው ተገልጿል:: ሰሞኑን በዞኑ ኣስተዳዳሪ የተመራው ኣንድ ከሲዳማ ዞን እና ከክልል ቢሮዎች የተወጣጣ የሲዳማ ልኡካን ቡድን ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣቅንቶ የተመለስ ሲሆን በዛሬው ቀን ሙሉ ቀኑን የዞን ካቢኔዎች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጓዧቹ ከፈዴራል መንግስት ባለስጣናት የተሰጣቸውን ምላሽ ለመስማት ኣልተቻለም:: ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች የፈዴራል መንግስት ኣጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጥ እንዳልቀረ ከውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ያገኝናቸው መረጃዎች ያሳያሉ::   በዛሬው እለት መላዋ ሲዳማ በተለይ የሃዋሳ ከተማ ምንም እንኳን በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለ ቢሆንም በከተማዋ ጸጥ ረጭ ብለው የነበሩ ንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ ቀደሞው እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል::  በሌላ በኩል የክልሉ ፕሬዚዴንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልሉ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክት ያስተላላፉ ሲሆን፤ በደኢህዴን ተዘጋጅቶ ወሳኔ ሳይሰጥበት በድንገት ወደ ህዝብ ጆሮ የደረሰው እና ለተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ መሰረት የሆነው ጽሁፍ “በሬ ወለደ ወሬ”

የሲዳማ ዳይስፖራ በማወያያ ጽሁፉ ላይ የሰላ ሂስ ኣቀረበ

ሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው? በሚል የደኢህዴን ስራ ኣስፈጻም ኮሚቴ በተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ ላይ ከተላያዩ ኣካላት እየቀረበ ያለው ትችት ተፋፉሞ ቀጥሏል፡፡የሲዳማ ዳይስፖራ በማወያያ ጽሁፉ ላይ የሰላ ሂስ ኣቅርቧል። በኣቀረበው ሂስ ላይ የማወያያ ጽሁፉን ከተለያየ ጎን የተመለከተው ሲሆን፤ ከስያሜው ጀምሮ በጽሁፉ ውስጥ የተነሱ እና ትኩረት የተሰጣቸውን ጽንስ ሀሳቦች ገምግመዋል። ''The Sidama leadership that ensured that Hawassa grew faster than any other towns in the country during the past 20 years is regarded as having no political commitment and capacity to deliver these all of the sudden! Another blatant fallacy!''   ከጽሁፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ::  የማወያያ ጽሁፉ እና የዳይስፖራውን ሂስ በሚቀጥለው ሊንክ ይመልከቱ። ደኢህዴን በሃዋሳ ከተማ እጣ ፋንታ ላይ በየደረጃው ያሉት ኣመራሮች ለማወያያት ያዘጋጁት ባላ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ Ethiopia Regime Manfesto Uprooting Sidama From City

የሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው? በሚል የደኢህዴን ስራ ኣስፈጻም ኮሚቴ በሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ በየደረጃው ካሉት ከሚመለከታቸው ኣመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ ኣዘጋጅቶት በነበረው በለ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ ላይ ትችት ቀረበ:: የማወያያ ጽሁፉ የሲዳማ ህዝብ ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ እሴቶቹን የሚያንቋሽሽ እና ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ለ ህዝቡ ያለውን ንቀት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ::

የሲዳማ ምሁራን የማወያያ ጽሁፉን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ መረቦች ላይ ያቀረቡት ትችት እንደምያመለክተው፡ በደኢህዴን ስራ ኣስፋጻሚ ኮሚቴ የተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ የሃዋሳ ከተማ በጥቂት ኣመታት ውስጥ ያሳየችው እድገት በሲዳማ ኣስተዳደር ብቃት መሆኑን የ ሚ ክድ፤ የሲዳማን ህዝብ እንግዳ ተቀባይነትን ከግምት ውስጥ ያላስገባና በጭፍን የሲዳማን ህዝብ የሚያጥላላ ነው ብለዋል :: በማወያያ ጽሁፉ ላይ የቀረበውን ሙሉ ትችት እንደምከተለው ኣቅርበናል :: ሲዳማ ከዘመነ አፄ ምኒልክ እስከ ደኢህዴን/ኢህአዴግ የአፄ ምኒልክ ተዋጊ ኃይል የሲዳማን ህዝብ በአስከፊ ጭቆናና ብዝበዛ ስር ለማስተዳደር ባካሄደው ወረራ በወቅቱ ይጠቀምበት የነበረውን የጦር መሳሪያ ከህዝቡ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት አንጻር የማይጣጣም በመሆኑ የሲዳማን ህዝብ በግፍ እየጨፈጨፈ እስከ ደቡባዊ አገር ድረስ መዝለቁ አልቀረም፡፡ በወቅቱ ያደረሰው ብዝበዛና ጭቆና የህዝባችንን ሰብዓዊ ክብር ያዋረደና ነፃነቱን ያሳጣ በመሆኑ የሲዳማ ህዝብ በቡድንና በተናጥል ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ከምኒልክ ወረራ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለስላሴ ውድቀት ድረስ ለማንነቱና ለሰብዓዊ ክብሩ ያደረጋቸው የነፃነት ተጋድሎዎች ለታሪክ የሚዘከሩ ናቸው፡፡ በተለያየ መንገድ ፈርጀ ብዙ የሆኑ የፀረ ነፍጠኛ ወይንም መልከኛ ትግል እስከ ደርግ መንግስት ቀጥሎ የመልከኛ ስርዓት ተወገደ፡፡ እንደማንኛውም ነፃነት ፈላጊና ገባሪ ብሔሮች ሁሉ የሲዳማ ሕዝብ የተቀማውን የመሬት ባለቤትነት መብት አገኘ፡፡ ቀጣይ የማንነትና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎች ባይመለሱለትም የሲዳማ ሕዝብ ከ70 ዓመታት በፊት ከአባቶቹ እጅ የተነጠቀውን መሬት መልሶ በማግኘት ለአጭር ጊዜም ቢሆን እፎይታ ያገኘ መስሎ ቢታይም ሰው በላው የወቅቱ መንግሥት ግን በር

በሲዳማ ዞን እየተነሳ ባለው ተቃውሞ የመንግስት እጅ አለበት ተባለ

Image
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ለዘመናት ተቻችለው የኖሩ ህዝቦች እንዲጋጩ ለማድረግ የመንግስት ባለስልጣናት ሆን ብለው እየሰሩ ነው። ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ፣ በመብት አፈናው እና በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች እየተማረረ፣ ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል እያለ በሚናፍቅበት በዚህ አስቸጋሪና አስፈሪ ወቅት፣ መንግስት የዋሳ ከተማን አስተዳደር እንደገና የህዝብ አጀንዳ አድርጎ በማቅረብ ግጭት እንዲነሳ መጣሩ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። የዞኑ ባለስልጣናት የሚያስወሩት ዘርን ከዘር የሚያጋጭ ወሬ የከተማው ህዝብ የፍርሀትን ካባ እንዲደርብ እንዳደረገው ነዋሪዎች ይገልጣሉ። በዛሬው እለት ዳቶና  መምቦ በተባሉ አካባቢዎች ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ዘርፊያ መካሂዱን፣ መኪኖች ታግተው መዋላቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል። በከተማዋ አሉ ሱቆች ዝርፊያ በመፍራት ተዘግተው መዋላቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በዳቶና መምቦ አካባቢዎች የፌደራል ልዩ አድማ በታኝ ፖሊሶች በአስለቃሽ ጭስ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር መቻላቸውን ውጥረቱ ግን አሁንም መኖሩን ዘጋቢዎች ገልጠዋል። ግጭቱ  ከአዋሳ ከተማ እጣ ፋንታ አልፎ የዘር ጉዳይ እየሆነ መምጣቱ፣ የከተማውን ህዝብ ለሁለት መክፈሉም እየተነገረ ነው። የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች ለዘመናት ተፈቃቅሮ የኖረውን ህዝብ የሚያበጣብጠው መንግስት በመሆኑ ተቃውሞው ሁሉ መንግስት ላይ እንዲሆን ወጣቶችን የማሳመን ስራ እየሰሩ ነው። የሲዳማ ተወላጅ ያለሆኑ የአዋሳ ነዋሪዎች ጥያቄው ከዘር አልፎ አገርአቀፍ አጀንዳ ይዞ ከመጣ ሊቀላቀሉዋቸው ዝግጁ መሆናቸውን እየገለጡ ነው። አንድ ስሙን መግለጥ ያልፈለገ ወጣት ችግሩ እንዲህ በቀላሉ ይፈታል ብሎ እንደማያምን ገልጦ ፣ ተቃውሞውን ወደ ችግር ፈጣሪው መን