Posts

በሲዳማ ዞን እየተነሳ ባለው ተቃውሞ የመንግስት እጅ አለበት ተባለ

Image
ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዋሳ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ለዘመናት ተቻችለው የኖሩ ህዝቦች እንዲጋጩ ለማድረግ የመንግስት ባለስልጣናት ሆን ብለው እየሰሩ ነው። ህዝቡ በኑሮ ውድነቱ፣ በመብት አፈናው እና በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች እየተማረረ፣ ከዛሬ ነገ ለውጥ ይመጣል እያለ በሚናፍቅበት በዚህ አስቸጋሪና አስፈሪ ወቅት፣ መንግስት የዋሳ ከተማን አስተዳደር እንደገና የህዝብ አጀንዳ አድርጎ በማቅረብ ግጭት እንዲነሳ መጣሩ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል። የዞኑ ባለስልጣናት የሚያስወሩት ዘርን ከዘር የሚያጋጭ ወሬ የከተማው ህዝብ የፍርሀትን ካባ እንዲደርብ እንዳደረገው ነዋሪዎች ይገልጣሉ። በዛሬው እለት ዳቶና  መምቦ በተባሉ አካባቢዎች ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ዘርፊያ መካሂዱን፣ መኪኖች ታግተው መዋላቸውን ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል። በከተማዋ አሉ ሱቆች ዝርፊያ በመፍራት ተዘግተው መዋላቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በዳቶና መምቦ አካባቢዎች የፌደራል ልዩ አድማ በታኝ ፖሊሶች በአስለቃሽ ጭስ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር መቻላቸውን ውጥረቱ ግን አሁንም መኖሩን ዘጋቢዎች ገልጠዋል። ግጭቱ  ከአዋሳ ከተማ እጣ ፋንታ አልፎ የዘር ጉዳይ እየሆነ መምጣቱ፣ የከተማውን ህዝብ ለሁለት መክፈሉም እየተነገረ ነው። የሲዳማ አገር ሽማግሌዎች ለዘመናት ተፈቃቅሮ የኖረውን ህዝብ የሚያበጣብጠው መንግስት በመሆኑ ተቃውሞው ሁሉ መንግስት ላይ እንዲሆን ወጣቶችን የማሳመን ስራ እየሰሩ ነው። የሲዳማ ተወላጅ ያለሆኑ የአዋሳ ነዋሪዎች ጥያቄው ከዘር አልፎ አገርአቀፍ አጀንዳ ይዞ ከመጣ ሊቀላቀሉዋቸው ዝግጁ መሆናቸውን እየገለጡ ነው። አንድ ስሙን መግለጥ ያልፈለገ ወጣት ችግሩ እንዲህ በቀላሉ ይፈታል ብሎ እንደማያምን ገልጦ ፣ ተቃውሞውን ወደ ችግር ፈጣሪው መን

ሲኣን የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ክልል የመሆን ጥያቄ በኣስቸኳይ እንድመለስ ጠየቀ፤ በሲዳማ ህዝብ ስም እየነገዱ የሲዳማን ማንነት ለመሸጥ የምሯሯጡ ጥቂት ኣድርባዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኣስጠነቀቀ::

New ሲኣን የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ክልል የመሆን ጥያቄ በኣስቸኳይ እንድመለስ ጠየቀ፤ በሲዳማ ህዝብ ስም እየነገዱ የሲዳማን ማንነት ለመሸጥ የምሯሯጡ ጥቂት ኣድርባዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኣስጠነቀቀ:: የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሲኣን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሲዳማ ህዝብ በህገ መንግስቱ የተሰጡትን የዲሞክራሲያዊ መብቶች ህጉና ደንቡን መሰረት በማድረግ በሰላማዊ መንገድ ስጠይቅ መቆየቱን ኣስታውሶ ከተጠየቁት ጥያቄዎች ኣንዳቸውም ተጨባጭ ምላሽ እንዳላገኙ ኣመልክቷል:: የሲዳማ ህዝብ የጠየቀው ክልል የመሆን ጥያቄ በህገ መንግስት የተደነገጉውን ክልል የመሆን ቅድመ ሁኔታ በተገቢው መልኩ ያሟላ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ ለራሱ ኣገዛዝ እንዲመቸው ሲል ጥያቄውን በልማት ሽፋን ሳይመልስ መቆየቱን ጠቅሶ፡ ኣሁንም ቢሆን በድጋሚ የተነሳው የክልል ጥያቄው በኣግባቡ እንዲመለስ ጠይቀዋል:: ኣያይዞም በሲዳማ ህዝብ ስም እየነገዱ የህዝቡን ማንነት ለማሸጥ የምሯሯጡ ኣድርባዮች ከድርጊቻቸው እንዲቆጠቡ ኣስጠንቅቋል:: የጋዜጣዊ መግለጫውን ሙሉ ቃል በሚቀጥላው ሊንክ ይመልከቱ : የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ሲኣን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ

ኢሳት ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በሲዳማ ዞን ውስጥ በመከሄድ ላይ ያለውን የህዝብ ንቅናቄን በተመለከተ የሚያቀርባቸው ኣንዳንድ ዘገባዎች የህዝባዊ ንቅናቄ ኣላማ ከግምት ውስጥ ያላስገቡና ግጭቶችን የሚያባቡሱ ናቸው በሚል ቅረታ ቀረበ::

New ኢሳት ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በሲዳማ ዞን ውስጥ በመከሄድ ላይ ያለውን የህዝብ ንቅናቄን በተመለከተ የሚያቀርባቸው ኣንዳንድ ዘገባዎች የህዝባዊ ንቅናቄ ኣላማ ከግምት ውስጥ ያላስገቡና ግጭቶችን የሚያባቡሱ ናቸው በሚል ቅረታ ቀረበ:: ቅረታ ኣቅራቢዎቹ እንደምሉት ከሆነ ኢሳት ሰሞኑን በተከታታይ በሲዳማ ዞን ውስጥ በመከሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄውን እንደ ህዝባዊ ኣመጽ ኣድርጎ ማቅረቡ ትክክል ኣይደለም ብለዋል::  የዞኑ ነዋሪዎች ህገ መ ንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በማቅረብ ላይ ያሉትን የክልል ጥያቄ ከህዝባዊ ኣመጽ ጋር ተያያዥነት እንደሌለው ገልጸዋል:: ከዚህም በተጨማሪ በዞኑ ውስጥ ከፍተኛ የሆን የጎሳ ግጭት ልነሳ ይችላል በማለት የሚያቀርበው ዘገባ የሲዳማ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ለዘመናት ተቻችሎ ኣብረው የመኖር ባህሉ ላይ ጥላ ሽት እንደመቀባት እና የሲዳማን  ህዝብ ገጽታ እንደማባላሸት ይቆጠራል ብላዋል:: ኢሳት ሌሎች የኣገሪቱ የዜና ኣውታሮች ለመዘጋብ ወኔ ባጡት የሲዳማ ዞን ህዝባዊ ንቅናቄ ላይ ተከታታይ ዘጋባዎችን በማቅረቡ ያላቸውን ኣድናቆት የገለጹት እነኝው ቅረታ ኣቅራቢዎች ፤ ዘጋባዎቹን በ እውኔታ ላይ የተሞረከዙ በማድረግ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ እንዲደግፍ ጠይቀዋል:: ከቀረቡት ቅረታዎች መካከል ለኣብነት ያህል የሚቀጥለውን ይመልከቱ:   Dear Ethsat Editor, Thank you for your hard work in informing Ethiopian Diaspora and further. The reason of this email is in order.  It's to let you know my utter disappointment after I've watched your purely one-side

ESAT Breaking News Awassa Protest update June 22, 2012

Image
New

Ethiopia: Ethnic Clashes Feared in Sidama Zone, SNNP

New 22 June 2012 [ESAT] There are reports of heightened fear in Sidama Zone following the conflict in Aleta Chuco town two days ago. There are reports of student demonstrations and road blockades in Tula town 10 KM outside of Awassa. Government workers were denied passage to do their field work in the surrounding towns. The students who are believed to be ethnic Sidama are stopping cars and asking ethnic Wolaitas to come out. Two ethnic Wolaitas are so far reportedly killed inside of Awassa referral hospital as of today. The news of the two killed at the hospital have inflamed Wolaitas and many fear could ignite ethnic conflict. Our reporter who has been traveling in the area said businesses at the outskirts of Awassa town are closed since two days ago. There is a huge presence of Federal Police in Awassa and its environs. A lot of fliers are circulating in Awassa and the surrounding towns. ‘Awassa is being sold to Wolaitas!’, ‘Let us save Awassa!, come out to protest and resist