Posts

Ethiopian Regime Resumes Another Massacre of Sidama People: 2 dead, 7 wounded

June 20 2012 (SLF)- While the Sidama people are remembering victims of Loqqe massacre on the 10th year anniversary, the regime has started another wave of killings of innocent Sidama people in Chuko area. The killing took place when students and other Sidama people were staging demonstration to demand answer about the plan to control Hawaasa city by the Federal government. According to our sources from the area, 2 people were reported dead; one a business person and the other is a farmer. Seven others were wounded. A teenage girl that critically wounded is being treated at Yirgalem hospital. There is no denying that the Ethiopian regime always responds with brutal force to any peaceful quest instead of listening and understanding what people want. 10 years ago, over 100 Sidama people were massacred when peacefully demonstrating to request the government of their basic human rights. The Ethiopian regime and its affiliates have already controlled most resources of Sidama while coun

የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ በተመለከተ ኣስታያየቶች እየጎረፉ ነው

ከኣስታያዬቶቹ መካከል፥ የዳንግላው ዋርካ ተብሎ በሚታወቀው ትልቁ የኢትዮጵያውን ዌይብ ሳይት ላይ እንደጻፈው: የሲዳማ ሕዝብ በሀዋሳ ከተማ ባለቤትነት ጥያቄ በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በአዋሳ ከተማ በፌደራል / ወያኔ መልዕክተኞችና በሲዳማ ክልል የፓርላማ ተወካዮች መካከል በተደረገው ፍጥጫ የሲዳማ ተወካዮች ጉባኤውን ረግጠው ሲወጡ በርካታ የሲዳማ ተወላጅ ባለሀብቶች : ባለስልጣኖችና ተማሪዎች ከየቤታቸው በሌሊት እየታፈኑ እየታሰሩ ሲሆን አንድ ግለሰብ በአጋዚ ተደብድቦ ሕይወቱን አጥቷል :; ከተማዋ በአጋዚ ሠራዊት ታንክና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ሄሊኮፕተሮች በብዛት እያንዣበቡባት ነው :: አዋሳ ባሁኑ ጊዜ በፍርሐትና በጭንቀት ተውጣለች :: ሲዳሞች ሲዳማ ሕዝብ በአዋሳ ከተማ የዞን ዋና መሥሪያ ቤቶች አዋሳ ውስጥ እንዳይኖሩ በከተማዋ ውስጥ ሲዳሚኛ እንዳይነገሩ ባህላችን ተገፍትሮ ከገዛ ወገኑ እንዲርቅ ተገዷል ይላሉ :: ኃ /ማሪያም ደሳለኝ ከ 6 ዐመት በፊት የሲዳማ ተወላጅ የሆነውን የቀድሞ የደቡብ ፕሬዚዳንት አባተ ኪሾን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በገዛ ፊርማው ከሥልጣን አባሮ በወንበሩ ላይ ጉብ ብሎ ፕሬዚዳንት እንደሆነ ይታወሳል :: በጊዜው በተነሳውም ረብሻ የ 121 ሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ወንጀለኛው ኃይለማሪያም ፕሮሞት ተደርጎ ላሁኑ ቦታ እንደበቃ ይታወቃል :: አሁን ደግሞ የክልሉ መደበኛ ስብስባ ሲደረግ የሲዳማ ተወካዮች ሁሉም ባንድ ቃል መብታችን ይከበርልን ብለው ሲጠይቁ አምባገነኑ ኃይለማሪያም ይህን ጥያቄ ደጋግማቹ የምታነሱ ከሆነ አዋሳ ይገባናል ካላችሁ የደቡብ ዋና ከተማ ወደ ራሴ ትውልድ ቦታ ወላይታ ሶዶ ይሆናል ብሎ አረፈው ::         This message expresses the views and opinions

በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገለጸ

New በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገልጿል:: በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰላማዊ ሰልፍኞ የክልል ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከሶስት ቀናት ባሃላ ተመሳሳይ የክልል ጥያቄ ሰልፍ በሃዋሳ ለማካሄድ ታስቧል:: በዛሬው እለት በሲዳማ ዞን በጭሬ ወረዳ በጭሬ ኩንቡልታ፣ በበንሳ፣ሁላ እና በጠጥቻ የክልል ጥያቄ ባነሱ ሰዎች የተካሄዱ ሰልፎች ያለምንም ግጭት በሰላም መጠናቀቃቸው ተገልጿል:: ዴኢህደን/ ኢህኣዴግ የሃዋሳን ከተማ በኮታ ለማስተዳዳር በሚል ያቀረበውን ኣማራጭ  ሀሳብ በመቃወም የተጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ ተቀጣጥሎ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ያለ ኮታ የማስተዳደር መብት ጥያቄነት ኣልፎ ክልል ይገባኛል ጥያቄ በመሆኑ በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ፍጥሯል:: በየኣስር ኣመቱ በመንግስት ኣካላት የምነሳውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ሃሳብ የሰለቻቸው የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የክልል ጥያቄ ለማንሳት መገደዳቸው ተገልጿል:: በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ የተቀጣጠለውን የክልል ጥያቄ ለመቀልበስ የግዥው ፓርቲ ኣባላት ወይም ካድሬዎች ህዝቡን እንዲያወያዩ ወደየ ወረዳዎች በመላክ ላይ ሲሆን፥ የወረዳዎቹ ህዝብ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ መምጣቻቸውን በመጠባባቅ ላይ ነው ተብሏል:: በሲዳማ ዞን ውስጥ በኣንድ ሳምንት ጊዜ  ውስጥ ካጫፍ እስከ ጫፍ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ መንግስትን ግራ ያጋባው ሲሆን እስከ ኣሁን የንቅናቄው መሪዎች ተለይተው ኣለማቻወቃቸው ሁኔታውን ኣስቸጋሪ እንዳደረገው እየተነገረ ነው:: በሌሎች የዞኑ ወረዳዎች እየተደረጉ ያሉ የክልል ጥያቄ ሰልፎች በሚቀጥለ ሶስት ቀናት ውስጥ

በሲዳማ ዞን በአለታ ጭኮ ከተማ በተደረገው ተቃውሞ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

Image
ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ተቃውሞው የተነሳው ከአዋሳ እጣ ፋንታ ጋር በተያያዘ ነው። የኢሳት ምንጮች እንደተናገሩት በአለታ ጭኮ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ፖሊስ የታረደ ሲሆን ሁለት ነዋሪዎች በፖሊሶች ሳይገደሉ አልቀረም አራት ተማሪዎችም በጽኑ ቆስለዋል። በመላው ሲዳማ ዞን ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ የገለጠው ዘጋቢአችን በነገው እለት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ሊነሳ ይችላል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው። የመከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸውም ታውቋል። ከትናንት ጀምሮ “አዋሳ ለወላይታ አትሰጥም” የሚል በራሪ ወረቀት ሲበተን እንደነበር የአይን እማኞች ገልጠዋል። አንድ የአዋሳ ነዋሪ በከተማው ያለው ውጥረት አስፈሪ እንደሆነና በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊነሳ እንደሚችል ተናግሯል። አዋሳ ከተማን ወደ ፌደራል መንግስቱ ለማዞር በፌደራል መንግስት እና በሲዳማ ዞን ባለስልጣናት መካከል ባለፈው ሳምንት ውይይት ተደርጎ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ከ10 አመታት በፊት በአዋሳ በተመሳሳይ ምክንያት በተነሳ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። http://www.ethsat.com

ዛሬ ኣለታ ወንዶ ወረዳ ጩኮ ከተማ ላይ በሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ እና የሲዳማ የክልል ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረው ግጭት ኣራት ተማሪዎች መቁሰላቸውን እና ሁለት ደግሞ መሞታቸው እየተነገረ ነው

New ዛሬ ኣለታ ወንዶ ወረዳ ጩኮ ከተማ ላይ በሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ እና የሲዳማ የክልል ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረው ግጭት ኣራት ተማሪዎች መቁሰላቸውን እና ሁለት ደግሞ መሞታቸው እየተነገረ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: ልጆቻቸው ላጡት እና ልጆቻቸው ለተጎዱባቸው ቤተሰቦች የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን:: በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እናሳውቃለን::