ኪንናማ
New ኪ ን ናማ ት ረ ካ በአበበ ከበደ ኣርትኦት በመልካም ኪ ን ናማ ብዙ ፍየሎች የነበሯት የሲዳማ እረኛ ልጃገረድ ነበረች፡፡ ኪ ን ናማ ትኖር የነበረው በአንድ በጣም ግዙፍ የአለት መዝግያ በነበረው ትልቅ ዋሻ ውስጥ ነበር፡፡ ፍየሎቿን ወደ ግጦሽ ይዛ ስትሄድ ሁለት ከባድ ችግሮች ነበሩባት፡፡ አንደኛው ሁልግዜ ልጆቿን እየሰረቀ የሚያስቸግራት ነብር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሁልጊዜ የሚያስቸግራት ጅብ ነበር፡፡ ነገር ግን ዋነኛው ጠላቷ ነብሩ ስለነበረ ሁልጊዜ ልታሞኘው ትሞክር ነበር፡፡ ጠዋት ትነሳና ፍየሎቿን ከዋሻ ውስጥ “ግዙፉ ዋሻዬ ሆይ ! በርህን ክፈተው !” እያለች የዋሻው መዝጊያ አለት ሲከፈት ልጆቿን ይዛ ትወጣለች፡፡ ከዚያም በግሩም ድምጿ ጮክ ብላ “ዛሬ ፍየሎቼን ወደ ዲጋሬ ይዣቸው እሄዳለሁ፡፡” ብላ ትናገራለች፡፡ ሆኖም ወደ ዲጋሬ ሳይሆን ወደ ተመዴ ትሄዳለች፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ ጠዋት ትነሳና “ዛሬ ወደ ተመዴ ነው የምሄደው፡፡” ብላ ተናግራ ወደ ዲጋሬ ትሄዳለች፡፡ እናም በየቀኑ በዚህ ዓይነት ነብሩን እያታለለች ፋጎ ፋጋግ “ግዙፉ ዋሻዬ ሆይ ! በርህን ክፈት፡፡ ክቦ ክቢብ ግዙፉ ዋሻዬ ሆይ ! በርህን ዝጋ፡፡” እያለች ትኖር ነበር፡፡ ሁልጊዜም ማንም እንዳይሰማት በማድረግ ስትኖር ነብሩ የሚያማምሩትን ልጆቿን እያየ በመጎምዠት እርሷንም እንዴት ሊያታልላት እንደሚችል ያስብ ነበር፡፡ ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን ነብሩ ከዋሻው አናት ላይ ካለ ዛፍ ላይ ተደብቆ ሳለ ኪና ን ማ ከዋሻው ወጥታ ስትመለከት ማንንም ስላላየች በተለመደው ቆንጆ የድምጽ ቃና ጮክ ብላ “የኔ ዋሻ ሆይ ! በርህን ዝጋ !” ካለችው በኋላ ፍየሎቿን ይዛ ሄደች፡፡ በዚህ ጊዜ