የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህግ ተማሪዎች የአምሳለ ፍርድ ቤት የክርክር ውድድር የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ
አዋሳ, ሚያዝያ 29 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - ሰብአዊ መብት እንዲጎለብት ከትምህርት ሚኒስቴርና ከ18 ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለሶስት ቀናት ያዘጋጀው 4ኛ ብሄራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህግ ተማሪዎች የአምሳለ ፍርድ ቤት የክርክር ውድድር ትናንት ተጠናቋል፡፡ በውድድሩም የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡ የኮሚሽኑ የሴቶችና ህጻናት ኮሚሽነር ወይዘሮ አስማሩ በሪሁን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሰብኣዊ መብቶች በየደረጃው በሚገኙ የትምህር ተቋማት በስርዓተ ትምህርት እንዲካተት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው ተግባራዊ እንቅሳቃሴ ተጀምሯል፡፡ እንዲሁም ከ18 የህግ ትምህርት ከሚሰጡ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ በመደረሱ ከ110 በላይ ነጻ የህግ ማዕከላትን ከፍተው አቅም ለሌላቸው በተለይም ለሴቶች፣ ለህጻናት፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎችም የህብረተስብ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም የህግ ትምህርት ከሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የሰብአዊ መብት ግንዛቤን የማስፋት ስራዎች እየተከናወነ ከመሆኑም በላይ በህግ ተማሪዎች መካከል የአምሳለ ፍርድ ቤት የክርክር ውድድር በመቀሌ ፣ በጅማና በባህር ዳር ዩኒቨርስቲዎች አዘጋጅነት በተለያዩ ርዕሶች ላይ ላለፉት ሶስት አመታት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር " የባህል መብቶችና የሴቶች መብት " በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ መካሄዱንና በተለይ በሴቶች መብት ላይ ተማሪዎች መሰረታዊ ዕውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ መንገድ በማሳየት ለ