የኢጋድ አባል ሀገራት የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ሜካኒዝምን (ሲዋርን CEWARN) አቋቋመው እንቅስቃሴ ከጀመሩ ወዲህ በቀጣናው ድንበር ዘለል ግጭቶች እየቀነሱ መጥተዋል ተባለ፡፡
የኢጋድ አባል ሀገራት የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ሜካኒዝምን (ሲዋርን CEWARN) አቋቋመው እንቅስቃሴ ከጀመሩ ወዲህ በቀጣናው ድንበር ዘለል ግጭቶች እየቀነሱ መጥተዋል ተባለ፡፡የሜካኒዝሙ ጥረት በሀገራቱ መሀከል መተማመንና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ የመስራት ልምድ እንዲያዳብሩ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ገልጿል፡፡ ሜካኒዝሙ ለሚቀጥሉት 8 ዓመታት የሚመራበት አዲስ ስትራቴጂ በመንደፍ ላይ መሆኑን አመልክቷል፡፡የኢጋድ አባል ሀገራት በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚከሰቱት ድንበር ዘለል ግጭቶችን በማስወገድ አካባቢው አስተማማኝ ስላም ያለው የልማት ቀጠና ለማድረግ ነበር ከ9 ዓመታት በፊት የግጭት ቀድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ሜካኒዝምን ያቋቋሙት፡፡ ሜካኒዝሙ በሀገሪቱ የሚገኘውን የመነገስት መዋቅርና ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ግጭቶች እንዳይከሰቱ ከተሰከቱም በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ሲሰራ ቆይቷል፡፡በኢትዮጵያ የሜካኒዝሙ የካራሞጃና የሶማሊያ ቅርንጫፎች ሜካኒዝሙ ለቀጣዩቹ 9 ዓመታት የሚመራበት አዲስ ስትራቴጂ ለመንደፍ በሀዋሣ ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ እንደተገለፀውም በሁሉም ሀገራት በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እየሰፈነባቸው መጥቷል፡፡ የሜካኒዝሙ ዳይሬክተር ዶክተር ማርቲን ኪማኒ እንዳሉት በሀገሪቱ እስከ ቀበሌ ደረጃ መዋቅሮችን በመዘርጋት ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ድንበር ተሻጋሪ ግጭቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለመከላከል ተችሏል፡፡በቀጣናው በተፈጥሮ ሀብት፣ በግጦሽ፣ በውሃ፣በባህላዊ ተፅዕኖና ሌሎች ምክንያቶች አልፎ አልፎ ግጭቶች ሲከሰቱም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ተፈጥዋል ብለዋል፡፡ አባል ሀገራቱ ግጭቱን ለማስወገድ ፈጣን የመረጀ ልውውጥና የጋራ አፈተት ስልቶች ማዳበራ