Posts

በማንኛውም ቦታ የሚለበስ የሲዳማ ባህላዊ ልብስ

Image
የፋሽን ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ ከመጣበት ዘመን አንስቶ በርካታ የአለባበስ ልምዶችም አብረው ተፈጥረዋል። በተለይ በአውሮፓውያኑ አካባቢ አንድን ልብስ ከመምረጣቸው በፊት ለምን ጉዳይ እንደሚለብሱትና በምን ወቅት እንደሚያዘወትሩት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአገራችን የሚዘጋጁ ባህላዊ አልባሳት ጊዜና ቦታ ተመርጦላቸው እንዲለብሱ እየሆነ ነው። ብዙ ጊዜ የባህላዊ አልባሳት በበዓላት ቀን ላይ ብቻ እንዲለበሱ የተወሰኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን የባህላዊ አልባሳትን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት በተለያዩ ወቅቶች በማንኛውም ቦታ እንዲለበሱ እየደተረገ ነው። በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻና ማከፋፈያም ከአገራችን አልፎ እስከ ውጭ አገር ድረስ ባህላዊውን አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት ዕውቅናን እያተረፈ መጥቷል፡፡  ዋና ሥራ አስኪያጇ ወይዘሮ አበባ ዘነበር እንደ ገለጹልን፣ የባህላዊ አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በመዘጋጀታቸው ፈላጊያቸው መብዛቱን ነው። ለዛሬ ሊያስተዋውቁን የወደዱት በሲዳማ የባህል ጨርቅ የሚሠራውን ሸሚዝ ወይም የሱሪ አላባሽ ነው። ልብሱ የሚሠራው የሲዳማ ባህላዊ አልባሳት ከሚጠቀምባቸው ሦስት ቀለሞች አንዱ በሆነው በቀይ ቀለም ነው። የጨርቁ ምርት ሳባ ይባላል። አሠራሩ ብዙዎች እንዲጠቀሙበት በማሰብ በአፍሪካውያን አለባበስ ዲዛይን ተደርጓል። ሰፋ ያለና ለሁሉም ሰው እንዲያመች ተደርጐ ተዘጋጅቷል። ሸሚዙን ወፍራምም ሆነ ቀጭን ሰው፤ ወንድም ሆነ ሴት በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊለብሰው ይችላል። «ወንዶች ከመረጡት ሱሪ ጋር ሴቶች ደግሞ በጂንስና በታይት ቢለብሱት የበለጠ ውበታቸውን ያጐላላቸዋል» የምትለው ዲዛይነር ወይዘሮ አበባ፣ በተለይ በሙቀት ወቅት ቢለበስ የበለጠ ምቾትን ይሰ

በሲዳማ ዞን የቦርቻ ወዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የወባ በሽታን በመከላከልና በመቆጣር ረገድ የአንድ ለእምስት ትስስር ስኬታማ ውጤት እያስገኘ መሆኑ አስታወቀ:

በሲዳማ ዞን የቦርቻ ወዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የወባ በሽታን በመከላከልና በመቆጣር ረገድ የአንድ ለእምስት ትስስር ስኬታማ ውጤት እያስገኘ መሆኑ አስታወቀ::ጽህፈት ቤቱ ሰሞኑን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጡ ቀበሌያትን ባስመረቀበት ወቅት የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ዱባለ ባራሳ እንዳስታወቁት በወረዳው በሚገኙ 42 ቀበሌያት በአንድ ለአምስት ትስስር በተደረገው ጥረት 16ቱን ጤና ፖኬጅ ተግባራዊ በማድረግ አበረታች ውጤት ማየት ተችሏል:: ለውጤቱ መገኘትም የጤና ልማት ሠራዊት በአንድ ለአምስት ትስስር መሠረታዊ የግል ንጽህና፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ፣ የቤተሰብ ጤና አገልግሎት እንዲሁም የወባ በሽታን በመከላከልና በመቆጣጠር ቀዳሚ ተዋናይ መሆናቸውን ተናግረዋል:: በተይም የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ፣በጎ መልክተኞችና የጤና ባለሙያዎች ድርሻ የጎላ መሆኑን ኃላፊው ገልፀው በጥረቱም 9 ሺህ ሞዴል ቤተሰብ መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል:: የዞኑ በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኢማላ ላማቻ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ግንባር ቀደም ተዋናይና በማህበረሰብ ውይይት ንቁ ተሳትፉ በመሆን ጤናውን ማጐልበት እንደሚገባው የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንደዘገበው::

በሲዳማ ዞን ሐዋሣ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የሐዋሳ ሐይቅንና ጥልቀት የሌላቸው ጉድጓዶችን በመጠቀም ከ800 በላይ ሄክታር መሬት በአነስተኛ መስኖ አልምተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ:

በሲዳማ ዞን ሐዋሣ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች የሐዋሳ ሐይቅንና ጥልቀት የሌላቸው ጉድጓዶችን በመጠቀም ከ800 በላይ ሄክታር መሬት በአነስተኛ መስኖ አልምተው ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ::ተጠቃሚ አርሶ አደሮቹ እንደተናገሩት በአመት 4 ጊዜ የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችንና ወቅታዊ ሰብሎችን በማምረት እስከ 1 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ችለዋል:: የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ሻሾ እንደገለጹት በመስኖው ልማት ከ2ሺ 500 በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል::በመንግሥት ድጋፍ የተገኙትን 20 የውሃ መሣቢያ ሞተሮችን በ1ለ5 ትስስር ለተደራጁ አርሶ አደሮች በማከፋፈል ዓመቱን በሙሉ ዝናብ ሳይጠብቁ በማምረት ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል:: አርሶ አደሮቹ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ሽንኩርትና ቃሪያ ከሚያለሙዋቸው ምርቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል::በአሁኑ ጊዜ ማሳ ላይ ከሚገኘው ምርትም ከ1 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ክፍሌ ገልፀዋል ሲል የሲዳማ ዞን የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ ዘግቧል :: Back

በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ አባል ሀገራት አዲስ እቅድ ላይ የሚነጋገር አውደ ጥናት በሀዋሳ ተጀመረ

Image
New አዋሳ, ሚያዝያ 23 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ አባል ሀገራት ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ስልት ስትራቴጂክ ዕቅድን ለማዳበር ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዋጾኦ እያበረከተች መሆኗ ተገለጸ፡፡ በስትራቴጅክ ዕቅዱ ላይ ለመምከርና ሀሳብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ትናንት በሃዋሳ ከተማ ሲጀመር የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ እንደገለጹት በአፍሪካ ቀንድ በተለይ በኢጋድ አባል ሀገራት የሚከሰቱ ግጭቶች ለልማት፣ለመልካም አስተዳዳርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት አሉታዊ ተጽልኖና ጫና እያሳረፉበት እንዳለ ይታወቃል፡፡ የግጭቶች መንስኤ እንደ ሰዎች ፍላጎትና ባህሪ ተለዋዋጭ መሆናቸውን ገልጸው ችግሮቹ በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገር በአርብቶ አደር አካባቢ ለጥሎሽ የሚጠየቀውን ከብት ከሌላ ጎሳ ለማምጣት መሞከር፣ውሃና ግጦሽ ፍለጋ ፣የተመጣጠነ የሀብት ጉድለት የመሳሳሉ ችግሮች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለኢትዮጵያና ለቀሩትም የኢጋድ አባል ሀገራት ትልቁ ጠላት ድህነት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሚከሰቱ ግጭቶች ከድህነት ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ችግሮቹን ከምንጫቸው ለማድረቅ እንደያአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ህብረተሰቡን ባሳተፈ ሁኔታ አዲስ የጋራ ስትራቴጂክ ዕቅድ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቀደም ሲልም ከሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በመተባበር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ስልት እንዲቋቋም ግምባር ቀደም ሚና በመጫወት ድንበር ተሻጋሪ የአርብቶ አደር ግጭቶችን በመከላከልና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ስትንቀሳቀስ መቆየቷን ተናግረዋል፡፡ ላለፉት አምስት አመታት የቆየው ፕሮግራም በቅ

Coffee processing in Sidama, Ethiopia

Image
http://www.firstpost.com/topic/place/vietnam-coffee-processing-in-sidama-ethiopia-video-Z6dCWkYVNpw-270-7.html