በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ አባል ሀገራት አዲስ እቅድ ላይ የሚነጋገር አውደ ጥናት በሀዋሳ ተጀመረ
New አዋሳ, ሚያዝያ 23 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት/ኢጋድ/ አባል ሀገራት ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ስልት ስትራቴጂክ ዕቅድን ለማዳበር ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዋጾኦ እያበረከተች መሆኗ ተገለጸ፡፡ በስትራቴጅክ ዕቅዱ ላይ ለመምከርና ሀሳብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ትናንት በሃዋሳ ከተማ ሲጀመር የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ እንደገለጹት በአፍሪካ ቀንድ በተለይ በኢጋድ አባል ሀገራት የሚከሰቱ ግጭቶች ለልማት፣ለመልካም አስተዳዳርና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት አሉታዊ ተጽልኖና ጫና እያሳረፉበት እንዳለ ይታወቃል፡፡ የግጭቶች መንስኤ እንደ ሰዎች ፍላጎትና ባህሪ ተለዋዋጭ መሆናቸውን ገልጸው ችግሮቹ በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገር በአርብቶ አደር አካባቢ ለጥሎሽ የሚጠየቀውን ከብት ከሌላ ጎሳ ለማምጣት መሞከር፣ውሃና ግጦሽ ፍለጋ ፣የተመጣጠነ የሀብት ጉድለት የመሳሳሉ ችግሮች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለኢትዮጵያና ለቀሩትም የኢጋድ አባል ሀገራት ትልቁ ጠላት ድህነት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የሚከሰቱ ግጭቶች ከድህነት ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ችግሮቹን ከምንጫቸው ለማድረቅ እንደያአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ህብረተሰቡን ባሳተፈ ሁኔታ አዲስ የጋራ ስትራቴጂክ ዕቅድ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቀደም ሲልም ከሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በመተባበር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና አፋጣኝ ምላሽ ስልት እንዲቋቋም ግምባር ቀደም ሚና በመጫወት ድንበር ተሻጋሪ የአርብቶ አደር ግጭቶችን በመከላከልና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ስትንቀሳቀስ መቆየቷን ተናግረዋል፡፡ ላለፉት አምስት አመታት የቆየው ፕሮግራም በቅ