Posts

በሀዋሣ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ መሠረታዊ ማህበራት ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገብ መቻላቸው ተገለፀ::

Image
በሀዋሣ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ መሠረታዊ ማህበራት ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማስመዝገብ መቻላቸው ተገለፀ::የወረዳው የግብይትና ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት እንዳለው በ23 ቀበሌያት የተቋቋሙት ማህበራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቱን በማገዝ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው:: የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ ማርቆስ ማህበራቱ በሁለገብ መሠረታዊ ህብረት ስራ፣ በወጣት፣ በገንዘብ ቁጠባና ብድር እንዲሁም በወተትና የወተት ተዋፅኦ፣ በኃይድሮ ኤሌክትሪክና ሶላር ማህበራት የተቋቋሙ መሆናቸውን ተናግረዋል::መስኖ፣ ማዕድንና የደን ልማት ቀሪዎቹ ማህበራቱ የተደራጁባቸው መስኮች መሆናቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል:: የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮንን ወላንሳ በበኩላቸው ህብረት ስራ ማህበራት የነበሩባቸውን የአመለካከትና ግንዛቤ ችግር ቀርፈው ችግር ፈቺ እየሆኑ መምጣታቸውን መናገራቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/08MiyaTextN104.html

በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ 16ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ተግባራዊ ያደረጉ 228 አባወራዎችና እማወራዎች ማስመረቁን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ::

Image
በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ 16ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ተግባራዊ ያደረጉ 228 አባወራዎችና እማወራዎች ማስመረቁን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ::የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አኔቦ አንዳሉት በጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም የግልና የአካባቢ ንጽህናን፣ የቤተሰብ ጤና ክብካቤንና የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር በቤተሰብ ደረጃ እውን እንዲሆን መጠነ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል:: ርብርቡን ስኬታማ ለማድረግም በወረዳው የዛሬዎቹን ጨምሮ 38 ሺህ 459 አባወራና እማወራዎች መሰልጠናቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል::የዞኑ ጤና መምሪያ መከላከልና ጤና ማጎልበት ኦፊሰር አቶ ኢማላ ላሚቻ በበኩላቸው መንግስት የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የነደፈውን የጤና ፖሊሲ ስኬታማ ማድረግ ከተመራቂዎች የሚጠበቅ ተግባር ነው ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/08MiyaTextN304.html

በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በተያዘው የምርት ዘመን ከ171 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ::

Image
በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በተያዘው የምርት ዘመን ከ171 ሺህ  ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ:: የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ጋቤራ ለወረዳው ምክር ቤት 3ኛ ዙር 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ባቀረቡት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ምርቱ የተሰበሰበው በ6 ሺህ 5 መቶ 9ዐ ሄክታር መሬት ላይ ከተመረቱ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦሎቄና ከሌሎች ሰብሎች መሆኑን ገልፀዋል::በምርት ዘመኑ 625 ሺህ የቡና ችግኞች ለበልግ የተከላ ወቅት መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው በ156 ሄክታር መሬት ላይ የነበሩ ያረጁ የቡና ተክሎች ተጐንድለዋል::2ዐ ኩንታል የቡና ዘር መዘጋጀቱን ተናግረዋል:: በወረዳው የተሻሻሉ ምርጥ የከብት ዝሪያዎችን ለማርባት 82 ከብቶች በሰው ሠራሽ ዘዴ፣ 447 ደግሞ በኮርማ መዳቀላቸውን አውስተው የእንስሳት በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በተደረገው ጥረት ለ6 መቶ ከብቶች ክትባት መሰጠቱን ገለፀዋል::ሪፖርተራችን ካሳ ጀንቦላ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው:: http://www.smm.gov.et/_Text/08MiyaTextN604.html

በሀዋሣ ታቦር ክፍለ ከተማ የፋራ ቀበሌ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የምሳ ግብዣ አደረገ:

በሀዋሣ ታቦር ክፍለ ከተማ የፋራ ቀበሌ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የምሳ ግብዣ አደረገ::የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በልጉዳ ባሪሳ በዝግጅቱ ላይ እንዳሉት የሁላችንም የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነትና ኃላቀርነትን ለማሸነፍ በተሰማራንበት መስክ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል::በቀበሌው ከ47ዐ በላይ አረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ለምሳ ግብዣው በመጥራት በአሉን በጋራ ማክበር መቻላቸውን አስረድተዋል:: ድጋፍ ያደረጉ ባለሀብቶች በበኩላቸው አመት በዓልን ጠብቆ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር በዘላቂነት ህይወታቸውን ለመቀየር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተዋካይ አቶ አየለ ኪአ ቀበሌው እንደዚህ አይነት ዝግጅት በራሱ ተነሳሽነት ማካሄዱ የሚያመሰግነው መሆኑን ገልፀው፤ ሌሎችም አርአያነቱን ሊከተሉ እንደሚገባ አውስተዋል:: የፋራ ቀበሌ ከአመት በዓል ዝግጅቶች ባለፈ የችግረኛ ወገኖችን  ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ተገልጿል ሲል ባልደረባችን ወንድወሰን ሽመልስ ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/08MiyaTextN704.html

የሀዋሣ ግብርና ምርመር ማዕከል አዳዲስ የአኩሪ አተርና የባቄላ ዝርያዎችን መልቀቁን አስታወቀ::

የሀዋሣ  ግብርና ምርመር ማዕከል አዳዲስ የአኩሪ አተርና የባቄላ ዝርያዎችን መልቀቁን አስታወቀ::በብሔራዊ የዝሪያዎች አፅዳቂ ኮሚቴ ተገምግሞ የፀደቀው ሁለት የአኩሪ አተርና አንድ የባቄላ ዝርያዎች ሲሆን አስካሁን ከተለቀቁት ከ16 እስከ 21 ቀናት በመቅደም የሚደርሱ ናቸው::ዝርያዎቹ በተዘሩ በአማካኝ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ የሚደርሱ ናቸው:: በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ከፍተኛ ሲሆን ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ጭምር ማምራት እንደሚቻል ተገልጿል::ግኝቱ ለአርሶ አደሩ አዋጭ ከመሆኑም በተጨማሪ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግም ከምርምር ማዕከሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: http://www.smm.gov.et/_Text/08MiyaTextN904.html