በሀዋሣ ታቦር ክፍለ ከተማ የፋራ ቀበሌ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የምሳ ግብዣ አደረገ:
በሀዋሣ ታቦር ክፍለ ከተማ የፋራ ቀበሌ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የምሳ ግብዣ አደረገ::የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በልጉዳ ባሪሳ በዝግጅቱ ላይ እንዳሉት የሁላችንም የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነትና ኃላቀርነትን ለማሸነፍ በተሰማራንበት መስክ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል::በቀበሌው ከ47ዐ በላይ አረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ለምሳ ግብዣው በመጥራት በአሉን በጋራ ማክበር መቻላቸውን አስረድተዋል:: ድጋፍ ያደረጉ ባለሀብቶች በበኩላቸው አመት በዓልን ጠብቆ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር በዘላቂነት ህይወታቸውን ለመቀየር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተዋካይ አቶ አየለ ኪአ ቀበሌው እንደዚህ አይነት ዝግጅት በራሱ ተነሳሽነት ማካሄዱ የሚያመሰግነው መሆኑን ገልፀው፤ ሌሎችም አርአያነቱን ሊከተሉ እንደሚገባ አውስተዋል:: የፋራ ቀበሌ ከአመት በዓል ዝግጅቶች ባለፈ የችግረኛ ወገኖችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ተገልጿል ሲል ባልደረባችን ወንድወሰን ሽመልስ ዘግቧል:: http://www.smm.gov.et/_Text/08MiyaTextN704.html