Posts

በሲዳማ ዞን ይርጋአለም ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በሚበልጥ ገንዘብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡

በሲዳማ ዞን ይርጋአለም ከተማ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከስድስት መቶ ሺህ ብር በሚበልጥ ገንዘብ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ቦንድ ለመግዛት ቃል ገቡ፡፡ በከተማው በፎቶና ቪዲዮ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ናአሚን ፍረሕይወት በበኩላቸው የ5 ሺህ ብር ቦንድ ገዝተው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው ለማጠናቀቅ ቃል ገብተዋል፡፡ በሌላም በኩል በሸቀጣሸቀጥ ንግድ ስራ የተሰማሩት ወ/ሮ አበባየሁ ለገሰ የ3 ሺህ ብር ቦንድ የገዙ ሲሆን አምስት መቶ ብር ስጦታ መለገሳቸውንም ገልፀዋል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ቦልካ ጉዳዩን አስመልክተው እንደገለፁት የግድቡን ስራ ከዳር ለማድረስ የከተማው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በተለያዩ ጊዜያት ሰፊ የገንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በየጊዜው በተደረገው ውይይት በከተማው የሚኖሩ ነጋዴዎች፣ የሐይማኖት ተቋማትና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባታቸውን የገለፁት ከንቲባው በቃላቸው መሰረት ግዥውን በመፈፀም ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተራችን መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ እንደዘገበው፡፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ መግዛታቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ መግዛታቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለገሰ ላሺ እንደገለፁት በቦንድ ግዥው የተሳተፉት በወረዳው 33 የገጠር ቀበሌያትና 4 ከተሞች የሚኖሩ የተለያዩ የእምነት ተቋማት፣ እድሮች እንዲሁም ሞዴል አርሶ አደሮችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ በተለይም የተፈሪ ኬላ ከተማ ነዋሪዎች የ41 ሺህ 45ዐ ብር ቦንድ እጅ በእጅ ክፍያ በመግዛት ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የወረዳው ደህኢዴን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ዘዳግም በበኩላቸው ህብረተሰቡ ከ5ዐ እስከ 1ዐዐዐ ብር ዋጋ ያለውን ቦንድ ግዥ መፈፀሙን ገልፀዋል ሲል የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/05MiyaTextN704.html

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በህዝብ የሚመራ የጤና ልማት ስራ እያከናወነ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በህዝብ የሚመራ የጤና ልማት ስራ እያከናወነ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ለዚሁም ጽህፈት ቤቱ በ16ቱ ጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጆች ዙሪያ አዲስ የትግበራ ስልት በመንደፍ ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ለባለሙያዎችና ለሱፐርቫይዘሮች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ በጽህፈት ቤቱ በሽታ መከላከልና ጤና ማጐልበት ዋና ስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ማቴዎስ ማልጌ በወረዳው የትግበራ ስልቱን ውጤታማ ለማድረግ በሁሉም ቀበሌያት የጤና ልማት ሰራዊት መገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዋናነትም የእናቶችና ህፃናት ሞትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ጠቁመው በዚሁ መሰረት ነፍሰጡር እናቶች በወረዳው በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ጽሀፈት ቤት እንደዘገበው፡፡

ባለፉት 7 ወራት ከልዩ ልዩ የገቢ አርእስቶች ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ባለፉት 7 ወራት ከልዩ ልዩ የገቢ አርእስቶች ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡አፈፃፀሙ ካለፈው ዓመት ብልጫ ያለው መሆኑንም ገልፀዋል፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ እንዳሉት ከመደበኛ ገቢ 116 ሚሊዮን ከማዘጋጃ ቤቶች ደግሞ 12 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ በታክስ ክፍያ ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ማደግ ለገቢው መጨመር አስተዋፅኦው የጐላ እንደነበር መግለፃቸውንም የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25MegTextN404.html

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ከ33 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ እየተሰራ ነው፡

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ከ33 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ እየተሰራ ነው፡፡በወረዳው በመገንባትና በመጠገን ላይ የሚገኙት መንገዶች ሁሉም ቀበሌያት ከወረዳዋ ዋና ከተማ የሚያገናኙ ናቸው፡፡የወረዳው የመንገዶችና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ድንቅነህ አለማየሁ ግንባታዎቹ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሱታል፡፡ በተለይ ወረዳውን ከኦሮሚያ ክልል የሚያገናኘው ሔማ የተባለው የ18 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲጠናቀቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የላቀ እንደሆነ መግለፃቸውንም የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25MegTextN504.html