የሀዋሳ ከተማን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ የቱሪዝም ማዕከል ለማደረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነዋሪዎች ገለጹ
የሀዋሳ ከተማን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ነዋሪዎች ከከተማው አስተዳደሩ ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡ የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ የመንግስት ሰራተኞችና የንግዱ ማህበረሰብ ጨምሮ በከተማው ስምንቱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የጽዳትና የተተከሉ የዛፍ ችግኞችን የመንከባከብ የስራ ዘመቻ ትናንት ተካሄዷል፡፡ የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍ በየክፍለ ከተማው ተዘዋውረው በስራው የተሳተፉትን ነዋሪዎች አበረታትዋል፡፡ "እያንዳንዱ አካባቢውን ካጸዳ ከተማዋ የጸዳች ትሆናለች" በሚል መርህ ትናንት ለግማሽ ቀን በተካሄደው የስራ ዘመቻ ከተሳተፉት መካከል በባህል አዳራሽ ክፍለ ከተማ የሀረር ቀበሌ ነዋሪው ወጣት ሙሉቀን አለማየሁ በሰጠው አስተያየት አካባቢቸውን ከቆሻሻና ከብክለት ለመከለካል ከሰፈር ጓደኞቹና ነዋሪው ጋር በራሳቸው ተነሳሽነት የጽዳት ዘመቻውን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ብቻ ሳይሆን በቋሚነት በየሳምንቱ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ አካባቢያቸውን ከፍሳሽና ከደረቅ ቆሻሻ ማዕዳት ለጤናቸው ብሎም ለሀዋሳ ውበትና አረንጓዴ ልማት የላቀ አስተዋጾኦ እንዳለው በመገንዘብ በቀጣይም ከከተማው አስተዳደርና ማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የዚሁ ክፍለ ከተማና ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ አሰለፈች በቀለ በበኩላቸው ሀዋሳ ያላትን ጽዳትና ውበት ለማስጠበቅ ጽዳትን ከቤታቸውና ከመንደራቸው በመጀመር እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የመሃል ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02 ነዋሪ ወይዘሮ እናኑ መዘምር በሰጡት አስተያየት ጽዳት ለጤንነትና ለከተማ ውበት ወሣኝ መሆኑን በመረዳት ቆሻሻን ከአካባ