Posts

ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡

ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሊዮን ማቴዎስ ለም/ቤቱ በእጩነት ያቀረቧቸው ካቢኔዎች የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ የከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በም/ቤቱ ሙሉ ድምፅ መመረጣቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ም/ቤቱ ለቀጣይ ወራት የዞን ማዕከል፣ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም ለሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ የሚጠቀሙበትን ከ32 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ በጀት ማፅደቁ ተመልክቷል፡፡ በም/ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሲምቦ ሽብሩ የተጨማሪ በጀት ደንብ ሰነድ ለም/ቤቱ አባላት ሲያቀርቡ ከተመደበው ተጨማሪ በጀት ከ6 ነጥብ 9 በላይ ሚሊዮን በ2ዐዐ3 የበጀት አመት በተለያዩ ምክንያት ስራ ላይ ያልዋለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ቀሪው ከ25 ነጥብ 9 በ ላይ ሚሊዮን በጀት ደግሞ የዞኑ ማዕከል፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከእቅዳቸው በላይ የሰበሰቡት መሆኑን አቶ ሱምቦ መጠቆማቸውን የዘገበው የዞኑ ባህል ቱሪዝም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ተወካይ አቶ ባንታየሁ ጉዲሳ አንደገለፁት በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮግራም እቅድ ከተያዙት 17 ምንጮች የ12ቱ ግንባታ 87 በመቶ ተጠናቋል፡፡ የግንባታው ወጪም 85 በመቶ ትንሳኤና ብርሃን በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን 15 በመቶ በወረዳው በጀት ይሸፈናል፡፡ግንባታው ሲጠናቀቅ የወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 38 ነጥብ 8 በመቶ ይደርሳል ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ Source: http://www.smm.gov.et/_Text/20MegTextN404.html

የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Image
የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አነቦ ባለፉት ወራት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ለ2 ሺህ 985 እናቶች የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ምርመራ እንዳደረገላቸውም ተናግረዋል፡፡ 14 ሺህ 49ዐ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተው ቁጥራቸው በተጨማሪም እናቶች በባለሙያ የተደገፈ የወሊድ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በአንፃሩ የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በተደረገው ርብርብ 3 ሺህ 383 ህፃናት የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከል ክትባት ማግኘታቸው መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡ ምንጭ:  http://www.smm.gov.et/_Text/16MegTextN304.html

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዘለቀ በላይነህ እንደገለፁት ህብረተሰቡን ከውሃ ወሊድ በሽታ ለመታደግና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የዘጠኝ አነስተኛና መለስተኛ የውሃ ተቋማት ግንባታዎች እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ከሚገኙ መካከልም 1 የጥልቅና 3 መለስተኛ የውሃ ጉድጓድ እንዲሁም 5 የአዳዲስ ምንጮች ግንባታ እንደሚገኝ አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ሲል መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በመጠጥ ውኃ እጥረት መቸገራቸውን የመጆ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በመጠጥ ውኃ እጥረት መቸገራቸውን የመጆ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡በተከሰተው የውሀ እጥረት የተነሳ ለህብረተሰቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት ለመስጠት መቸገሩን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አመልክቷል፡፡ የወረዳው ውኃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት በበኩሉ ችግሩ እስከ ሚያዚያ 3ዐ ባለው ጊዜ ይፈታል ብሏል፡፡የመጆ ከተማ የአሮሬሳ ወረዳ ዋና ከተማ ስትሆን ዙሪያዋ 8 በሚበልጡ የተፈጥሮ ምንጮች የተከበበች ናት፡፡ ይሁንና ምንጮቹ በበጋ ወራት መድረቅ በመጀመራቸው በተለይም ካለፈው አመት ጀምሮ ለከፍተኛ የመጠጥ ውኃ ችግር መጋለጣቸውን ነው ነዋሪዎች የተናገሩት፡፡አንዳንዶቹ እንደሚሉት በውኃ ማድያ ወረፋ ለመያዝ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ ከቤት ስለሚወጡ ዘረፋና ድብደባ እንደሚደርስባቸውና ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚጋለጡ ተናግረዋል፡፡ የወረፋውን ሰልፍ ይዘው እስከ እኩለ ቀን ድረስ እንደሚቆዩ የገለፁት ነዋሪዎቹ በዚህም የተነሳ በረሃብ እንደሚጐዱና ወረፋው ሳይደርሳቸው ሲቀር ደግሞ በዐ.5ዐ ሣንቲም የሚገዛውን ባለ 2ዐ ሊትር አንድ ጀሪካን ውኃ ከአትራፊዎች ከ5 እስከ 6 ብር ለመግዛት እንደገደዳለን ብለዋል፡፡ እነዚህ አትራፊዎች ከከተማው በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኘውና ጪጩ ከተባለ ወንዝ ንጽህናው ያልተጠበቀ ውኃ ቀድተው ስለሚሸጡላቸው ለተለያዩ ውኃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጡ እንደሚገኙ አስድተዋል፡፡የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በበኩሉ በከተማው በተፈጠረው የውኃ ችግር የተነሳ ለህብረተሰቡ ንፅህናውን የተጠበቀ የጤና አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን አመልከቷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙንጣሽ ብርሃኑ እንዳሉት በከተማውና በአካባቢው የሚገኙ 4 ጤና ጣቢያዎች ከመኝታና ከመፀዳጃ አገልግሎቶች አንስቶ ለህሙማኑ ደረጃውን የጠበቀ የጤና አ