Posts

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ተወካይ አቶ ባንታየሁ ጉዲሳ አንደገለፁት በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮግራም እቅድ ከተያዙት 17 ምንጮች የ12ቱ ግንባታ 87 በመቶ ተጠናቋል፡፡ የግንባታው ወጪም 85 በመቶ ትንሳኤና ብርሃን በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን 15 በመቶ በወረዳው በጀት ይሸፈናል፡፡ግንባታው ሲጠናቀቅ የወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 38 ነጥብ 8 በመቶ ይደርሳል ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ Source: http://www.smm.gov.et/_Text/20MegTextN404.html

የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

Image
የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አነቦ ባለፉት ወራት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ለ2 ሺህ 985 እናቶች የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ምርመራ እንዳደረገላቸውም ተናግረዋል፡፡ 14 ሺህ 49ዐ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተው ቁጥራቸው በተጨማሪም እናቶች በባለሙያ የተደገፈ የወሊድ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በአንፃሩ የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በተደረገው ርብርብ 3 ሺህ 383 ህፃናት የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከል ክትባት ማግኘታቸው መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡ ምንጭ:  http://www.smm.gov.et/_Text/16MegTextN304.html

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዘለቀ በላይነህ እንደገለፁት ህብረተሰቡን ከውሃ ወሊድ በሽታ ለመታደግና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የዘጠኝ አነስተኛና መለስተኛ የውሃ ተቋማት ግንባታዎች እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ከሚገኙ መካከልም 1 የጥልቅና 3 መለስተኛ የውሃ ጉድጓድ እንዲሁም 5 የአዳዲስ ምንጮች ግንባታ እንደሚገኝ አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ሲል መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በመጠጥ ውኃ እጥረት መቸገራቸውን የመጆ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በመጠጥ ውኃ እጥረት መቸገራቸውን የመጆ ከተማ ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡በተከሰተው የውሀ እጥረት የተነሳ ለህብረተሰቡ የተሟላ የጤና አገልግሎት ለመስጠት መቸገሩን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አመልክቷል፡፡ የወረዳው ውኃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት በበኩሉ ችግሩ እስከ ሚያዚያ 3ዐ ባለው ጊዜ ይፈታል ብሏል፡፡የመጆ ከተማ የአሮሬሳ ወረዳ ዋና ከተማ ስትሆን ዙሪያዋ 8 በሚበልጡ የተፈጥሮ ምንጮች የተከበበች ናት፡፡ ይሁንና ምንጮቹ በበጋ ወራት መድረቅ በመጀመራቸው በተለይም ካለፈው አመት ጀምሮ ለከፍተኛ የመጠጥ ውኃ ችግር መጋለጣቸውን ነው ነዋሪዎች የተናገሩት፡፡አንዳንዶቹ እንደሚሉት በውኃ ማድያ ወረፋ ለመያዝ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ ከቤት ስለሚወጡ ዘረፋና ድብደባ እንደሚደርስባቸውና ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚጋለጡ ተናግረዋል፡፡ የወረፋውን ሰልፍ ይዘው እስከ እኩለ ቀን ድረስ እንደሚቆዩ የገለፁት ነዋሪዎቹ በዚህም የተነሳ በረሃብ እንደሚጐዱና ወረፋው ሳይደርሳቸው ሲቀር ደግሞ በዐ.5ዐ ሣንቲም የሚገዛውን ባለ 2ዐ ሊትር አንድ ጀሪካን ውኃ ከአትራፊዎች ከ5 እስከ 6 ብር ለመግዛት እንደገደዳለን ብለዋል፡፡ እነዚህ አትራፊዎች ከከተማው በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኘውና ጪጩ ከተባለ ወንዝ ንጽህናው ያልተጠበቀ ውኃ ቀድተው ስለሚሸጡላቸው ለተለያዩ ውኃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጡ እንደሚገኙ አስድተዋል፡፡የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በበኩሉ በከተማው በተፈጠረው የውኃ ችግር የተነሳ ለህብረተሰቡ ንፅህናውን የተጠበቀ የጤና አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን አመልከቷል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙንጣሽ ብርሃኑ እንዳሉት በከተማውና በአካባቢው የሚገኙ 4 ጤና ጣቢያዎች ከመኝታና ከመፀዳጃ አገልግሎቶች አንስቶ ለህሙማኑ ደረጃውን የጠበቀ የጤና አ

የዳዬ በንሳን ጨምሮ በደቡብ ክልል ከ263 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ ስድስት የቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ኮሌጆች ስራ ጀመሩ

አዋሳ, መጋቢት 20 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል ከ263 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተጀመሩ ስድስት የቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ኮሌጆች ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ቴክኒክ መያና ትምህርት ስልጠና ቢሮ ገለጸ፡፡ የኮሌጆቹ መገንባት በክልሉ ያሉት መሰል ኮሌጆች ብዛት ወደ 22 ያሳድገዋል ። በቢሮው የልማት ዕቅድ ፣ ዝግጅት፣ ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ኢዮብ አዳ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በ2002 ግንባታቸው ተጀምሮ ዘንድሮ የተጠናቀቁት ኮሌጆች በሳውላ ፣ በተርጫ ፣በጂንካ በሃላባ ፣ በወራቤና በዳዬ ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡ ለኮሌጆቹ የመምህራን ቅጥር በማከናወንና የውስጥ ድርጅት በማሟላት በአሁኑ ወቅት ከ6ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በአጫጭር ፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የስልጠና ፕሮግራም መጀመራቸውን አመልከተዋል፡፡ ኮሌጁቹ ከሚያሰለጥኑባቸዉ መስኮች መካከል ኮንስትራክሽን ፣ አውቶሞቲቨ ፣ ብረታብረት ፣ ኤሌክትሪክ ሲቲ ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጨርቃጨርቅና ቆዳ ቴክኖሎጂ እንደሚገኙባቸዉ የስራ ሂደቱ ባለቤት አስረድተዋል፡፡ ተቋማቱ በውስጣችው ቤተ መጻህፍት ፣ ቤተ ሙከራ ፣ የመማሪያ ክፍሎች ፣ ቢሮዎችና ሌሎችም ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚያገለግሉ ከ12 እስከ 13 ክፍሎች ማካተታቸወን ጠቁመው የግንባታቸው ወጪ ሙሉ በሙሉ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተቋማቱ መገንባት የህብረተሰቡንና የገበያው ፍላጎት መሰረት በማድረግ ውጤታማና የተቀናጀ ስልጠና በመስጠት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራላይ የሚሰማሩ ባለሙያዎች በብዛትና በጥራት በማፍራት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሳካት በተለይ ወደ ኢንዱስትሪው መር ልማት ለመሸጋገር ከፍተኛ