በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አስተዳደር ባለፈው ግማሽ የበጀት ዓመት በህብረተሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ፡
በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አስተዳደር ባለፈው ግማሽ የበጀት ዓመት በህብረተሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ፡፡የአስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን መንግስቱ እንደገፁት በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት 13ዐ የህዝብ አቤቱታዎች ለወረዳው አስተዳደር ቀርበው እልባት ላይ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶችና ጊዜያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰው ሠራሽ እግርና ባለ ብረት የአካል ድጋፍ ተገዝቶ አንደተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡የገንዘብ ችግር ያለባቸው 28 ሰዎች በይርጋለም ሆስፒታልና ጤና ጣቢያ ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን አቶ ተመስገን መግለፃቸውን የዘገበው የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው፡፡ Source: http://www.smm.gov.et/_Text/14MegTextN204.html