Posts

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ መኩሪያ እንደገለፁት ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውና የእቅዱ አፈፃፀም 98 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ለገቢው መገኘት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ክትትልና የቅርብ ድጋፍ ማድረጋቸው እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ጋር በቅንጅት መስራቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡በጽህፈት ቤቱ የገቢ አሰባሰብ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ፍስሐ በኬ በበኩላቸው ለባለሙያዎች በገቢ አሰባሰብ ስርአት የሚሰጠው የግልፀኝነት፣ የተጠያቂነትና የስነ ምግባር ትምህርት ስራቸውን በታማኝነት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ማለታቸውን የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ፡፡ ፡፡

ሀዋሳ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣውን የወላጅ አጥ ህፃናት ቁጥር ችግር ለመፍታታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የከተማው ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡

Image
ሀዋሳ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣውን የወላጅ አጥ ህፃናት ቁጥር ችግር ለመፍታታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የከተማው ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡፡መምሪያው ከተለያዩ የዕምነት ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገሪቱ አዲስ የሆነውን የፎስተር ኬር ኘሮግራም እንደሚጀምርም ገልጿል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ በሀገሪቷ በቅርቡ ተግባራዊ መደረግ የተጀመረውን የፎስተር ኬር ኘሮግራም ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ከቢታኒ ቤተክርስትያን ሰርቪስና ከርሆቦት ዴቨሎኘመንት ኤንድ ሳፓርቲንግ ኦርጋናይዜሽን ጋር በመተባበር ለወንጌላዊያን አብያተክርስትያናት መሪዎች መምሪያው ባዘጋጀው የምክክር ስብሰባ ላይ እንደተባለውም በከተማው የፎስተር ኘሮግራም ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሪት ስምረት ግርማ እንዳሉት ከ4 ወራት በኋላ የሚጀመረው የፎስተር እንክብካቤ በከተማው በህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ከ2ዐዐ በላይ ህፃናትን ጨምሮ በየደረጃው በጐዳና ላይ ያሉት ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ህፃናት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡በኘሮግራሙ ወላጅ አጥ ህፃናትና ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦች ድጋፍ ያገኛሉ ያሉት ወይዘሪት ስምረት ወላጅ አጥ ህፃናት የቤተሰብ ፍቅር አግኝተው እንዲያድጉ ከቤተሰቦቻቸው ካልሆነም ፈቃደኛ ከሆኑ ሌሎች ቤተሰቦች እንዲያድጉ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ኘሮግራሙ የህፃናትን ችግር ለመፍታት ከሚደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንዱ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ህፃናቱን የሚያሳድጉ ቤተሰቦች በየእምነት ተቋሙ የሚመለመሉ በመሆናቸው የእምነት ተቋማት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የህዝቡ የመተሳሰብና የመተባበር ባህል በማጐልበትና በማሳመን ሞራላዊና መንፈሳዊ ግዴታቸው እንዲወጡም

በሲዳማ ዞን በሁሉም ቀበሌያት 2ዐ5 ሺህ 9 መቶ 24 ሄክታር መሬት በተፋሰስ ለማልማት ከታቀደው 75 በመቶ ማከናወን መቻሉን የዞኑ ግብርና ልማት መምሪያ ገለፀ፡፡

በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ በግማሽ የበጀት አመት ቀጥታና ቀጥታ ካልሆኑ የገቢ አርዕስቶች ከ5 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ገቢ መሰብሰቡን የወረዳው ገቢዎች ባለስልጣን ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ መኩሪያ እንደገለፁት ገቢው ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውና የእቅዱ አፈፃፀም 98 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ለገቢው መገኘት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ክትትልና የቅርብ ድጋፍ ማድረጋቸው እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ጋር በቅንጅት መስራቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡በጽህፈት ቤቱ የገቢ አሰባሰብ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ፍስሐ በኬ በበኩላቸው ለባለሙያዎች በገቢ አሰባሰብ ስርአት የሚሰጠው የግልፀኝነት፣ የተጠያቂነትና የስነ ምግባር ትምህርት ስራቸውን በታማኝነት እንዲሰሩ አድርጓቸዋል ማለታቸውን የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል ፡፡ ፡

US Agency for International Development - Reading for Ethiopia's Achievement Developed (READ) including Sidama Language-- Deadline Extended

US Agency for International Development - Reading for Ethiopia's Achievement Developed (READ) -- Deadline Extended Synopsis: The purpose of this Program Description is to obtain technical assistance and services proposals from qualified institutions for implementation of “Reading for Ethiopia‘s Achievement Developed (READ) Technical Assistance project" in Ethiopia. Recipients should develop technical and financial descriptions for a five-year project that begins on or about May 2012 and ends no later than June 2017. This project will provide an innovative approach to supporting the Ethiopian Ministry of Education‘s (MOE‘s) efforts in developing a nationwide reading and writing program that will reach the vast majority of Ethiopian primary students. This project has a heavy focus on providing technical expertise in international best practices of teaching reading and writing; expertise that is to be applied to a variety of Ethiopian languages in order to develop syllabi, cur

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተፋሰስ ልማትን ለማጠናከር በውሃ ሀብት ላይ ያተኮሩ ሶስት የምርምር ፕሮጀክቶችን እያካሄደ ነዉ

Image
አዋሳ, መጋቢት 14 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የተፋሰስ ልማት ለማጠናከር በውሃ ሀብት ላይ ያተኮሩ ሶስት የምርምር ፕሮጀክቶችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ ። አለም አቀፍ የውሃ ቀን " ውሀና ምግብ ዋስትና ለሁሉም " በሚል መሪ ቃል ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት በዩኒቨርስቲው ዋናው ግቢ በፓናል ውይይትና በፎቶ ግራፍ አውደ ርእይ ተከብሯል፡፡ የዩኒቨርስቲው ምሁራን በፓናል ውይይቱ ላይ እንዳስረዱት በሀገራችን የተጀመረው የተፋሰስ ልማት ውሃን በአግባቡ ለመጠበቅና ለመጠቀም በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለዉ አስተዋጾኦ ከፍተኛ ነዉ ። በዩኒቨርስቲው የመስኖና ውሃ ሀብት ምህንድስና ትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ሄኖክ ጥላሁን እንደገለጹት የተጀመሩትን አበረታች የተፋሰስ ልማት ስራዎች ይበልጥ ለማጠናከር የርምር ፕሮጀክቶቹ እየተካሄዱ ያሉት በደቡብ ክልል በሀዋሳ ሀይቅ ፣ በብላቴ ወንዝና ሌሎች የተፋሰስ አካባቢዎች ላይ ነዉ ። ከምርምሮቹም መካከል በሀዋሳ ሀይቅ ላይ ከከተማው የተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚለቀቁ ዝቃጭ ቆሻሻዎች ለመታደግና የሃይቁን ደህንነቱ ለመጠበቅ ብሎም ለልማት እንዲውል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰሩና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በደቡብ ክልል ከሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚያካሄዳቸው የምርምር ስራዎች ወደሌሎችም የሀገራችን አካባቢዎች በማስፋፋት የድርሻውን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርስቲው የባዮ ሲስተምና ኢንቫይሮሜንታል ምህንድስና ዲፓርተመንት መምህር አቶ አሰግድ ቸርነት በበኩላቸው በተለይ ተማሪዎችንና ወጣቶች የውሃን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በውል ተገንዝበው እን