Posts

የደቡብ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመገልገል የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን አስታወቀ

Image
በደቡብ ክልል ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመገልገል በመንግስትና በህዝብ መሬትና ገንዘብ ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ኃላፊዎች ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን የክልሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ እንዳለው በተጠርጣሪዎቹ እና በግብረአበሮቻቸው የተመዘበረ የመንግስት መሬትና ገንዘብን የማስመለስ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የአዲሱ መሸሻን   ሪፖርት   ከቀጣዩ   ቪዲዮ   ይመልከቱ፡፡ http://www.ertagov.com/amerta/erta-news-archive/49-erta-tv-hot-news-addis-ababa-ethiopia/1859-2012-03-16-16-51-48.html

Previously Missed Hearing on Awassa Hotel Adjourned for Investigation

Image
Justices at the Federal Supreme Court adjourned the hearing of an appeal in the case between the Privatisation & Public Enterprises Supervising Agency (PPESA) and United Africa Group (UAG) by a little over a month, for further investigation. The parties have been locked in a courtroom battle since June 2010, after lawyers from the Agency instituted a suit at the Federal High Court, involving a claim of close to 700,000 Br in punitive damages. The Group, which acquired a state property in Hawassa Town, has failed to honour its contractual obligations. lawyers claim, UAG, established in 1992 by Haddis Tilahun, an Ethiopian residing in Namibia for 18 years, and his Namibian wife, Marta Namumdjebo, pledged to renovate Awassa Lakeside Hotels (Number One), formerly under the Wabe Shebelle Hotels brand, after it acquired it from the Agency in May 2005 for 6.95 million Br. The company acquired the only property it has in Ethiopia now, agreeing to spend a total of 18 million Br

lemboo e'ama ቆንጆ ኣይቼ ከሲዳማ

New http://www.habeshazefen.com/music/musiclist/musicnew.html?tags=http://www.habeshazefen.com/music/listenmusic/1546/konjo-aychy-ke-sidama--debub.html

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤን በኣምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ለመተካት የሲዳማን ህዝብ የማሳመን ስራ በምስጥር በመሰራት ላይ መሆኑ ተሰማ::

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል የተከሰተው የፖለቲካ ኣለመረጋጋትና ኣለመተማመን ያሰጋው የኢህኣዴግ ኣገዛዝ ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤን ከሃላፊነታቸው ለማንሳት የሲዳማን ህዝን የማሳመን ስራ ጀምሯል:: ታማኝ ምንጭች እንዳሉት ኣቶ ሽፈራውን እንዲተኩ በጃፓን የኢትዮጵያ በኣምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ታጭተዋል:: ዝርዝር ዜናውን የምቀጥለው ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ: ምንጭ :  http://www.ethiolion.com/   http://www.ethiolion.com/Pdf/031112_Shiferaw_Shigute.pdf

በሐዋሳ ከተማ ህገወጥ ነጋዴዎችና ፖሊሶች ሲታኮሱ አደሩ

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ሐዋሳ፣ ባለፈው ረቡዕ ምሸት ፖሊሶችና የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ሲታኮሱ አደሩ፡፡ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅ ባይቻልም አንድ ህፃን መቁሰሉን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡በከተማው ሐይቅ ዳር ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘውና በተለምዶ ገበያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፣ ባለፈው ረቡዕ ከምሽቱ 4፡30 ላይ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ እስከ ሌሊቱ ስምንት ሰዓት ድረስ ቀጥሎ መቆየቱንና በዚህ ምክንያትም የተመቱና የቆሰሉ ሰዎች በአዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው እንደቆዩ ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡ የተኩስ ልውውጡ መንስኤ ከኮንትሮባንድ ንግድ ጋር የተገናኘ መሆኑን የገለፁልን የክልሉ የወንጀል መከላከል ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር በላይነህ በላይ፤ በህገወጥ መንገድ የገቡና የተከማቹ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዳሉ ለፖሊስ ጥቆማ ደርሶት ወደ ስፍራው እንደሄዱ ተናግረዋል፡፡ ቦታው ሲደርሱ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎቹ ያደራጇቸውና ኮንትሮባንድ ዕቀዎቹን በመጫን፣ በማውረድና በመበለት ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በጉምሩክ ሠራተኞችና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ለማድረስ መሞከራቸውን ኮማንደር በላይነህ ገልፀዋል፡፡ በህገወጥ ነጋዴዎቹ የተደራጁት ወጣቶች፣ መሣሪያ ታጥቀው ነበር ያሉት ኮማንደሩ፤ በፀጥታ ኃይሎቹና በጉምሩከ ሠራተኞቹ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጉዳት ለማድረስ ከመሞከራቸውም በላይ ኦፕሬሽኑን ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን በሄደው የፌደራል፣ የክልሉና የከተማው የፀጥታ ኃይሎችና በጉምሩክ ሠራተኞች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ጠቁመው፤ በተኩስ ልውውጡ ከየትኛው ወገን እንደተተኮሰ ባልታወቀበት ሁኔታ አንድ ህፃን መቁሰሉን ገልፀዋል፡፡ ከችግሩ ጋር በተያያዘ 40 የሚደርሱ ሰዎች በቁ