Posts

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውስትራሊያ ጠቅላይ ገዢ አቀረቡ

Image
New አዲሰ አበባ, የካቲት 30 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) - አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአውስትራሊያ ጠቅላይ ገዢ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡ ሚኒስቴሩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ ለአውስትራሊያ መንግስት ጠቅላይ ገዢ ሚስ ኩዌንቲን ብሪክ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡ አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የሁለቱን አገራት ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንዲሚሰሩ በመግለጽ አውስትራሊያ ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የልማት እንቀስቃሴ ድጋፍ እንድትሰጥ ጠይቀዋል፡፡ በወቅቱ አውስትራሊያ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር አመርቂ ውይይት መካሔዱንም አስረድተዋል፡፡ ጠቅላይ ገዢዋ ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን መጎብኝታቸውንና በወቅቱ በአገሪቱ መንግስት ለተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዲፕሎማሲ ማእከል በመሆኗ የአውስትራሊያ አፍሪካ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ማእከል አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም ጠቁመዋል፡፡

በደቡብ ክልል ከ17ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የህፃን ለህፃናት ትምህርት ሊሰጥ ነው::በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ በ2003 የትምህርት ዘመን የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ተልጸዋል፡

Image
New አዋሳ, የካቲት 28 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል ከ17 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የህፃን ለህፃናት አቀራረብ ዘዴን በመጠቀም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በፕሮግራሙ ከስድስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ጎበዝ ተማሪዎች በማስተማሩ ስራ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በመደገፍ የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ለሚያከናውኑ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራን፣ ሱፐር ቫይዘሮችና የወላጅ መምህር ህብረት ተወካዮች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የቢሮው መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ተወካይ ወይዘሮ እናኑ ብዙነህ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የቅድመ መደበኛ ትምህርትና ክብካቤ የህፃናትን አካልና አዕምሮ በማዳበር ለመደበኛ ትምህርት ለማዘጋጀትና መሰረት ለመጣል ቁልፍ ድርሻ አለው፡፡ አስተማማኝ ድጋፍና ክብካቤ ያገኙ ህፃናት ለመደበኛ ትምህርት በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋጁ ስለሚያደረጋቸው ወደ መደበኛ ትምህርት ሲገቡ ለየደረጃው የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት በቀላሉ መረዳት እንደሚችሉና አጥጋቢ የመማር ብቃት መመዘኛዎችን አሟልተው ወደ ሚቀጥሉት እርከኖች መሸጋገር ይችላሉ ብለዋል፡፡ በክልሉ በሲዳማ ዞን በዳራ ወረዳ በ2003 የትምህርት ዘመን የህፃን ለህፃን ትምህርት ፕሮግራም በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በወረዳው የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ፕሮግራሙን በክልሉ ሁሉም አካባቢ በማስፋፋት እድሜያቸው ከሶስት እስከ ስድስት ዓመት የሆኑ ህፃናትን ተጠቃሚ ለማደረግ እየሰራ መሆኑን ወይዘሮ እናኑ ገልጸው በ2004 በጀት ዓመት በአራት ዞ

Coffee Transaction and Tax on Exported Coffee in Ethiopia: Regulations and Procedures

Coffee is the major foreign currency generating export product of Ethiopia; Ethiopia is known for its high quality, organic Arabica Coffee and also as the birth place of the commodity. A large number of exporters are engaged in coffee exporting from Ethiopia and even more number of people are engaged in businesses that involve in farming/ producing the product to finally supplying it to the exporters. Hence the authorities have been paying attention to regulate the marketing process. This article takes highlights from: 01 Coffee Quality and Marketing Proclamation No. 602/2008, Coffee Quality Control and Transaction Council of Ministers Regulations No. 161/2009 and Proclamation No.99/19998, Tax on Coffee Exported proclamation and its Amendment Proclamation No. 287/2002. Coffee Transaction Process Obligation of coffee suppliers Obligation of coffee exporters Obligations of Domestic Consumption Coffee Wholesalers Obligations of Coffee Roasters   Obligation of  Coffee Produce

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” አሉ (በመምህሩ መልካሙ)

Image
New የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ የክልሉ ፓርቲ ባደረገው ድርጅታዊ ግምገማ ውሳኔ አስተላለፈ። ፕሬዚዳንቱ “እኔ ብቻዬን መከሰስ የለብኝም። ከተከሰስኩም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር መሆን አለበት” በማለት ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ምንጮች አስታወቁ። አቶ መለስ ድርጅቱ የወሰነውን ውሳኔ ቀለበሱ።  በዚህም ሳቢያ በደቡብ ክልል የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻና የፖለቲካው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ይህ የሆነው ከየካቲት 5 ቀን እስከ የካቲት 11 ቀን 2004 ዓም ድረስ የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን የሚመራው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደኢህዴን) የከፍተኛ አመራር ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ነው። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት በክልሉ በተካሄደው ከባድ የተባለ ግምገማ ቅድሚያውን የያዙት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ነበሩ። የሲዳማ ቡና ላኪዎች ማህበር አባልና በማህበሩ ከፍተኛ ባለአክሲዮን እንደሆኑ በግምገማ የቀረበባቸው ፕሬዚዳንቱ፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መዝብረዋል በሚል ጠንካራ አውጫጪኝ ተካሄዶባቸዋል። በኢህአዴግ የፖለቲካ ቋንቋ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በ”ኪራይ ሰብሳቢነትና በሙሰኝነት” ተፈርጀዋል። እንደ መረጃ ምንጮቹ ገለጻ ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ወርደው በህግ እንዲጠየቁ ድርጅታዊ ውሳኔ ሲበየንባቸው፣ ”እኔ ብቻዬን አይደለሁም፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ጋር በጋራ ገንዘቡን ወስደናል፡፡ የምንጠየቅም ከሆነ ሁለታችንም በህግ ፊት መቅረብ አለብን፡፡ ብሩን መመለስም ካለብን ሁለታችንም እንመልስ” በማለት የግምገማ መድረ

በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ ይለማል

Image
New አዋሳ, የካቲት 23 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆነችው ቦርቻ ወረዳ በተያዘው የበልግ ወቅት ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት እየተሰራ ነው፡፡ ከልማቱም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡ አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም ምርታማነታቸውን ለማሻሻል በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አዴላ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በወረዳው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ሁሉም አርሶ አደር ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡ በወረዳው ከሚሰበሰበው ምርት 70 በመቶ ያህሉ በበልግ ወቅት ከሚለማ መሬት የሚገኝ በመሆኑ ለበልግ እርሻ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የእርሻ ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታዲዮስ ነዲ በበኩላቸው ዘንድሮ 16 ሺህ 614 ሄክታር መሬት በቦሎቄ፣ በበቆሎ እና በተለያዩ ስራስሮችና ዓመታዊ በሆኑ የተክል ዓይነቶች እንደሚሸፈን ገልፀዋል፡፡ በዘንድሮው በልግ በልዩ ልዩ ዘር ከሚሸፈነው መሬት ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ የተያዘውን ዕቅድ ለመሳካት ከወረዳ እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ከሚገኙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ከደቡብ ክልል ምርጥ ዘር አቅርቦት ድርጅት ጋር በመቀናጀት ከ1ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 850 ኩንታል ምርጥ ዘር ተገዝቶ ለአርሶ አደሩ መቅረቡንም ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም 37 ሺህ 700 ኩንታል በ