Posts

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት “እኔ ከተከሰስኩ ወ/ሮ አዜብ መስፍንም መከሰስ አለባቸው” አሉ (በመምህሩ መልካሙ)

Image
New የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ የክልሉ ፓርቲ ባደረገው ድርጅታዊ ግምገማ ውሳኔ አስተላለፈ። ፕሬዚዳንቱ “እኔ ብቻዬን መከሰስ የለብኝም። ከተከሰስኩም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር መሆን አለበት” በማለት ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ምንጮች አስታወቁ። አቶ መለስ ድርጅቱ የወሰነውን ውሳኔ ቀለበሱ።  በዚህም ሳቢያ በደቡብ ክልል የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻና የፖለቲካው ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ ይህ የሆነው ከየካቲት 5 ቀን እስከ የካቲት 11 ቀን 2004 ዓም ድረስ የደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን የሚመራው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ደኢህዴን) የከፍተኛ አመራር ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ነው። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት በክልሉ በተካሄደው ከባድ የተባለ ግምገማ ቅድሚያውን የያዙት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ነበሩ። የሲዳማ ቡና ላኪዎች ማህበር አባልና በማህበሩ ከፍተኛ ባለአክሲዮን እንደሆኑ በግምገማ የቀረበባቸው ፕሬዚዳንቱ፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መዝብረዋል በሚል ጠንካራ አውጫጪኝ ተካሄዶባቸዋል። በኢህአዴግ የፖለቲካ ቋንቋ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በ”ኪራይ ሰብሳቢነትና በሙሰኝነት” ተፈርጀዋል። እንደ መረጃ ምንጮቹ ገለጻ ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ወርደው በህግ እንዲጠየቁ ድርጅታዊ ውሳኔ ሲበየንባቸው፣ ”እኔ ብቻዬን አይደለሁም፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ጋር በጋራ ገንዘቡን ወስደናል፡፡ የምንጠየቅም ከሆነ ሁለታችንም በህግ ፊት መቅረብ አለብን፡፡ ብሩን መመለስም ካለብን ሁለታችንም እንመልስ” በማለት የግምገማ መድረ

በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበልግ ይለማል

Image
New አዋሳ, የካቲት 23 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆነችው ቦርቻ ወረዳ በተያዘው የበልግ ወቅት ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት እየተሰራ ነው፡፡ ከልማቱም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡ አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም ምርታማነታቸውን ለማሻሻል በመስራት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አዴላ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በወረዳው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ሁሉም አርሶ አደር ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው፡፡ በወረዳው ከሚሰበሰበው ምርት 70 በመቶ ያህሉ በበልግ ወቅት ከሚለማ መሬት የሚገኝ በመሆኑ ለበልግ እርሻ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የእርሻ ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታዲዮስ ነዲ በበኩላቸው ዘንድሮ 16 ሺህ 614 ሄክታር መሬት በቦሎቄ፣ በበቆሎ እና በተለያዩ ስራስሮችና ዓመታዊ በሆኑ የተክል ዓይነቶች እንደሚሸፈን ገልፀዋል፡፡ በዘንድሮው በልግ በልዩ ልዩ ዘር ከሚሸፈነው መሬት ከ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ የተያዘውን ዕቅድ ለመሳካት ከወረዳ እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር ከሚገኙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የግብርና ባለሙያዎችና ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ጽህፈት ቤቱ ከደቡብ ክልል ምርጥ ዘር አቅርቦት ድርጅት ጋር በመቀናጀት ከ1ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ 850 ኩንታል ምርጥ ዘር ተገዝቶ ለአርሶ አደሩ መቅረቡንም ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም 37 ሺህ 700 ኩንታል በ

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሽብቁ ማጋኔ በክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቀረበ ጥያቄ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተደረገ

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትናንት ማምሻውን ተጠናቀቀ ሃዋሳ, የካቲት 21 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - የደቡብ ክልል ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከ183 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ፣ አራት ዳኞችን ከሀላፊነታቸው በማንሳትና የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት በማንሳት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ጉባኤው በትናንት ውሎው ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ በተከናውኑ በትምህርት፣ በመንገድ፣ በጤናና ግብር አሰባሰብ ላይ በመወያየት የስድስት ወራት የክልሉን መንግስት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አጽድቋል። ምክር ቤቱ በበጀት ዓመቱ በቀጣይ በ15 ወረዳዎች ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ፣ በ10 ወረዳዎች አዲስ ለሚጀመሩ ፕሮጀክቶች፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለግብርናና ለክልል ቢሮዎች ለመደበኛና ለካፒታል በጀት ማሟያና ለመጠባበቂያ 183 ሚሊዮን 869 ሺህ 652 ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል። ጉባኤው የተሰጣቸውን የዳኝነት ስልጣን ተገን በማድረግ በግለሰቦች ላይ በደል ፈጽመዋል የተባሉትን የአርባምንጭ አካባቢ ጋማ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ስንታየሁ ለማ፣ በጌድዮ ዞን የቡሌ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ፍላሳ ቡርቃ፣ የቦዲቲ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ፋንታ ቤርቦና የከፋ ዞን ጠሎ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አደመ አርጋጎ ከኃላፊነታቸው በማንሳት ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ ወስኗል። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሙሉጌታ አጎን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሲሾም 24 አዲስ የወረዳ፣ የዞንና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል። ምክር ቤቱ ትናንት ማምሻውን ሲጠናቀቅ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሽብቁ ማጋኔ በክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቀረበ ጥያቄ መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው እን

PCI Receives Starbucks Foundation Grant For Sidama Coffee Farmers

New Two-year, $500,000 grant will improve health through clean water, sanitation and hygiene project San Diego, CA (PRWEB) February 27, 2012 PCI (Project Concern International) announced today it has received a $500,000 grant from the Starbucks Foundation for its Sidama Coffee Farmers Health through Water, Sanitation and Hygiene Project. The project is designed to improve the health outcomes of coffee farmers and their communities in two high-need areas in the Sidama Zone of Southern Ethiopia. The grant is part of a long-term commitment by Starbucks and the Starbucks Foundation to support relevant local needs in coffee growing communities and a continuation of supporting integrated water and sanitation programs. In Ethiopia, coffee farming is the primary source of income for many rural households, which also have some of the lowest coverage of water access, sanitation and hygiene (WASH) facilities and systems in Sub-Saharan Africa. Contamination of water sources from coffee w

Documentary - Fiche - Sidama new year

New http://www.ethiotube.net/video/15783/Documentary--Fiche--Sidama-New-Year