Posts

Debub Global to Enter Ethiopian Banking Sector

Debub Global Bank Share Company is to enter the Ethiopian banking sector in 2012. The Bank has raised 286 million birr in subscribed capital and 150 million in paid up capital through the sale of shares. 5481 shares have been presented to the National Bank pending signature and verification by shareholders according to an official at the Bank. Debub Global Bank expects to concentrate its activities in the South of Ethiopia where there exists untapped potential for investment said the official. The shareholders of the bank understand the potentials in the South and are interested in engaging in investment and trade in the area explained the official. The General Assembly of the bank has presented a list of people who could potentially serve on its board of directors and has waited six months, after meeting all requirements, to begin operations explained the official. The National Bank reviewed the thirty potential nominees to the board of directors according to their credentials

በሲዳማ ዞን ከ113 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጠ

አዋሳ, ህዳር 26 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን በበጀት አመቱ የመጀመሪያው ሩብ አመት ከ113 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላስመዘገቡ 25 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የዞኑ ንግድና ኢንደስትሪ መምሪያ ገለጸ። በመምሪያው የኢንቨስትመንት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለሀብቶቹ የሚሰማሩባቸው የስራ መስኮች በግብርና፣ በኢንዱስትሪና ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለመሰማራት ነው። በሩብ ዓመቱ ፈቃድ የወሰዱት ባለሀብቶች ቁጥር ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት በሁለት ባስመዘገቡት ካፒታል በ30 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንደነበረው ገልጸው ባለሀብቶቹ 3 ሺህ ሄክታር መሬት በማግኘታቸው ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገቡ ከ4 ሺህ 500 ለሚበልጡ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል። መምሪያው ለባለሀብቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው የተሰጣቸው ያላለሙና ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፈው የሰጡ 19 ባለሀብቶች የወሰዱትን ቦታ በመመለስ ፈቃዳችው እንዲሰረዝ ማድረጉን ጠቁመዋል። በዞኑ ወርቅ ታንታለምና የማእድን ውሃና ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ሰፊ መሬት እንደሚገኝ ጠቁመው በመስኩ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች መምሪያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በሲዳማ ዞን በወንሾ ወረዳ የተሻሻለ የቡና ዝርያ በመሰራጨት ላይ ነው

አዋሳ, ህዳር 26 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በሲዳማ ዞን በወንሾ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች በሽታና ድርቅን መቋቋም የሚችሉና የተሻለ ምርት የሚሰጡ የቡና ዝርያዎች በመሰራጨት ላይ መሆኑን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ በቀለ ሁሞ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በወንዶ ገነት ደን ኮሌጅና በጅማ ግብርና ምርምር ተቋም በአዋዳ ማዕከል በምርምር የተገኙ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡና በሽታና ድርቅ መቋቋም የሚችሉ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ሶስት ዓይነት የሲዳማ ስፔሻሊቲ ቡና ዝርያዎች እየተሰራጩ ነው። በመሰራጨት ላይ የሚገኙት የቡና ዝርያዎች በሁለት አመት ጊዜ ምርት መስጠት የሚችሉና ከነባሩ የቡና ዝርያ ጋር ሲነጻጸር ከ8 እስከ 12 ኩንታል ብልጫ ያለው ምርት በሄክታር መስጨት የሚችል መሆኑን ተናግረዋል። አዲስ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው የቡና ዝርያ እስካሁን ከስድስት መቶ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች መሰራጨቱንና በሄክታር ከ20 እስከ 25 ኩንታል ምርት መስጠት እንደቻለ አቶ በቀለ ገልጸዋል። በመጪው ሚያዚያ 2004 ለአርሶ አደሮች የሚሰራጭ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ የሲዳማ ስፔሻሊቲ ቡና ችግኝ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን ጠቁመው በመንግስት ችግኝ ጣቢያ ብቻ የሚዘጋጀው የቡና ችግኝ በቂ ባለመሆኑ በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ እንዲባዛ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል። የቡና ችግኙን በማልማት ላይ ከሚገኙት አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር አፀደ ጎኔሶ እንደገለጹት በምርምር ከተገኘው የቡና ዝርያ ለሙከራ ወስደው ካለሙት 700 ችግኝ ያገኙት ምርት ከፍተኛ በመሆኑ ችግኙን በብዛት ወስደው ለማልማት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።

በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አዳማ፤ አዲስ አበባና ሐዋሳ የተሻሉ ተሞክሮዎች ያላቸው ናቸው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አዳማ፤ አዲስ አበባና ሐዋሳ የተሻሉ ተሞክሮዎች ያላቸው ናቸው ተባለ። ሶስተኛው  የከተሞች ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ያለው ዝግጅት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በተመለከተ አየተካሄደ ባለው  የፓናል ወይይት ላይ የኤጀንሲው  ዳይሬክተር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ እንደተናገሩት ከተሞች የተሻሉ እንዲሆኑ ያስቻላቸው  የቴክኒክና ትምህርት ሙያና የብድር ተቋማት ጋር በጥምርት በመስራታቸው ነው። ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም ከእነዚህ በየከተሞቻቸው ከተደራጁት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልምድ  ሊወስዱ ይገባል blewal.

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን የትምህርት ፕሮግራም ከፈተ፤ በአምስት የትምህርት መስኮችም የድህረ ምረቃ ኘሮግራም ሊጀምር ነው

ሃዋሳ, ህዳር 21 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በተያዘው የትምህርት ዘመን የጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን የትምህርት ፕሮግራም በመጀመሪያ ዲግሪ መክፈቱን አስታወቀ፡፡ በአምስት የትምህርት መስኮችም የድህረ ምረቃ ኘሮግራም ሊጀምር ነው፡፡ የዩኒቨርሰቲው የማህበረሰብና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ንጉሴ መሸሻ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ዩኒቨርስቲው ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን የትምህርት ፕሮግራም ከ30 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል፡፡ ፕሮግራሙ የተከፈተው ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ከተሟሉ በኋላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተለይ ተማሪዎች ከንድፈ ሀሳብ ትምህርት በተጨማሪ በተግባር የተደገፈ ልምምድ የሚያደርጉበት በዩኒቨርስቲው የማህበረሰብ ሬዲዮ እንዲሁም ከደቡብ ክልል መንግስት ጋር በመተባበር የክልሉን ኤፍ ኤም ሬዲዮና ቴሌቭዥን ለመጠቀም ምቹ ሁኔታ በመፈጠር ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፕሮግራሙ መከፈት ብቃት ያለው የመገናኛና የኮሚኒኬሽን ባለሙያ በጥራት በማፍራት ሀገሪቱ ለተያያዘችው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማነት አስተዋጾኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ዩኒቨርስቲው በጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን ፣ እንግሊዘኛን እንደ መነጋገሪያ ቋንቋ ማስተማር ፣ የባህልና ዘርፈ ብዙ የቋንቋዎች ጥናት፣ ሶሻል አንትሮፖሎጂ ፣ ማስታወቂያና ህዝብ ግንኙነት የትምህርት መስኮች የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ለዚሁ ኘሮግራም የስርዓተ ትምህርት ቀረጻና ግምገማ፣ የመምህራን ምደባና የመሳሰሉ ዝግጅቶች በማካሄድ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በእያንዳንዱ ፕሮግራምም ከ10 በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው እንደሚያሰ