Posts

Ethiopian Music : Himanot Girma - Lembo

Image
New

Menalush Reta Dayo Bushu Ethiopian Ethiopia Habesha Amharic Music dvd Qu...

Image
New

Ethiopian new 2011 Mulatua Abate, Kai Kai * Sidama s Groove*

Image
New

በደቡብ ክልል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሶስት ቢሊዮን በሚበልጥ በጀት የልማት ስራ እያካሄዱ ነው

አዋሳ, ህዳር 5 ቀን 2004 (ሃዋሳ) - በደቡብ ክልል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመደቡት ከሶስት ቢሊዮን ብር የሚበልጥ በጀት ህብረተሱቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡ አብዛኛዎቹ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱት በሀዋሳ ከተማ ፣በሲዳማ ፣ በወላይታ ፣ በጋምጎፋ ፣ በሀዲያና በጉራጌ ዞኖች መሆኑን አስታውቀው የልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ታፈሰ ገዳዎ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2015 የሚካሄዱት የልማት ስራዎች 490 ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ ፕሮጀክቶቹ በ202 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንደሚካሄዱ አመልክተው የልማት ስራዎቹ የሚያተኩሩት በግብርና ፣በጤና ፣በትምህርት ፣ በመጠጥ ውሃ ፣በመስኖና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱት በሀዋሳ ከተማ ፣በሲዳማ ፣ በወላይታ ፣ በጋምጎፋ ፣ በሀዲያና በጉራጌ ዞኖች መሆኑን አስታውቀው የልማት ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ሁሉንም የክልሉ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። አፈጻጸማቸውን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እንደሚካሄድ ገልጸው መንግስታዊ ያልሆኑት ድርጅቶች ለመንግስት የልማት አጋር በመሆን የአምስት አመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሰካት የበኩላቸው አስተዋጾኦ እንዳላቸ ገልጸዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሰማንያ የሚበልጡ የምርምርና ስርፀት ተግባራትን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሰማንያ የሚበልጡ የምርምርና  ስርፀት ተግባራትን እያካሄደ ነው። ዩኒቨርሲቲው እያካሄዳቸው ያሉ የምርምርና ስርፀት ስራዎች የአካባቢውን ህብረተሰብ  ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ናቸው። ግብርና፣ ትምህርትና ጤና በምርምርና ስርፀቱ ትኩረት ተሰጥቷቸው  እየተሰሩ ያሉ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ስርፀት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ አበበ ተናግረዋል።