Posts

Image
New

በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ማርቆስ ተክሌ አምስት አባላት ያሉት ጃፓን የኢትዮጵያን ቡና እንድትገዛ የሚያግባባ የልዑካን ቡድኑ መርተው ከትናንት በስቲያ ጃፓን ገቡ፡፡

Image
የአሜሪካና የአውሮፓ ኢኮኖሚ ለሁለተኛ ጊዜ አዘቅት ውስጥ እየገባ መሆኑን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሆነው ቡና ገበያ እንዳያጣ መንግሥትና የቡና ነጋዴዎች አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን በመፈለግ ሥራ ላይ ተጠምደው ሰንብተዋል፡፡ አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎች እንዲሆኑ የተመረጡት ጃፓን፣ ቻይናና ሩሲያ ሲሆኑ፣ ለሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ የቆዩት በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ማርቆስ ተክሌ፣ አምስት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድኑ መርተው ከትናንት በስቲያ ጃፓን ገብተዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት  በጊዜያዊነት የወጣውን አዲስ ዕቅድ ማለትም የቡና ነጋዴዎች ከገበሬዎች ሰብስበው በምርት ገበያ በኩል ከሚቀርበው ቡና በተለየ ሁኔታ፣  በዩኒየኖችና  በኢንቨስተሮች የሚቀርበውን ቡና ጃፓን እንድትገዛ ለማግባባት ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው የቡና መጠን ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነውን ትገዛ የነበረችው ጃፓን፣ በቡና ውስጥ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ኬሚካሎችን አግኝቻለሁ በሚል ቡና ከኢትዮጵያ መግዛቷን በማቋረጧ ነው፡፡ የተቋረጠውን ግብይት ለማስጀመር ኢትዮጵያና ጃፓን ባለፉት ጊዜያት በጉዳዩ ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም ጃፓን ኬሚካሉን ያገኘችው ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ከተላከ ቡና እንጂ፣ በቀጥታ ከኢትዮጵያ ወደ ጃፓን ከተላከ ቡና ውስጥ አይደለም፡፡ ኬሚካል ተገኘበት የተባለው ቡና ደግሞ በጉዞና በተለያዩ ምክንያቶች ጃፓን እስኪደርስ ድረስ ስምንት ወራት የቆየ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ልትጠየቅ አይገባም የሚል መከራከርያ ቀርቧል፡፡ ይሁንና ጃፓን የኢትዮጵያን ቡና መግዛት በማቋረጥ ከቡና ውስጥ አራት ዓይነት የኬሚካል ይዘቶችን ስትመረምር ቆይታለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ሦስት ኬሚካሎችን በቡናው ውስጥ ባለማግ

ጃፓን ለሲዳማ ዞን የገንዘብ ድጋፍ ሰጠች

አዲስ አበባ, መስከረም 18 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) - ጃፓን በኢትዮጵያ በሰብአዊ ደሕንነት ላይ ለሚካሔዱ ሁለት ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል የ225 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ሰጠች፡፡ የገንዘብ ድጋፉን ለመስጠት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ የጃፓን ኤምባሲ ከሲዳማ ዞን እና ሪሰሬክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎፕመንት ከተሰኝ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን በጃፓን በኩል የፈረሙት በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሒሮዩኪ ኪሽኖ፣ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እንዲሁ የሪሰሬክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎመንት ዳይሬክተር አቶ በላቸው ለማ ናቸው፡፡ የጃፓን መንግስት ለሰብአዊ ድህነነት ስራዎች ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን ድጋፉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደሚው አምባሳደሩ ጠቁመዋል ጃፓን ከ1997 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በትምህርት፣ በመጠጥ ውሃና በሌሎችም መሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎትን በሚያሟሉ ዘርፎች ከ300 በላይ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ማድረጓን አብራርተዋል፡፡ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እና የሪሰሬክሽን ኤንድ ላይፍ ዴቨሎመንት ዳይሬክተር አቶ በላቸው ለማ በዚሁ ወቅት የገንዘብ ድጋፉን በአግባቡ ለተፈቀደለት ስራ በማዋል ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡

በብሔራዊ ባንክ ብቻ ይሰጥ የነበረው የወርቅ ግዥ ሥርዓት በሐዋሳ መስጠት ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ, መስከረም 18 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) - በብሔራዊ ባንክ ብቻ ይሰጥ የነበረው የወርቅ ግዥ ሥርዓት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በክልል አራት ከተሞች አገልግሎት መሰጠት እንደሚጀመር የማዕድን ሚኒስትሯ አስታወቁ፡፡ የማዕድን ሚኒስትር ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአገር አቀፍ ደረጃ የወርቅ አቅርቦት መጠን እየጨመረ በመመጣቱ በብሔራዊ ባንክ ብቻ ይሰጠው የነበረውን ግዥ ወደ ምርት አካባቢዎች ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴሩ ወርቅ ከሚመረትባቸው ክልሎች መካከል በሐዋሳ፣ በጅማ፣ በመቀሌና በአሶሳ በሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ግዥውን ሥርዓቱ ከሚቀጥለው ሳምንት በይፋ እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው የወርቅ መጠን ሰባት ቶን የነበረ ሲሆን፣ በያዝነው ዓመት ግን ምርትና አቅርቦቱ ከ13 ቶን በላይ ምርት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል፡፡ በክልሎች የወርቅ ግዥ ጣቢዎች መክፈት ወርቅ አቅራቢዎች ወደ አዲስ አበባ ያደርጉት የነበረውን ረጅም ጉዞ ከማስቀረቱ ባሻገር፤ ፈጣንና ቀልጣፋ የግዥ ሂደት ለመፍጠር እንደሚያስችል ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡ በተለይ ወርቅ አምራች የኅብረት ሥራ ማህበራት በአቅራቢያቸው ወርቅ የሚሸጡባቸው የግዥ ማዕከላት ባለመኖራቸው ለሌላ ገዢ በመሸጥ ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም ሳያገኙ መቆየታቸን ወይዘሮ ስንቅነሽ ገልጸዋል፡፡ በአራቱ ከተሞች የግዥ አገልግሎቱ ሲጀመር ግን የወርቅ አቅራቢዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ይሆናል ብለዋል፡፡ በክልል ከተሞች በሚካሄደው የወርቅ ግዥ ሥርዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በአዲስ አበባ ማዕከል የሚሰጡትን ዓይነት አገልግሎት እንደሚሰጡም ሚኒስትሯ አመልክተዋል፡፡ በነዚህ የግዥ ጣቢያዎች

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚመጡ ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ እንዲያሰለጥን ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት  የሚመጡ ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ ተቀብሎ እንዲያሰለጥን ተመረጠ።         ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛ ዲግሪ ስልጠና ለመስጠት የተመረጠው ከዘጠኝ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳድሮ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ነው። የዩኒቨርሲቲው ማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መልሰው ደጀኔ ለኢ ዜ አ እንዳሉት ስልጠናው የሚሰጠው በ11 የተለያዩ ፕሮግራሞች ነው። ዩኒቨርሲቲው ስልጠናውን የሚሰጠው  በአውሮፓ ታዋቂ ከሆነው ኢራስመስ ከተባለው ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ ፕሮግራም ማዕቀፍ ጋር በመተባበር ነው።