Posts

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚመጡ ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ እንዲያሰለጥን ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት  የሚመጡ ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ ተቀብሎ እንዲያሰለጥን ተመረጠ።         ዩኒቨርሲቲው በሁለተኛ ዲግሪ ስልጠና ለመስጠት የተመረጠው ከዘጠኝ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳድሮ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ነው። የዩኒቨርሲቲው ማርኬቲንግና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መልሰው ደጀኔ ለኢ ዜ አ እንዳሉት ስልጠናው የሚሰጠው በ11 የተለያዩ ፕሮግራሞች ነው። ዩኒቨርሲቲው ስልጠናውን የሚሰጠው  በአውሮፓ ታዋቂ ከሆነው ኢራስመስ ከተባለው ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ ፕሮግራም ማዕቀፍ ጋር በመተባበር ነው።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለከተማው አዲስ ከንቲባ ሾመ

  አዋሳ, ነሐሴ 30 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - በደቡብ ሕዝቦች ክልል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ተጀመረ፡፡ ምክር ቤቱ ጉባኤውን ሲጀምር ለሀዋሳ ከተማ ከንቲባነት በሙሉ ድምጽ የሾማቸው አቶ ዮናስ ዮሴፍ ቀደም ሲል የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ የነበሩ ናቸው። አዲሱ ከንቲባ ቀደም ሲልም በሲዳማ ዞን የዳሌ ወረዳ አስተዳዳሪ ፣የሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ምክር ቤቱ ሾመቱን የሰጠው ቀደም ሲል የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በነበሩት በአቶ ሽብቁ ማጋኔ ምትክ መሆኑም ተገልጿል፡፡ የከተማው ምክር ቤት ጉባኤ የ6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ በሶስት ቀናት ቆይታው በ2003 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ፣በ2004 በጀት ዓመት ዕቅድና በጀት ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡

በሀዋሳ ከተማ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልገሎት ስራ አከናወኑ

አዋሳ, ነሐሴ 30 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - በሀዋሳ ከተማ ለሁለት ወራት በተካሄደ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልገሎት ከሁለት ሚልዮን ብር የሚበልጥ ግምት ያለው ስራ መሰራቱን የከተማው ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ ገለጸ፡፡ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ ምክትል መምሪያ ሃላፊው አቶ በላይ ዲካ እንደገለጹት በከተማው ስምንት ክፍለ ከተሞች 36 ሺህ 155 ወጣቶች ነፃ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከተሳተፉት ወጣቶች መካከል ስምንት ሺህ 903 ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው ወጣቶቹ በማጠናከሪያ ትምህርት፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ችግኝ ተከላ፣ በጤና፣ በአረጋውያንና ወላጅ አልባ ህፃናት ድጋፍ ላይ ያበረከቱት አስተዋፅኦ 2 ሚልዮን 57 ሺህ 150 ብር መገመቱን አስታውቀዋል፡፡ ወጣቶቹ ከራሳቸውና ሌሎች ወገኖች አልባሳትና የፅህፈት መሳሪያ በማሰባሰብ ለ3 ሺህ 160 አረጋውያንና ወላጅ አልባ ህፃናት ከማከፋፈላቸው በተጨማሪ የስምንት አረጋውያንን መኖሪያ ቤት መጠገናቸውን ገልጸዋል፡፡ የደቡብ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ምክትል ሃላፊና የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ህይወት ሃይሉ እንዳሉት ወጣቶቹ በእረፍት ጊዜያቸው ያበረከቱት አገልግሎት ለማህበረሰቡ ካስገኙት ጠቀሜታ በተጨማሪ የህይወት ክህሎት ትምህርት የቀሰሙበት ነበር፡፡ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ተወካይ አቶ ታዬ ቢሊሶ በከተማው እየተከናወነ ያለው የልማት ስራ ቀጣይ እንዲሆን ወጣቱ በበጎ ፈቃድ አገልገሎት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበው የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልገሎት ተሳታፊ ለሆኑ ወጣቶችና ድጋፍ ላደረጉ መንግስታዊና መንግስ

Ethiopian diaspora in US to build trade center worth 127m Birr in Hawasa.

South Ethiopia Community members living in United States (US) are to build a trade center worth 127 million Birr in Hawasa town. Representatives of the Community members and government officials on Thursday held a panel discussion in ERTA studio on ways of advancing development participation for Ethiopian diaspora. On the discussions, South Ethiopia Community President in US, Abbas Hussien said members of the Community have finalized preparations to build the trade center in Hawasa town. He said the Community is receiving the necessary support from the government, in an organized activity about 200 members are undertaking to be part of the ongoing development endeavors at home. Government officials participated in the discussions stated efforts made by the government to boost development participation of Ethiopian diaspora.

How Hawassa is changing

New