Posts

How Hawassa is changing

New

በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በትምህርት ልማት ዘርፍ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የትምህርት ልማት ሰራዊቶች ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በትምህርት ልማት ዘርፍ  የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ከ100 በላይ የትምህርት ልማት ሰራዊቶች ተሸለሙ። በሃዋሳ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 17ኛው አጠቃላይ የትምህርት ጉባኤ የላቀ ውጤት  ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ትምህርት ቤቶችና የትምህርት ጽህፈት ቤቶች የማበረታቻ ሽልማት  በመስጠት ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል። ለተሸላሚዎቹም የዋንጫ፣ የሜዳሊያ የቦንድና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በሽልማት ተሰጥቷል። የጉባኤው ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫ መላውን ህብረተሰብ በላቀ ሁኔታ በማነቃቃት  የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን በሙሉ ወደ ትምሀርት  ቤት ለማምጣት በግንባር ቀደምትነት ለመንቀሳቃስ ቃል መግባታቸውን ባልደረባችን ሰለሞን ገመዳ ከሃዋሳ ዘግቧል። 

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ለ 5 ሺ 671 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 5 ፣ 2003 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት አዲሱን  ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ 5 ሺ 671 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በተለያየ የወንጀል ድርጊት  ተከሰው በፍርድ ማረሚያ ቤት ከቆዩ የህግ ታራሚዎች መካከል ይቅርታ የተደረገላቸው የባህሪ ለውጥ  ያመጡና የእስራት ጊዜያቸውን ያገባደዱ ናቸው ። የተደረገው ይቅርታ በሙስና ፣በአስገድዶ መድፈር፣ በዘር ማጥፋትና በግፍ በሰው ህይወት ማጥፋት ክስ  ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸውን እንደማይመለክትም አስታውቀዋል። ይቅርታ የሚደረግላቸው ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀለቀሉ ዳግመኛ በወንጀል ድርጊት ባለመሳተፍ  የበደሉትን ህዝብና መንግሰት መካስ እንዳለባቸው ነው የሳሰቡት። ህብረተሰቡም ይቅርታ ለተደረገላቸው ታራሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

በደቡብ ክልል የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ሊሰጠን ይገባ የነበረውን የስራ ደረጃ ዕድገት አላገኘንም አሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)  በደቡብ ክልል የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች  አምና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ሊሰጠን ይገባ የነበረውን  የስራ ደረጃ ዕድገት አላገኘንም አሉ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ  ቢሮ ሀላፊ አቶ አቶ ደበበ አበራ በበኩላቸው ችግሩ መሰረታዊ የአሰራር ሂደት ተግባራዊ ሲደረግ የተከሰተ እንደሆነ ተናግረዋል። ሰራተኞቹ ለኤፍ ቢ ሲ ሪፖርተር እንደነገሩት ከደመወዝ ጭማሪው ጋር ተያይዞ በክልሉ የመሰረታዊ  የአሰራር ሂደት ለውጥ ተግባራዊ ቢደረግም ምደባው ችግር አለበት  ነው የሚሉት። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ አቶ አቶ ደበበ አበራ በበኩላቸው  ችግሩ መሰረታዊ የአሰራር ሂደት ተግባራዊ ሲደረግ የተከሰተ እንደሆነ ተናግረዋል። በ15 ቀናት ውስጥ ቅሬታዎቹ ምላሽ እንደሚያገኙም ነው ያስታወቁት። በመላው ሀገራችን የሰራተኛውን ገቢና የኑሮ ውድነት ታሳቢ በማድረግ መንግስት  በ2003 አጋማሽ ላይ ለሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል። ይህም በሁሉም የመንግስት ሴክተር መሰሪያ ቤቶች ነው ተግባራዊ የተደረገው። ከዚህው ጋር በታያያዘም የሰራተኛው የደረጃ እድገት በአብዛኞቹ ክልሎች ተግባራዊ ተደርጓል። የደቡብ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ቅሬታ አምና ተግባራዊ ከተደረገው የደመዎዝ ጭማሪ  ጋር በተያያዘ የስራ ደረጃ አመዳደብ ጋር ይያያዛል። ሰራተኞቹ የሚያነሷቸው ቅሬታም የስራ ደረጃ ዕድገቱ ፍትሃዊ አይደለም የሚል ነው።  ሰራተኞቹ አሉ የሚሏቸውን ችግሮች ያነሳሉ። በሌሎች ክልሎች ተግባራዊ መደረጉንም ያነሳሉ። ክልሉ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልግልን ነው የሚሉት። አቶ ደበበ አበራ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳርና የቢሮው ሀላፊ ናቸው። በሀገር

ከቻይና የመጣ የልኡካን ቡድን በሀዋሳ ከተማ የተቋቋመውን የኢንዱሰትሪ መንደር ጎበኘ፡፡

ከቻይና የመጣ የልኡካን ቡድን በሀዋሳ ከተማ የተቋቋመውን የኢንዱሰትሪ መንደር ጎበኘ፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከቻይና ቾንቺን ግዛት ለመጣው የልኡካን ቡድን እንደገለጹት  የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦቸና ህዝቦች መኖሪያ የሆነው የደቡብ ክልል በኢንዱሰትሪ፣ ግብርናና አገልግሎት ተቋማት  መሳተፍ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች ዕምቅ ሃብት ይገኝበታል፡፡ በክልሉ 22 የሪፎረም ከተሞች የመሰረተ ልማት አገልገሎት የተሟላላቸው የኢንዱሰትሪ መንደሮች መዘጋጀታቸውን ገልጸው በኢንዱስትሪ ዘርፍ መስራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ ካለው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ ብዛት ያላቸው ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው እየሰሩ መሆኑን ገልጸው  በክልሉ በማንኛውም መሰክ መሰማራት ለሚፈልጉ የቻይና ባለሃብቶችን ለመቀበል የክልሉ መንግስት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከቻይና የቾንቺን ግዛት የመጡት የልዑካን ቡድን ተወካይ የክልሉ መንግስት ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው የቻይናው ሊፋን ኢንዱስትሪ ፓርክ በሀዋሳ የመኪና አካላት ማምረቻና መገጣጠሚያ መንደር ለማቋቋም የተለያየ  ስራ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የቾንቺን ግዛት በርካታ ኢንዱስትሪ የሚገኙበት መሆኑ