Posts

Sidama Lodge offering different art to suit every taste

Image
Art Appreciation’s Never-ending The crowded lobby of Sidama Lodge offering different art to suit every taste, on Wednesday, March 2, 2011, with works by various artists including, from top left, Osman,Adamseged Michael, Kidist Brehane, Teferi Mekonnen, and Nebiyu Assefa. Upon entering Sidama Lodge, located on Cape Verde Street around Bole Rwanda, one meets the work of Fitsum Wubeshet, a local artist participating in his fourth exhibition at the lodge. The general theme of his work on show depicts desolate scenes of seemingly abandoned umbrellas over wheelbarrows, and stationary bajaj taxis, seemingly going nowhere in a dust blown sunny scene. He charges 4,000 Br for each of his four artworks on show. “I determine the price according to my feeling of how good it is,” Fitsum told Fortune. “I try to say something with each piece.” Along with his participating colleagues, of which the official number is 25, but Fortune counted a total of 28, there is a lot to say. Between t

የሃዋሳ ከተማን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ልማት ለማፋጠን የነዋሪዎችና የልማት አጋሮች ተሣትፎ ወሣኝ ነው

ሃዋሣ, የካቲት 14 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - የሃዋሳ ከተማን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ልማት ለማጥፋጠን በሚደረገው ጥረት የነዋሪዎችና የልማት በአጋሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አስታወቁ፡፡ የሃዋሣ 50ኛ ዓመትና ሁለተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ቀን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ከ80 በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች የከተማው አስተዳደር ትናንት የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡ በዚሁ ወቅት ከንቲባው አቶ ሽብቁ ማጋኔ እንደገለፁት በዓሉ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ የከተማውን ሁለንተናዊ ገጽታ ለማስተዋወቅ ተችሏል፡፡ ከ80 በላይ የኢትዮጵያ ከተሞችና ከ40 በላይ ድርጅቶች የተሣተፉበትን ይህንኑ በዓል ተከትሎ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍሰት በእጅጉ መጨመሩን ገልፀዋል፡፡ በአሉ ሃዋሳ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ እንዲሁም የፈጣን ልማት፣ የእድገትና የአንድነት ተምሣሌት መሆኗን ማስመስከር የተቻለበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም ስኬት መላው ነዋሪ ህዝብና የልማት አጋሮች ያደረጉት ተሣትፎ ከፍተኛ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ለበአሉ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያደረጉ ከ80 በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች ትናንት ምሽት በተዘጋጀው ኘሮግራም ላይ ከከተማው ከንቲባ ከአቶ ሽብቁ ማጋኔ እጅ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡

በሃዋሳ ከተማ በግጭት አፈታትና ሰላም ላይ የሚመክር አህጉራዊ አውደ ጥናት ተጀመረ

ሃዋሳ, የካቲት 14 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - በምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት አባል ሀገሮች ኢጋድ ድንበር ተሻጋሪ አካባቢ በሚኖሩ ህብረተሰብ መካከል የግጭት አፈታትና ሰላም ላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ የተዘጋጀ አውደ ጥናት ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተጀመረ ። በኢጋድ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ተቋም ከጀርመን መንግስት ጋር በመተባበር ለሦስት ቀናት በተዘጋጀ አውደ ጥናት ላይ ከኢትዮጵያ ፣ከኬኒያ ፣ ከሶማሌያ፣ከጅብቲ፣ከሱዳንና ኡጋንዳ ድንበር ተሻጋሪ አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ተወካዮች መሳታፋቸውን የተቋሙ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ኦፊሰር ሚስስ ትእግስት ሀይሉ ገልፀዋል ። ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው በግጭት አፈታት ፣በሠላም ፣በልማትና ሌሎች የጋራ ስምምነትና ጥቅሞች ላይ የየአካባቢያቸውን ምርጥ ተሞክሮ በተናጥልና በቡድን በማቅረብ የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። የምርጥ ተሞክሮና የልምድ ልውውጥ መድረኩ በፊልምና በተዘጋጁ የሬዲዮ ድራማዎችና የእርስ በርስ ባህላዊ ግንኙነቶች ላይ በተደገፈ ፕሮግራም የሚካሄድ መሆኑን ገልጠዋል ። አውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው ። በአውደ ጥናቱ ላይ የየሀገሪቱ መንግስታትና የመስተዳድር ተወካዮች አጋርና መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳተፈዋል ።

Sidama Coffee continues to surprise everyone in their climb to the top of the Ethiopian Premier League

Image
Yirgalem  -  Sidama Coffee continues to surprise everyone in their climb to the top of the Ethiopian Premier League (EPL) with a 3-0 victory over Trans Ethiopia. Meskel Mengistu, Amele Milkias and Mengistu Tadele scored the goals. Meanwhile in Dire Dawa, Sebeta City held Harar Brewery to a 2-2 draw. Former St. George player Biniam Assefa scored his 11 th  goal of the season, and Ghanaian Ouwsu Rogers got the second goal. Harar’s goals came from Daniel Ayalew and Demiss Teshome. Ethiopian Coffee moved to second place of the Ethiopian Premier League Championship with a 3-1 victory over Mugher Cement here today. Mulu Alem Tilahun opened the score for Coffee but Mugher tied the game before half-time. Once again, Coffee went ahead with Mulu Alem’s second goal and Menyahel Teshome assured his team victory with the third goal. However, 15 minutes prior to the end of the game, Mugher’s fans start throwing objects onto the field and the referee had to interrupt the match. The match resum

በሀዋሳ ከተማ የተገነባው አዳሬ ሆስቲፓል ተመረቀ

Image
ኢትዮጵያ የምዕተ ዓመቱን የጤና ግቦች ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገች ነው - ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም   አዲስ አበባ፣ የካቲት 13 ፣ 2003 ( ፋና   ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት )  ኢትዮጵያየምዕተ ዓመቱን የጤና ግቦች ለማሳካት አበረታች እንቅሰቃሴዎችን እያደረገች ነው አሉ  የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ። ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሐዋሳ ከተማ  የተገነባውን የአዳሬ ሆስፒታል መርቀውሲከፍቱ እንዳሉት ሀገሪቱ በጤናው ዘርፍ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት የህጸናትና የእናቶች ሞት ጨምሮ የወባ፣የኤች አይ ቪ ኤድስናየቲቪ  በሽታዎች ቀንሰዋል፡፡ በተለይ የእናቶችን ሞት እ ኤ አ አቆጣጠር በ1990 ከነበረበት 1 ሺ 40 በአሁኑ ወቅትወደ 470 ዝቅ ማለቱን  የዓለም ጤና ድርጅት በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት አመልክቷል፡፡ ወባ፣ኤች አይ ቪ ኤድስና የቲቢ በሽታዎች ስርጭትም  ከ50 በመቶ በላይ መቀነሱን አመልክተዋል ዶክተር ቴዎድሮስ። ለዚህም ስኬት በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጤና ባለሙያዎች ማህበራትና አባላትአስተዋጽኦ በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡