Posts

The Sidama Nation: An Introduction Seyoum Hameso

Small holder farmers coping strategies to household food insecurity and hunger in Sidama Small holder farmers coping strategies to household food insecurity and hunger in Sidama To appreciate a people’s explanation of life and misfortune, one needs to have a general picture of the wider framework of their existence (Brøgger 1986:21) L ittle is known about the Sidama nation, its people, its history and culture. Sidama studies were virtually non-existent even for academic purposes. Th ere are many reasons for this. First and foremost, the emergence of enlightened nationalists and the promotion of Sidama nationalism were late and slow in comparison to other regions. Secondly, the Ethiopian historiography had no room for the promotion or development of non-Habasha cultures and peoples. Worse, still, it had circumvented and undermined knowledge production and dissemination of the latter. Th e combination of these factors engendered ambiguity about the

የቀርከሃ ማገዶና ከሰል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ቀጣይነት ባለው የደን ልማት ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች ሰሞኑን በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ የመስክ ጉብኝት ማድረጋቸው ተነገረ፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ዘርፉ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውና ከሚነገረው የቀርቀሃ ደን ከአንድ ሄክታር ከ 10 እስከ 20 ሺህ ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡ ይሁንና ግን ጥቅሙን በስፋት ለማስተዋወቅ እየተደረገ ካለው ጥረት ወጪ በበቂ ደረጃ ጥቅም ላይ ውሏል ማለት እንደማይቻል በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገለጻል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2009 በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ዓቀፍ የቀርቀሃና ራታን ኔትወርክ (Inbar) ጋር በምስራቅ አፍሪካ ያለውን እምቅ ሃብት በተለያዩ ጥቅሞች ላይ ለማዋል የተለያ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የቀርቀሃ ቴክኖሎጂዎችን ከዓለም ዙሪያ ለማሰባሰብ በማስረጽ ላይ መሆኑን ከንቲሪ ፕሮጀክት ማናጀሩ ዶክተር ፉጀኒሂ ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በቻይናና ህንድ ያለውን ልምድ በአፍሪካ ማስተዋወቅ መሆኑን በማስታወስ፡፡ የዓለም አቀፉ Inbar ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኬሽ ሆጊንደር እንዳሉት ድርጅቱ በ 36 ሃገሮች ላይ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ገልጸው፤ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን  እምቅ የቀርቀሃ ዓቅም ለማስተዋወቅ  የተለያዩ ተግባራትን እያተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በሃገሪቱ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስተር ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኤጄንሲና ከግብርና ቢሮ ጋር እንሰራለን ይህ መሆኑ ደግሞ የተፈጥሮ ሃብትን በአግባቡ ለመጠበቅ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ባፈው ሁለት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎችን በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ተገኝተው ጐብኝተዋል፡፡ በክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃጐስ አባተ በዚሁ ጉብኝት ላይ እንዳሉት የደን ውጤቶችን አብቅቶ ለማገዶ ለመጠቀም በአማካይ እስከ 30 ዓመታት የሚፈጅ ሲሆን የሚያስከትለው መዘዝም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ የቀርቀሃ ምርት ግን ከ 3 ዓመት ባልዘለለ ጊዜ ውስጥ ለተለያ ጥቅም የሚደርስ በመሆኑ ቴክኖ

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ጩኮ ወረዳ የገጠር ህብረተሰብ የአማራጭ ኢነርጂ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን ላይ ነው ተባለ።

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ጩኮ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት የኤሌክትሪ ኃይል ባልተዳረሰበት አካባቢ የሚኖረውን የገጠር ህብረተሰብ በአማራጭ የኢነርጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ግርማ ዓለሙ እንዳስታወቁት ከክልሉ ባዩ ጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር  የገጠሩን ህበረተሰብ የባዩ ጋዝ ተጠቃሚ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ከዚህ ሌላ የጽህፈት ቤታቸው ባልደረባ የሆነ አንድ ወጣት ባለሙያ የግል ፈጠራውን ተጠቅሞ በፀሐይ ሃይል የሚሰራና ለምግብ ማብሰያነት የሚያገለግል መሳሪያ ሰርቶ ለሙከራ አገልግሎት ማብቃቱን ገልጸዋል፡፡ ከመቀሌ ዩንቨርስቲ ከሜካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ትምህርቱን አጠናቆ በጽህፈት ቤቱ የአንድ የሥራ ሂደት አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ ያለው ወጣት ሰርካለም ሰለሞን የዲግሪ ማሟያ ጽሑፉን በፀሐይ ሃይል በሚሰራ መሳሪያ ዙያ እንደፃፈና ከዚህ በመነሳት መሳሪያውን የራሱን ፈጠራ ተጠቅሞ እንደሰራ አስረድቷል፡፡ የባዩ ጋዝ ቴክኖሎጂ ምግብ ለማብሰልና የብርሃን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በጤና በኩልም ወጪን ለመቀነስና ለአካባቢ ጥበቃ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡   በወረዳው ሩፎ ጫንጮ ቀበሌ የባዩ ጋዝ ተጠቃሚዎች አንዱ የሆኑት አርሶ አደር ተስፋዬ ሔሊሶ እንዳሉት ተጠቃሚ መሆን ከጀመሩ ወዲህ ኩራዝና ፋኖስ መጠቀም በመተዋቸው በየጊዜው ዋጋው ከሚያሻቅበው ከጋዝ ግዥ ድነዋል፡፡ በተጨማሪም ባለቤታቸው ምግብ ሲያበስሉ ዓይናቸውን ከሚያቃጥላቸው ጢስ መትረፋቸውንና ልጆቻቸው ደግሞ ለማገዶ እንጨት ለቀማ የሚያጠፉትን ጊዜ ለትምህርታቸው ማዋል መጀመራቸውንና ማታም እስከቻሉበት ድረስ እንደሚያጠኑ መናገራቸውን የሲዳማ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪ