Posts

የቀርከሃ ማገዶና ከሰል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋትና ቀጣይነት ባለው የደን ልማት ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች ሰሞኑን በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ የመስክ ጉብኝት ማድረጋቸው ተነገረ፡፡

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ዘርፉ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውና ከሚነገረው የቀርቀሃ ደን ከአንድ ሄክታር ከ 10 እስከ 20 ሺህ ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡ ይሁንና ግን ጥቅሙን በስፋት ለማስተዋወቅ እየተደረገ ካለው ጥረት ወጪ በበቂ ደረጃ ጥቅም ላይ ውሏል ማለት እንደማይቻል በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይገለጻል፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2009 በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ዓቀፍ የቀርቀሃና ራታን ኔትወርክ (Inbar) ጋር በምስራቅ አፍሪካ ያለውን እምቅ ሃብት በተለያዩ ጥቅሞች ላይ ለማዋል የተለያ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የቀርቀሃ ቴክኖሎጂዎችን ከዓለም ዙሪያ ለማሰባሰብ በማስረጽ ላይ መሆኑን ከንቲሪ ፕሮጀክት ማናጀሩ ዶክተር ፉጀኒሂ ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በቻይናና ህንድ ያለውን ልምድ በአፍሪካ ማስተዋወቅ መሆኑን በማስታወስ፡፡ የዓለም አቀፉ Inbar ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኬሽ ሆጊንደር እንዳሉት ድርጅቱ በ 36 ሃገሮች ላይ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ገልጸው፤ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን  እምቅ የቀርቀሃ ዓቅም ለማስተዋወቅ  የተለያዩ ተግባራትን እያተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በሃገሪቱ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስተር ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኤጄንሲና ከግብርና ቢሮ ጋር እንሰራለን ይህ መሆኑ ደግሞ የተፈጥሮ ሃብትን በአግባቡ ለመጠበቅ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ባፈው ሁለት ዓመታት የተከናወኑ ስራዎችን በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ተገኝተው ጐብኝተዋል፡፡ በክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃጐስ አባተ በዚሁ ጉብኝት ላይ እንዳሉት የደን ውጤቶችን አብቅቶ ለማገዶ ለመጠቀም በአማካይ እስከ 30 ዓመታት የሚፈጅ ሲሆን የሚያስከትለው መዘዝም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፤ የቀርቀሃ ምርት ግን ከ 3 ዓመት ባልዘለለ ጊዜ ውስጥ ለተለያ ጥቅም የሚደርስ በመሆኑ ቴክኖ

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ጩኮ ወረዳ የገጠር ህብረተሰብ የአማራጭ ኢነርጂ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን ላይ ነው ተባለ።

በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ጩኮ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት የኤሌክትሪ ኃይል ባልተዳረሰበት አካባቢ የሚኖረውን የገጠር ህብረተሰብ በአማራጭ የኢነርጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ግርማ ዓለሙ እንዳስታወቁት ከክልሉ ባዩ ጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር  የገጠሩን ህበረተሰብ የባዩ ጋዝ ተጠቃሚ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ከዚህ ሌላ የጽህፈት ቤታቸው ባልደረባ የሆነ አንድ ወጣት ባለሙያ የግል ፈጠራውን ተጠቅሞ በፀሐይ ሃይል የሚሰራና ለምግብ ማብሰያነት የሚያገለግል መሳሪያ ሰርቶ ለሙከራ አገልግሎት ማብቃቱን ገልጸዋል፡፡ ከመቀሌ ዩንቨርስቲ ከሜካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ትምህርቱን አጠናቆ በጽህፈት ቤቱ የአንድ የሥራ ሂደት አስተባባሪ በመሆን እያገለገለ ያለው ወጣት ሰርካለም ሰለሞን የዲግሪ ማሟያ ጽሑፉን በፀሐይ ሃይል በሚሰራ መሳሪያ ዙያ እንደፃፈና ከዚህ በመነሳት መሳሪያውን የራሱን ፈጠራ ተጠቅሞ እንደሰራ አስረድቷል፡፡ የባዩ ጋዝ ቴክኖሎጂ ምግብ ለማብሰልና የብርሃን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በጤና በኩልም ወጪን ለመቀነስና ለአካባቢ ጥበቃ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡   በወረዳው ሩፎ ጫንጮ ቀበሌ የባዩ ጋዝ ተጠቃሚዎች አንዱ የሆኑት አርሶ አደር ተስፋዬ ሔሊሶ እንዳሉት ተጠቃሚ መሆን ከጀመሩ ወዲህ ኩራዝና ፋኖስ መጠቀም በመተዋቸው በየጊዜው ዋጋው ከሚያሻቅበው ከጋዝ ግዥ ድነዋል፡፡ በተጨማሪም ባለቤታቸው ምግብ ሲያበስሉ ዓይናቸውን ከሚያቃጥላቸው ጢስ መትረፋቸውንና ልጆቻቸው ደግሞ ለማገዶ እንጨት ለቀማ የሚያጠፉትን ጊዜ ለትምህርታቸው ማዋል መጀመራቸውንና ማታም እስከቻሉበት ድረስ እንደሚያጠኑ መናገራቸውን የሲዳማ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪ

Ethiopian Premier League: Hawassa City moves to 2nd place

Image
Yirgalem  – Hawassa City defeated Lideta Nyala 1-0 here today to move to 2nd place in the Ethiopian Premier League (EPL). Hawassa has now 24 points, three points behind leader Defence Force (12 matches). However, Hawassa has played more matches (14) than 3 rd  place Ethiopian Coffee (21pts/11matches) and fourth Dedebit FC (16pts/10 matches). This was the only EPL match scheduled this week as St. George and Dedebit FC are competing in African Clubs competitions and the other matches were postponed. The EPL has received a lot of criticism from fans and the media for continually moving and postponing matches, thus disrupting the competition’s momentum.

አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ለተያዘው የልማት እድገት መፋጠን የጐላ ሚና እንደሚኖረው የሃዋሳ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ እንደገለጹት መምሪያው በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አገልግሎት በከተማዋ ለሚገኙ 27 ሴክተር መስሪያ ቤቶች በአመራር ሚና፣ በስነ-ምግባርና በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኛው ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ መግባት ተችሏል፡፡

ቀድሞ የነበረውን የተንዛዛ አሰራር በተቀላጠፈና ተደራሽነት ባለው መልኩ በማሳለጥ BPRን በአግባቡ በመተግበር ህበረተሰቡን በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡ ከህብረተሰቡ አስተያየት ለማወቅ እንደተቻለው ከክልል እስከ ክፍለ ከተማ በወረደው የBPR መዋቅር ሳምንታት ይወሰዱ የነበሩ ሥራዎች በሰዓታት መፈጸም ከመቻላቸውም በላይ ያለምንም መጉላላት በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል የሃዋሳ ከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ የመሬት ሽያጭና ግንባታ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ በህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፣ በአዲሱ የንግድ አሰራር አዋጅና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ላይ አስተዳደሩ እየመከረ ነው፡፡

በሃገሪቱ ህገ-መንግስት ላይ እንደተጠቀሰው መሬት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ሃብት በመሆኑ መሸጥ መለወጥ አይቻልም፡፡ የህገ-መንግስቱን መርህ ተከትሎ ሌሎች ደንቦችና መመሪያዎች የወጡ ቢሆንም በሃዋሳ ከተማ በመሬት ደላሎች በሚናፈስ የተሳሳተ መረጃ ህገ-ወጥ የመሬት ሽያጭ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሷል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ሽብቁ መገኔ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ፣ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ላይ እንደገለጹት በከተማው ካሉት 8 ክፍለ ከተሞች አንደኛው ከ100ሺህ በላይ ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ የህብረተሰቡ መተዳደሪያ እርሻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ መሆኑን እያወቁ ደላሎች አርሶ አደሩን በገንዘብ እያባበሉ መሬቱን ሽጦ ገንዘቡ ካለቀ በኋላ ልጆቹን ማስተዳደር ባለመቻሉ ወደ ጐዳና ወጥተዋል፡፡ ቢሆንም ዛሬም ህገ-ወጥ ሽያጭና ግንባታው ያልቆመ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ለእርምጃው እንዲረዳው የመጀመሪያውን የምክክር ጀምሯል፡፡ በሂደቱም መሬት የሸጠውን አርሶ አደር ግንዛቤ ካስጨበጠ በኋላ በመሬት ሽያጩ የተሳተፉትን አመራሮችና ፖሊሶችን የቀበሌ አካላትን ገምግሞ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ይደረጋል፡፡ ቀጥሎም በህገ-ወጥ ግንባታ የተሳተፉ ግለሰቦች ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ ይተላለፋል፡፡ የተቀመጠውን መርህ የማይቀበሉ ካሉ አስተዳደር ማፍረሱን ይቀጥላል፡፡ መሬቱ የአርሶ አደር መሆኑ እየታወቀ ወደ ኋላ የ10 ዓመትና ከዚያ በላይ ካርኒ በመስጠት ህጋዊ ለማድረግ በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ወደ ኋላ ሄዶ ካርኒ በመቁረጥ የህገ-መንግስቱ አዋጅ ስለማይሻር የገዙ ሰዎች በኪሳራ ቦታቸውን ለአርሶ አደሩ ለቀው ይወጣሉ፡፡ ነባሩ አርሶ አደር ቦታው ተመልሶለት በተለካ መሬት ላይ የተረጋጋ እርሻውን አርሶ ልጆቹን እንዲያሳድግ ይደረ