Posts

Ethiopian Premier League: Hawassa City moves to 2nd place

Image
Yirgalem  – Hawassa City defeated Lideta Nyala 1-0 here today to move to 2nd place in the Ethiopian Premier League (EPL). Hawassa has now 24 points, three points behind leader Defence Force (12 matches). However, Hawassa has played more matches (14) than 3 rd  place Ethiopian Coffee (21pts/11matches) and fourth Dedebit FC (16pts/10 matches). This was the only EPL match scheduled this week as St. George and Dedebit FC are competing in African Clubs competitions and the other matches were postponed. The EPL has received a lot of criticism from fans and the media for continually moving and postponing matches, thus disrupting the competition’s momentum.

አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ለተያዘው የልማት እድገት መፋጠን የጐላ ሚና እንደሚኖረው የሃዋሳ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ እንደገለጹት መምሪያው በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አገልግሎት በከተማዋ ለሚገኙ 27 ሴክተር መስሪያ ቤቶች በአመራር ሚና፣ በስነ-ምግባርና በፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኛው ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ ወደ ሙሉ ትግበራ መግባት ተችሏል፡፡

ቀድሞ የነበረውን የተንዛዛ አሰራር በተቀላጠፈና ተደራሽነት ባለው መልኩ በማሳለጥ BPRን በአግባቡ በመተግበር ህበረተሰቡን በተሻለ መልኩ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡ ከህብረተሰቡ አስተያየት ለማወቅ እንደተቻለው ከክልል እስከ ክፍለ ከተማ በወረደው የBPR መዋቅር ሳምንታት ይወሰዱ የነበሩ ሥራዎች በሰዓታት መፈጸም ከመቻላቸውም በላይ ያለምንም መጉላላት በአቅራቢያቸው በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል የሃዋሳ ከተማ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥ የመሬት ሽያጭና ግንባታ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ በህገ-ወጥ የመሬት ወረራ፣ በአዲሱ የንግድ አሰራር አዋጅና በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ላይ አስተዳደሩ እየመከረ ነው፡፡

በሃገሪቱ ህገ-መንግስት ላይ እንደተጠቀሰው መሬት የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ሃብት በመሆኑ መሸጥ መለወጥ አይቻልም፡፡ የህገ-መንግስቱን መርህ ተከትሎ ሌሎች ደንቦችና መመሪያዎች የወጡ ቢሆንም በሃዋሳ ከተማ በመሬት ደላሎች በሚናፈስ የተሳሳተ መረጃ ህገ-ወጥ የመሬት ሽያጭ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሷል፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ሽብቁ መገኔ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ፣ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ላይ እንደገለጹት በከተማው ካሉት 8 ክፍለ ከተሞች አንደኛው ከ100ሺህ በላይ ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ የህብረተሰቡ መተዳደሪያ እርሻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ መሆኑን እያወቁ ደላሎች አርሶ አደሩን በገንዘብ እያባበሉ መሬቱን ሽጦ ገንዘቡ ካለቀ በኋላ ልጆቹን ማስተዳደር ባለመቻሉ ወደ ጐዳና ወጥተዋል፡፡ ቢሆንም ዛሬም ህገ-ወጥ ሽያጭና ግንባታው ያልቆመ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ለእርምጃው እንዲረዳው የመጀመሪያውን የምክክር ጀምሯል፡፡ በሂደቱም መሬት የሸጠውን አርሶ አደር ግንዛቤ ካስጨበጠ በኋላ በመሬት ሽያጩ የተሳተፉትን አመራሮችና ፖሊሶችን የቀበሌ አካላትን ገምግሞ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ይደረጋል፡፡ ቀጥሎም በህገ-ወጥ ግንባታ የተሳተፉ ግለሰቦች ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ ይተላለፋል፡፡ የተቀመጠውን መርህ የማይቀበሉ ካሉ አስተዳደር ማፍረሱን ይቀጥላል፡፡ መሬቱ የአርሶ አደር መሆኑ እየታወቀ ወደ ኋላ የ10 ዓመትና ከዚያ በላይ ካርኒ በመስጠት ህጋዊ ለማድረግ በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ወደ ኋላ ሄዶ ካርኒ በመቁረጥ የህገ-መንግስቱ አዋጅ ስለማይሻር የገዙ ሰዎች በኪሳራ ቦታቸውን ለአርሶ አደሩ ለቀው ይወጣሉ፡፡ ነባሩ አርሶ አደር ቦታው ተመልሶለት በተለካ መሬት ላይ የተረጋጋ እርሻውን አርሶ ልጆቹን እንዲያሳድግ ይደረ

Ethiopian Premier League: Sidama Coffee & Harar Brewery victorious

Image
Sebeta  – Sidama Coffee climbed four spots (5 th  place) with a 2-1 victory over home side Sebeta City, Harar Brewery edged Mugher Cement 1-0, while last placed Fincha Sugar continues its winless season after it was held to a 2-2 draw by Commercial Banks at home, reported  Ermias Amare . Former St. George striker Binyam Assefa scored Sebeta’s consolation goal, giving him 9 goal for the season. Harar’s victory was also monumental as the club climbed five spots to 7 th  place. Unlike in the past where the top teams will be so far ahead of the rest of the group, the current season seems to be a little bit compacted, thus making it very interesting. It is true that some teams have played fewer games than others and the situation could easily be reversed. Nevertheless, the fact that 8 teams (4 th  to 12 th ) are separated by just three points keeps all teams on their toes. Saturday February 5 Dire Dawa Kenema – Trans Ethiopia 1-1 Sunday February 6 Harar Beer – Mugher Cement 1-0 F

በሃዋሳ ከተማ ባሉ የገበያ ማዕከላት እና ከማዕከላቱ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ እየተደረገ ያለው ለውጥ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማጉላት አንፃር ከፍተኛ ድርሻ እንደሚያበረክቱ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ ለውጦቹ ከማህበራዊ ፋይዳቸው በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው የጐላ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የሃዋሳ ከተማ በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ካሉ የሃገሪቱ ከተሞች መካከል አንዷ ስትሆን የነዋሪው ቁጥርም እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎችን እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል በከተማው አንድ ተጨማሪ የገበያ ማዕከል በታቦር ክፍለ ከተማ በፋራ ቀበሌ የተቋቋመ ሲሆን ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ባላቸው የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያም ለውጥ ተደርጓል፡፡ አቶ ብርሃኑ ላታሞ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በከተማው አንድ የገበያ ማዕከል  ብቻ የነበረ በመሆኑ ራቅ ባሉ የከተማው ክፍሎች ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች አዳጋች ሁኔታዎች ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ሲከናወኑ የነበሩ የጉልት እና የቆጪ ገበያዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አዲሱ ገበያ የተወሰዱ ሲሆን በቀድሞ ገበያ ቦታ ያላገኙ  እስከ 400 የሚደርሱ ነጋዴዎችም በአዲሱ ገበያ ቦታ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ይከናወኑ የነበሩ የከብት ገበያዎች ወደ አዲሱ ገበያ የተሸጋገሩ ሲሆን ገበያው አገልግሎት ከሚሰጥባቸው የእሮብ እና አርብ ቀናት በተጨማሪ በሳምንት ውስጥ ባሉ ቀናቶች ሁሉ አገልግሎቱ ይከናወናል ሲሉ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ በከተማው የተቋቋመው አዲሱ የገበያ ማዕከል በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ እና በመሰረተ ልማት እየተደራጀ እንደሚኝ አቶ ብርሃኑ ገልጸው፤ ገበያው አመቺ መንገድ የተዘረጋለት ከመሆኑ በተጨማሪም ወደ ማዕከሉ የሚደረግ ጉዞ ቀልጣፋ እንዲሆን 3 ማዕከላትን መሰረት ያደረገ የታክሲ እና የባጃጅ ስምሪት ተመድቦ ህብረተሰቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡ በከተማው ተግባራዊ ከተደረጉ ለውጦች መካከል በሰረገላ ጋሪዎች ላይ