Posts

Sidama Coffee Comparison Cupping :: Sidama vs. Sidamo

Image
By Nate This week I have ventured into the world of more formal ‘cupping’  this is the  Image from sidacoop.com process in which coffee is tasted at it’s most raw state.  The beans are ground, placed into a bowl, and hot water is poured directly onto the ground coffee.  This allows for the true flavors to shine through, without a particular brewing method influencing the taste.  I am not a formally trained ‘cupper’, but I figured I’d give it a shot, especially seeing as I received 3 varieties of coffee from the same geographical area.  I chose to do this cupping blind, by writing the name of the coffee on the bottom of the cups.  This way, I wouldn’t be swayed by any other factor than the taste of the coffee.  I’m pleased to report that all three of the coffees that I cupped were excellent, and each had unique taste profiles.  It is quite something to taste them side by side, it accentuates the variation in flavor. This was a fun experiment in cupping, and I’m going to get some fo

የሀዋሳ ከተማን የመጠጥ ውሃ እጥረት ለማቃለል በ20 ሚሊዮን ብር እየተካሄደ ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ90 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12 2003 ( ሬዲዮ ፋና ) የሀዋሳ ከተማን የመጠጥ ዉሃ እጥረት ለማቃለል በ20ሚሊዮን ብር  እየተካሄደ  ያለው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከ90 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ ። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጥልቅ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁም ተገልጧል ። የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሽብቁ ማጋኔና ሌሎች የካቢኔ አባላት በወንዶ ገነት አካባቢ የሚገኘዉን የመጠጥ ዉሃ ማስፋፊያ ግንባታ ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል ። ከንቲባዉ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት በሃዋሳ ከተማ የኢንቨስትመንት መስፋፋትን ተከትሎ  በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣዉን የመጠጥ ዉሃ ፍላጎት ለማርካት የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸዉ ። ችግሩን ለማቃለል ከአለም ባንክ በተገኘ 16 ሚሊዮን ብር እና የከተማ አስተዳደር በመደበዉ  የአራት ሚሊዮን ብር ወጪ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ስራ ከ90 በመቶ በላይ መከናወኑን አስረድተዋል። ለከተማዋ ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት ሃዌላ ወንዶና ጋራ ሊቀታ በተባሉ ስፍራዎች በሰከንድ ከ200 እስከ 300 ሊትር ዉሃ መስጠት የሚያስችሉ የሁለት ጥልቅ የዉሃ ጉድጓደችን ቆፋሮ ለማካሄድ  የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን ገልጠዋል ። በጥናቱ መሰረት ፕሮጀክቱ ለሃያ አመታት ለከተማዋ አስተማማኝ የመጠጥ ዉሀ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑም ተገልጧል ። የሃዋሳ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ለጣ የታሞ በበኩላቸዉ  በወንዶ ገነት አካባቢ በመገንባት ላይ ያለዉ የአምቦ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት በቅርቡ አገልግሎት  መስጠት ሲጀምር በሰከንድ 55 ሊትር ማምረት እንደሚቻል ተናግረዋል። የፕሮጀክቱ አማካሪ መሃንዲስ አቶ ታከለ ፍሰሃ በበኩላቸዉ በአሁኑ ወቅት የዋናዉ ምንጭ የማጎልበት  ስራና የ1

ስለ ጥንታዊው የሲዳማ መገበያያ ገንዘብ ዎማሻ ምን ያውቃሉ?

ሲዳማዎች የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከመቀላቀላቸው በፊት የራሳቸው የሆነ የመገበያያ ገንዘብ እንደነበራቸው ይነገራል። በብሔሩ አጠራር ዎማሻ ተብሎ የሚታወቀው ይህ መገበያያ ገንዘብ፤ ከማሬትሬዛ ገንዘብ በፊት የነበረ ነው። የታሪክ መዛግብት እንደሚያሳዩት ከሆነ ዎማሻ ከነሐስ የተሰራ ሳንቲም ሲሆን፤ ጠፍጣፋና ክብ ነው። የዎማሻ ክቡ ክፍል መሃሉ ላይ ክፍት ሲሆን፤ ከክቡ አንደኛው ክፍል የሚነሳ ጠፍጣፋና ሹል አካል አለው። የሲዳማ አረጋውያን የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተመለከተ እንደሚሉት ከሆነ፤ አንድ ዎማሻ እስከ አምስት መቶ ከብቶች የመግዛት አቅም ነበው። ምንጭ፤ sidama@visitsidama.com

Ethiopia Premier League: Hawassa City forces Defence Force to drop valuable points at home

Image
Addis Ababa  –Defence Force dropped two valuable points here today when they were held to a 1-1 draw by the visiting Hawassa City team. Bedasso Hora for Defence and Yitsak for Hawassa were the goal scorers. Meanwhile, Lideta Nyala shared a point with Harar Brewery (1-1) in Harar. Remaining fixtures: Sunday, December 19, 2010: Ethiopian Coffee (1) vs Fincha Sugar (15) at 3pm Ethiopian Banks (3) vs EEPCO (14) at 5pm Dire Dawa City (6) vs Sebeta City (11) at 4pm Sidama Coffee (13) vs Adama City (9) at 3pm Tuesday, December 21, 2010: Mugher Cement (10) vs Dedebit FC (5) Trans Ethiopia (7) vs St. George (16)

የሃዋሳ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማኬሄድ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ፡

የሃዋሳ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማኬሄድ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዚሁ ጉባኤው በ3 አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ በዚሁም መሰረት የ1ኛ ዙር 2ኛ ዓመት ስራ ዘመን የ5ኛ መደበኛ ጉባኤንና የ1ኛ ዙር 3ኛ ዓመት ስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤዎችን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ የሹመት ሥነ-ሥርዓትም አካሂዷል፡፡ ምክር ቤቱ በዋና አፈ-ጉባኤነት እንዲመሩ የተከበሩ አቶ ደምሴ ደንጊሶን  በዋና አፈ-ጉባኤነት ሾሟል፡፡ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ሽብቁ ማጋኔ እንዳስታወቁት ከተማዋ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያና የቱሪስት መዳረሻ በመሆኗ የባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ እንዲዋቀር ተደርጓል ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ምክር ቤቱን በዋና አፈ-ጉባኤነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ ዘላለም ላሌን የባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ሆነው እንዲሾሙ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ ከንቲባው እንዳሉት ሹመቱ የተሰጣቸው ባላቸው የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተሿሚዎችም የቃለ-መሃላ ሥነ-ሥርዓት መፈፀማቸውን ባልደረባችን ታምራት ሽብሩ ዘግቧል፡፡